መዝሙር 150 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 150:1-6

መዝሙር 150

የምስጋና መዝሙር

1ሃሌ ሉያ።150፥1 አንዳንዶች ከ6 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤

በታላቅ ጠፈሩ አወድሱት።

2ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤

እጅግ ታላቅ ነውና ወድሱት።

3በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤

በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።

4በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤

በባለ አውታር መሣሪያና በእንቢልታ አወድሱት።

5ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤

ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል ወድሱት።

6እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።

ሃሌ ሉያ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 150:1-6

第 150 篇

讚美上帝

1你們要讚美耶和華!

在祂的聖殿讚美祂,

在彰顯祂能力的穹蒼讚美祂!

2你們要因祂大能的作為讚美祂,

讚美祂的無比偉大!

3要吹響號角讚美祂,

要彈琴鼓瑟讚美祂!

4要擊鼓跳舞讚美祂,

要撥弦吹笛讚美祂!

5要擊響鐃鈸讚美祂,

用響亮的鈸聲讚美祂!

6凡有生命的都要讚美耶和華!

你們要讚美耶和華!