ማቴዎስ 14 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 14:1-36

የመጥምቁ ዮሐንስ መሞት

14፥1-12 ተጓ ምብ – ማር 6፥14-29

1በዚያን ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረው፣ ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ዝና ሰማ፤ 2ባለሟሎቹንም፣ “እንዲህ ከሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶ መጥቷል ማለት ነው፤ ይህ ሁሉ ድንቅ ታምራት በእርሱ የሚደረገውም ለዚህ ነው” አላቸው።

3ቀደም ሲል ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ ወህኒ አስገብቶት ነበር። 4ምክንያቱም ዮሐንስ፣ “እርሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር። 5ሄሮድስም ዮሐንስን ሊገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለ ነበር ፈራ።

6ሄሮድስ የልደቱን ቀን ሲያከብር፣ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን ደስ ስላሰኘችው፣ 7የምትጠይቀውን ሁሉ ሊሰጣት በመሐላ ቃል ገባላት። 8ልጅቷም በእናቷ ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በሳሕን ላይ አድርገህ አሁኑኑ ስጠኝ” አለችው። 9በዚህ ጊዜ ንጉሡ ዐዘነ፤ ይሁን እንጂ ስለ መሐላውና ከእርሱ ጋር ስለ ነበሩ እንግዶች ሲል ጥያቄዋ እንዲፈጸምላት አዘዘ። 10ልኮም በወህኒ ውስጥ እንዳለ የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ። 11የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን ላይ አድርገው ለልጂቱ ሰጧት፤ ልጂቱም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። 12የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትም አስከሬኑን ወስደው ቀበሩት፤ ከዚያም ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት።

ኢየሱስም አምስት ሺሕ ሰዎችን በታምር መገበ

14፥13-21 ተጓ ምብ – ማር 6፥32-44ሉቃ 9፥10-17ዮሐ 6፥1-13

14፥13-21 ተጓ ምብ – ማቴ 15፥32-38

13ኢየሱስ የሆነውን ነገር በሰማ ጊዜ፣ ከነበረበት ተነሥቶ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ በጀልባ ሄደ። ሕዝቡም ይህን ሰምተው፣ ከየከተማው በእግር ተከተሉት። 14ኢየሱስም ከጀልባው ሲወርድ ብዙ ሕዝብ አይቶ ራራላቸው፤ ሕመምተኞቻቸውንም ፈወሰላቸው።

15እየመሸ በመሄዱም ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ይህ ስፍራ ምንም የማይገኝበት ምድረ በዳ ነው፤ ጊዜው እየመሸ ስለሆነ፣ ወደ መንደሮች ሄደው የሚበሉት ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት” አሉት።

16ኢየሱስ ግን፣ “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው” አላቸው።

17እነርሱም፣ “በዚህ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው” አሉት።

18እርሱም፣ “እስቲ ያለውን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው። 19ከዚያም ሕዝቡ በሣሩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ዐይኑን ወደ ሰማይ በማቅናት አመስግኖና ባርኮ እንጀራውን ቈረሰ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሰጠ፤ እነርሱም ለሕዝቡ ሰጡ። 20ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ የተረፈውን ቍርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ። 21የበሉትም ከሴቶችና ከሕፃናት ሌላ፣ አምስት ሺሕ ወንዶች ያህሉ ነበር።

ኢየሱስ በባሕር ላይ በእግሩ ሄደ

14፥22-33 ተጓ ምብ – ማር 6፥45-51ዮሐ 6፥15-21

14፥34-36 ተጓ ምብ – ማር 6፥53-56

22ወዲያውኑ ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ተሳፍረው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት አዘዛቸውና እርሱ ሕዝቡን ለማሰናበት ወደ ኋላ ቀረት አለ። 23ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላም ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ፤ በጨለመም ጊዜ ብቻውን በዚያው ነበር፤ 24በዚያ ጊዜ ጀልባዋ ባሕሩን ዘልቃ14፥24 ግሪኩ ብዙ ምዕራፍ ይላል። እየተጓዘች ሳለች ነፋስ ተነሥቶ በማዕበል ትንገላታ ጀመር።

25ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት መጣ። 26ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ እየተራመደ ሲመጣ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ምትሀት ነው!” በማለት በፍርሀት ጮኹ።

27ኢየሱስም ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ፤ እኔ ነኝ አትፍሩ” አላቸው።

28ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ከሆንህስ፣ በውሃው ላይ እየተራመድሁ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” አለው።

