ማቴዎስ 5 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 5:1-48

የተራራው ስብከት

5፥3-12 ተጓ ምብ – ሉቃ 6፥20-23

1ብዙ ሕዝብ እንደ ተሰበሰበ ባየ ጊዜ፣ ወደ ተራራ ወጣና ተቀመጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጡ። 2እንዲህም እያለ ያስተምራቸው ጀመር፤

3“በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤

መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

4የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤

መጽናናትን ያገኛሉና።

5የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤

ምድርን ይወርሳሉና።

6ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤

ይጠግባሉና።

7ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤

ምሕረትን ያገኛሉና።

8ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤

እግዚአብሔርን ያዩታልና።

9ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።

10ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤

መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

11“ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። 12በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳድደዋቸዋልና።

ጨውና ብርሃን

13“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጣዕሙን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም።

14“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ 15ሰዎችም መብራት አብርተው ከዕንቅብ ሥር አያስቀምጡትም፤ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ። 16እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።

የሕግ ፍጻሜ

17“ሕግንና የነቢያትን ቃል ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ለመፈጸም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። 18እውነት እላችኋለሁ፤ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ሕግ ሁሉ ይፈጸማል እንጂ ከሕግ አንዲት ፊደል ወይም አንዲት ነጥብ እንኳ አትሻርም። 19ስለዚህ ማንም ከእነዚህ ትእዛዞች አነስተኛዪቱን እንኳ ቢተላለፍ፣ ሌሎችንም እንዲተላለፉ ቢያስተምር፣ በመንግሥተ ሰማይ ታናሽ ተብሎ ይጠራል፤ ነገር ግን እነዚህን ትእዛዞች እየፈጸመ ሌሎችም እንዲፈጽሙ የሚያስተምር በመንግሥተ ሰማይ ታላቅ ይባላል። 20ጽድቃችሁ ከፈሪሳውያንና ከኦሪት ሕግ መምህራን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ መንግሥተ ሰማይ መግባት አትችሉም።

ነፍስ መግደል አይገባም

5፥2526 ተጓ ምብ – ሉቃ 12፥5859

21“ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘አትግደል፤ የገደለ ይፈረድበታል’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ 22እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወንድሙን ያለ አግባብ የሚቈጣ ይፈረድበታል፤ ማንም ወንድሙን ‘ጅል’ የሚል በሸንጎ ፊት ይጠየቅበታል፤ ‘ደደብ’ የሚለው ደግሞ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጠብቀዋል።

23“ስለዚህ መባህን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በምታቀርብበት ጊዜ፣ ወንድምህ የተቀየመብህ ነገር መኖሩ ትዝ ቢልህ፣ 24መባህን በዚያው በመሠዊያው ፊት ተወው፤ በመጀመሪያ ሄደህ ከወንድምህ ጋር ተስማማ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን ለእግዚአብሔር አቅርብ።

25“የከሰሰህ ባላጋራህ እንዳያስፈርድብህ፣ ዳኛውም ለአሳሪ አሳልፎ እንዳይሰጥህ፣ በወህኒም እንዳትጣል፣ በመንገድ ላይ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ። 26እውነት እልሃለሁ፤ ካስፈረደብህ ግን የመጨረሻዋን ሳንቲም5፥26 ግሪኩ ኮድራንቴስ ይላል። እስክትከፍል ድረስ ከዚያ አትወጣም።

ማመንዘር አይገባም

27“ ‘አታመንዝር’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 28እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ሴትን በምኞት ዐይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሯል። 29ቀኝ ዐይንህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል። 30ቀኝ እጅህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ ቈርጠህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።

31“ ‘ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ የፍቺ ወረቀት መስጠት አለበት’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 32እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በላዩ ላይ ስታመነዝር ካላገኛት በስተቀር፣ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እንድታመነዝር ያደርጋታል፤ በዚህ ሁኔታ የተፈታችውን ሴት ያገባም እንዳመነዘረ ይቈጠራል።

ስለ መሐላ

33“ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘በሐሰት አትማል፤ በእግዚአብሔር ፊት የማልኸውንም ጠብቅ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 34እኔ ግን ፈጽሞ አትማሉ እላችኋለሁ፤ በሰማይም ቢሆን አትማሉ፤ የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤ 35በምድርም ቢሆን አትማሉ፤ የእግዚአብሔር የእግሩ ማረፊያ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አትማሉ፤ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና 36በራስህም ቢሆን አትማል፤ ከጠጕራችሁ መካከል አንዲቷን እንኳ ነጭ ወይም ጥቍር ማድረግ አትችሉምና። 37ስለዚህ ስትነጋገሩ ቃላችሁ፣ ‘አዎን’ ከሆነ፣ ‘አዎን’፤ አይደለም፣ ከሆነ ‘አይደለም’ ይሁን፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ሁሉ ከክፉው የሚመጣ ነውና።

ስለ መበቀል

38“ ‘ዐይን ስለ ዐይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 39እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ‘ክፉ አድራጊውን ሰው አትቃወሙት’፤ ነገር ግን ቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ አዙርለት። 40አንድ ሰው እጀ ጠባብህን ሊወስድ ቢከስስህ ካባህን ጨምረህ ስጠው። 41አንድ ሰው አንድ ኪሎ ሜትር ተኩል የሚያህል ርቀት እንድትሄድ ቢያስገድድህ ዕጥፉን መንገድ አብረኸው ሂድ። 42ለሚለምንህ ስጥ፤ ከአንተም ሊበደር የሚሻውን ፊት አትንሣው።

