መዝሙር 65 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 65:1-13

መዝሙር 65

የምስጋና መዝሙር

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤65፥1 በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጉም በትክክል አይታወቅም።

ለአንተ የተሳልነውን እንፈጽማለን።

2ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፤

የሰው ልጆች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ።

3ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣

አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።65፥3 ወይም አንተ ተቤዠኸን

4አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣

በአደባባይህም ያኖርኸው ምስጉን ነው!

ከተቀደሰው መቅደስህ፣

ከቤትህም በረከት እንረካለን።

5እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤

በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤

አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣

በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ።

6ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤

ኀይልንም ታጥቀሃል።

7አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣

የማዕበላቸውን ፉጨት፣

የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።

8ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤

የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣

በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ።

9ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤

እጅግ ታበለጥጋታለህም።

ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣

የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤

አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና።65፥9 ወይም “አንተም ለዚህ ነው ምድርን ያዘጋጀሃት”

10ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤

ቦይዋን ታስተካክላለህ፤

በካፊያ ታለሰልሳለህ፤

ቡቃያዋንም ትባርካለህ።

11ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤

ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል።

12የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤

ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።

13ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤

ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤

እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 65:1-13

第 65 篇

赞美和感恩

大卫作的诗,交给乐长。

1上帝啊,

人们在锡安赞美你,

向你履行誓言。

2你垂听祷告,

世人都来到你面前。

3虽然我们深陷罪中,

你却赦免了我们。

4蒙你拣选、

能住在你圣所的人有福了!

我们在你美好的居所,

你圣洁的殿中心满意足。

5拯救我们的上帝啊,

你凭公义、行可畏之事来应允我们的祈求。

你是普天下的盼望。

6你充满力量,以大能创造群山,

7又平息怒海狂涛,

止息列邦的喧嚣。

8你奇妙的作为使远在地极的人心生敬畏,

你使日出之地和日落之处都传来欢呼声。

9你眷顾大地,降下沛雨,

使土地肥沃富饶。

上帝啊,你使江河涌流不息,

浇灌大地,为世人预备五谷。

10你降下甘霖,浇透垄沟,

滋润垄背,使地松软、

长出庄稼。

11你赐下丰年福月,

你的脚踪恩泽满溢。

12旷野的草地生机盎然,

山岭间充满欢乐,

13草场遍布羊群,

谷中长满庄稼,

处处欢歌笑语。