መዝሙር 27 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 27:1-14

መዝሙር 27

ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ሰው ድፍረት

የዳዊት መዝሙር።

1እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤

የሚያስፈራኝ ማን ነው?

እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤

ማንን እፈራለሁ?

2ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣27፥2 ወይም ስሜን ሊያጠፉ

ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣

ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣

እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።

3ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣

ልቤ አይፈራም፤

ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣

ልበ ሙሉ ነኝ።

4እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤

እርሷንም እሻለሁ፤

ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣

በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣

የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣

በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።

5በመከራ ቀን፣

በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤

በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል።

6በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣

ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤

በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤

ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤

እዘምርለታለሁም።

7እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤

ራራልኝ፤ ስማኝም።

8“ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤27፥8 ወይም ልቤ ሆይ፤ ለአንተ “ፊቴን” አለ

ልቤ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።

9ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤

ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤

መቼም ረዳቴ ነህና።

አዳኝ አምላኬ ሆይ፤

አትጣለኝ፤ አትተወኝም።

10አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ፣

እግዚአብሔር ይቀበለኛል።

11እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤

ስለ ጠላቶቼም፣

በቀና መንገድ ምራኝ።

12ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ፤

የሐሰት ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፣

ዐመፃ የሚረጩ ናቸው።

13የእግዚአብሔርን ቸርነት

በሕያዋን ምድር እንደማይ

ሙሉ እምነቴ ነው።

14እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤

አይዞህ፣ በርታ፤

እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 27:1-14

第 27 篇

讚美的禱告

大衛的詩。

1耶和華是我的光,我的拯救,

我還怕誰?

耶和華是我的堡壘,

我還怕誰?

2當惡人來吞吃我,

仇敵來攻擊我時,

必失足跌倒。

3雖然大軍圍攻我,

我心中卻一無所懼;

雖然戰爭來臨,我仍滿懷信心。

4我曾向耶和華求一件事,

我還要求,就是能一生住在祂的殿中,

瞻仰祂的榮美,尋求祂的旨意。

5危難之時,祂保護我,

把我藏在祂的聖幕裡,

高高地安置在磐石上。

6我要昂首面對四圍的敵人,

我要在祂的聖幕裡歡呼獻祭,

歌頌讚美祂。

7耶和華啊,求你垂聽我的呼求,

求你恩待我,應允我。

8你說:「來尋求我!」

我心中回應:

「耶和華啊,我要尋求你。」

9別掩面不理我,

別憤然拒絕你的僕人,

你一向是我的幫助。

拯救我的上帝啊,

別離開我,別撇棄我。

10縱使父母離棄我,

耶和華也必收留我。

11耶和華啊,

求你指教我行你的道,

引導我走正路,遠離仇敵。

12求你不要讓仇敵抓到我,

遂其所願,

因為他們誣告我,恐嚇我。

13我深信今世必能看見耶和華的美善。

14要等候耶和華,

要堅定不移地等候耶和華。