29እርሱም፣ “ና” አለው።

ጴጥሮስም፣ ከጀልባው ወርዶ በውሃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ። 30ነገር ግን የነፋሱን ኀይል ባየ ጊዜ ፈራ፤ መስጠምም ሲጀምር፣ “ጌታ ሆይ፤ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ።

31ኢየሱስም ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጐደለህ፤ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።

32ኢየሱስና ጴጥሮስ ጀልባው ላይ እንደ ወጡ ነፋሱ ጸጥ አለ። 33ከዚያም በጀልባው ውስጥ የነበሩት፣ “በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።

ፈውስ በጌንሴሬጥ

34ባሕሩን ከተሻገሩ በኋላ ጌንሴሬጥ ወደ ተባለ ቦታ ደረሱ። 35ነዋሪዎቹም ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በዙሪያው ወዳለ አካባቢ ሁሉ መልእክት ላኩ፤ የታመሙትን ሁሉ ወደ እርሱ በማስመጣት፣ 36በሽተኞቹ የልብሱን ጫፍ ብቻ ይነኩ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።

King James Version

Matthew 14:1-36

1At that time Herod the tetrarch heard of the fame of Jesus, 2And said unto his servants, This is John the Baptist; he is risen from the dead; and therefore mighty works do shew forth themselves in him.

3¶ For Herod had laid hold on John, and bound him, and put him in prison for Herodias’ sake, his brother Philip’s wife. 4For John said unto him, It is not lawful for thee to have her. 5And when he would have put him to death, he feared the multitude, because they counted him as a prophet. 6But when Herod’s birthday was kept, the daughter of Herodias danced before them, and pleased Herod. 7Whereupon he promised with an oath to give her whatsoever she would ask. 8And she, being before instructed of her mother, said, Give me here John Baptist’s head in a charger. 9And the king was sorry: nevertheless for the oath’s sake, and them which sat with him at meat, he commanded it to be given her. 10And he sent, and beheaded John in the prison. 11And his head was brought in a charger, and given to the damsel: and she brought it to her mother. 12And his disciples came, and took up the body, and buried it, and went and told Jesus.

13¶ When Jesus heard of it, he departed thence by ship into a desert place apart: and when the people had heard thereof, they followed him on foot out of the cities. 14And Jesus went forth, and saw a great multitude, and was moved with compassion toward them, and he healed their sick.

15¶ And when it was evening, his disciples came to him, saying, This is a desert place, and the time is now past; send the multitude away, that they may go into the villages, and buy themselves victuals. 16But Jesus said unto them, They need not depart; give ye them to eat. 17And they say unto him, We have here but five loaves, and two fishes. 18He said, Bring them hither to me. 19And he commanded the multitude to sit down on the grass, and took the five loaves, and the two fishes, and looking up to heaven, he blessed, and brake, and gave the loaves to his disciples, and the disciples to the multitude. 20And they did all eat, and were filled: and they took up of the fragments that remained twelve baskets full. 21And they that had eaten were about five thousand men, beside women and children.

22¶ And straightway Jesus constrained his disciples to get into a ship, and to go before him unto the other side, while he sent the multitudes away. 23And when he had sent the multitudes away, he went up into a mountain apart to pray: and when the evening was come, he was there alone. 24But the ship was now in the midst of the sea, tossed with waves: for the wind was contrary. 25And in the fourth watch of the night Jesus went unto them, walking on the sea. 26And when the disciples saw him walking on the sea, they were troubled, saying, It is a spirit; and they cried out for fear. 27But straightway Jesus spake unto them, saying, Be of good cheer; it is I; be not afraid. 28And Peter answered him and said, Lord, if it be thou, bid me come unto thee on the water. 29And he said, Come. And when Peter was come down out of the ship, he walked on the water, to go to Jesus. 30But when he saw the wind boisterous, he was afraid; and beginning to sink, he cried, saying, Lord, save me. 31And immediately Jesus stretched forth his hand, and caught him, and said unto him, O thou of little faith, wherefore didst thou doubt? 32And when they were come into the ship, the wind ceased. 33Then they that were in the ship came and worshipped him, saying, Of a truth thou art the Son of God.

34¶ And when they were gone over, they came into the land of Gennesaret. 35And when the men of that place had knowledge of him, they sent out into all that country round about, and brought unto him all that were diseased; 36And besought him that they might only touch the hem of his garment: and as many as touched were made perfectly whole.