ማርቆስ 16 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ማርቆስ 16:1-20

ትንሣኤው

16፥1-8 ተጓ ምብ – ማቴ 28፥1-8ሉቃ 24፥1-10

1ሰንበት ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሄደው የኢየሱስን ሥጋ ለመቀባት ሽቱ ገዙ። 2በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ጧት በማለዳ፣ ገና ፀሓይ እንደ ወጣች፣ ወደ መቃብሩ በመሄድ ላይ ሳሉ፣ 3“ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ላይ ማን ያንከባልልልናል?” በማለት እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።

4ቀና ብለው ሲመለከቱ፣ በጣም ትልቅ የነበረው ድንጋይ ከደጃፉ ላይ ተንከባልሎ አዩ። 5ወደ መቃብሩ እንደ ገቡም፣ ነጭ ልብስ የለበሰ ጕልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።

6እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትደንግጡ፤ የምትፈልጉት የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፤ እርሱ ተነሥቷል፤ እዚህ የለም፤ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ። 7ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ፣ ‘ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ እንደ ነገራችሁ እዚያ ታገኙታላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው።”

8ሴቶቹም እየተንቀጠቀጡና እየተደነቁ ከመቃብሩ ሸሽተው ወጡ፤ ፈርተው ስለ ነበር ለማንም አንዳች አልተናገሩም።

9በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ማለዳ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለማርያም መግደላዊት በመጀመሪያ ታየ። 10እርሷም ሄዳ፣ ከእርሱ ጋር የነበሩት እያዘኑ ሲያለቅሱ አግኝታ፣ 11እርሱ ሕያው መሆኑንና ለእርሷም መታየቱን ነገረቻቸው፤ እነርሱ ግን አላመኗትም።

12ከዚህ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱ ወደ ገጠር ሲሄዱ በሌላ መልክ ታያቸው። 13እነርሱም ተመልሰው ይህንኑ ለቀሩት ነገሯቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱንም አላመኗቸውም።

14ከዚያም ዐሥራ አንዱ በማእድ ላይ ሳሉ ተገለጠላቸው፤ ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች የነገሯቸውን ስላላመኗቸው፣ አለማመናቸውንና የልባቸውን ድንዳኔ ነቀፈ። 15እንዲህም አላቸው፤ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ 16ያመነ የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። 17የሚያምኑትን እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ልሳንም ይናገራሉ፤ 18እባቦችን በእጃቸው ይይዛሉ፤ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውንም በሕመምተኞች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይፈወሳሉ።”

19ጌታ ኢየሱስ ይህን ከተናገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። 20ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ወጥተው፣ በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ ትምህርታቸውንም ተከትለው በሚፈጸሙ ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።16፥20 አንዳንድ የጥንት ቅጆች ከ9-20 ያለው ክፍል የላቸውም።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

马可福音 16:1-20

耶稣复活

1过了安息日,抹大拉玛丽亚雅各的母亲玛丽亚撒罗米买了香料,要去抹耶稣的遗体。 2周日清早,太阳刚刚升起,她们就去坟墓那里。 3途中她们彼此议论说:“谁能替我们滚开墓口那块大石头呢?” 4她们抬头一看,那块大石头已经滚到一旁。 5她们进了坟墓,看见一位身穿洁白长袍的青年坐在右边,吓了一跳。 6那青年对她们说:“不要害怕,你们要找那位被钉十字架的拿撒勒人耶稣吗?祂已经复活了,不在这里。你们看!这是安放祂的地方。 7你们快回去,告诉祂的门徒,特别是彼得,‘祂先你们一步去了加利利,你们将在那里见到祂,正如祂以前所说的一样。’”

8她们从坟墓出来,跑走了,战战兢兢,疑惑不已,什么也没有告诉他人,因为她们很害怕。

耶稣显现

9耶稣在周日清晨复活后,首先向抹大拉玛丽亚显现,耶稣曾在她身上赶出七个鬼。 10玛丽亚赶到门徒那里,看见他们仍然在哭泣哀悼, 11就告诉他们耶稣已经复活了,还向她显现过,但他们不相信。

12此后,有两个门徒在去乡下的路上,看到耶稣以另一种形象向他们显现。 13他们回去告诉其他的门徒,但门徒还是不相信。

最后的使命

14后来,当十一位门徒在一起吃饭的时候,耶稣向他们显现,责备他们又不信又固执,因为他们不肯相信那些人在祂复活后见过祂。 15耶稣又对他们说:“你们要到世界各地去,向全人类传扬福音。 16相信并接受洗礼的人必定得救,不肯相信的人必被定罪。 17必有神迹随着信我的人,他们能奉我的名赶鬼,说新的方言, 18又能用手拿蛇,万一喝了什么毒物,也不会受害。他们把手按在病人身上,病人就可痊愈。” 19主耶稣说完这些话,就被接回天上,坐在上帝的右边。 20门徒出去到处传扬福音,主和他们一同工作,借着神迹证实他们所传的道。