43“ ‘ወዳጅህን ውደድ፤ ጠላትህን ጥላ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 44እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤5፥44 አንዳንድ የጥንት ቅጆች የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ ይላሉ። ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ። 45እንደዚህም በማድረጋችሁ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ፀሓዩን ለክፉዎችና ለደጎች ያወጣል፤ ዝናቡንም ለኀጢአተኞችና ለጻድቃን ያዘንባል። 46የሚወድዷችሁን ብቻ የምትወድዱ ከሆነ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮችስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? 47ወንድሞቻችሁን ብቻ እጅ የምትነሡ ከሆነ ከሌሎች በምን ትሻላላችሁ? አሕዛብስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? 48ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።

King James Version

Matthew 5:1-48

1And seeing the multitudes, he went up into a mountain: and when he was set, his disciples came unto him: 2And he opened his mouth, and taught them, saying, 3Blessed are the poor in spirit: for theirs is the kingdom of heaven. 4Blessed are they that mourn: for they shall be comforted. 5Blessed are the meek: for they shall inherit the earth. 6Blessed are they which do hunger and thirst after righteousness: for they shall be filled. 7Blessed are the merciful: for they shall obtain mercy. 8Blessed are the pure in heart: for they shall see God. 9Blessed are the peacemakers: for they shall be called the children of God. 10Blessed are they which are persecuted for righteousness’ sake: for theirs is the kingdom of heaven. 11Blessed are ye, when men shall revile you, and persecute you, and shall say all manner of evil against you falsely, for my sake. 12Rejoice, and be exceeding glad: for great is your reward in heaven: for so persecuted they the prophets which were before you.

13¶ Ye are the salt of the earth: but if the salt have lost his savour, wherewith shall it be salted? it is thenceforth good for nothing, but to be cast out, and to be trodden under foot of men. 14Ye are the light of the world. A city that is set on an hill cannot be hid. 15Neither do men light a candle, and put it under a bushel, but on a candlestick; and it giveth light unto all that are in the house. 16Let your light so shine before men, that they may see your good works, and glorify your Father which is in heaven.

17¶ Think not that I am come to destroy the law, or the prophets: I am not come to destroy, but to fulfil. 18For verily I say unto you, Till heaven and earth pass, one jot or one tittle shall in no wise pass from the law, till all be fulfilled. 19Whosoever therefore shall break one of these least commandments, and shall teach men so, he shall be called the least in the kingdom of heaven: but whosoever shall do and teach them, the same shall be called great in the kingdom of heaven. 20For I say unto you, That except your righteousness shall exceed the righteousness of the scribes and Pharisees, ye shall in no case enter into the kingdom of heaven.

21¶ Ye have heard that it was said by them of old time, Thou shalt not kill; and whosoever shall kill shall be in danger of the judgment: 22But I say unto you, That whosoever is angry with his brother without a cause shall be in danger of the judgment: and whosoever shall say to his brother, Raca, shall be in danger of the council: but whosoever shall say, Thou fool, shall be in danger of hell fire. 23Therefore if thou bring thy gift to the altar, and there rememberest that thy brother hath ought against thee; 24Leave there thy gift before the altar, and go thy way; first be reconciled to thy brother, and then come and offer thy gift. 25Agree with thine adversary quickly, whiles thou art in the way with him; lest at any time the adversary deliver thee to the judge, and the judge deliver thee to the officer, and thou be cast into prison. 26Verily I say unto thee, Thou shalt by no means come out thence, till thou hast paid the uttermost farthing.

27¶ Ye have heard that it was said by them of old time, Thou shalt not commit adultery: 28But I say unto you, That whosoever looketh on a woman to lust after her hath committed adultery with her already in his heart. 29And if thy right eye offend thee, pluck it out, and cast it from thee: for it is profitable for thee that one of thy members should perish, and not that thy whole body should be cast into hell. 30And if thy right hand offend thee, cut it off, and cast it from thee: for it is profitable for thee that one of thy members should perish, and not that thy whole body should be cast into hell. 31It hath been said, Whosoever shall put away his wife, let him give her a writing of divorcement: 32But I say unto you, That whosoever shall put away his wife, saving for the cause of fornication, causeth her to commit adultery: and whosoever shall marry her that is divorced committeth adultery.

33¶ Again, ye have heard that it hath been said by them of old time, Thou shalt not forswear thyself, but shalt perform unto the Lord thine oaths: 34But I say unto you, Swear not at all; neither by heaven; for it is God’s throne: 35Nor by the earth; for it is his footstool: neither by Jerusalem; for it is the city of the great King. 36Neither shalt thou swear by thy head, because thou canst not make one hair white or black. 37But let your communication be, Yea, yea; Nay, nay: for whatsoever is more than these cometh of evil.

38¶ Ye have heard that it hath been said, An eye for an eye, and a tooth for a tooth: 39But I say unto you, That ye resist not evil: but whosoever shall smite thee on thy right cheek, turn to him the other also. 40And if any man will sue thee at the law, and take away thy coat, let him have thy cloke also. 41And whosoever shall compel thee to go a mile, go with him twain. 42Give to him that asketh thee, and from him that would borrow of thee turn not thou away.

43¶ Ye have heard that it hath been said, Thou shalt love thy neighbour, and hate thine enemy. 44But I say unto you, Love your enemies, bless them that curse you, do good to them that hate you, and pray for them which despitefully use you, and persecute you; 45That ye may be the children of your Father which is in heaven: for he maketh his sun to rise on the evil and on the good, and sendeth rain on the just and on the unjust. 46For if ye love them which love you, what reward have ye? do not even the publicans the same? 47And if ye salute your brethren only, what do ye more than others? do not even the publicans so? 48Be ye therefore perfect, even as your Father which is in heaven is perfect.