መዝሙር 127 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 127:1-5

መዝሙር 127

በእግዚአብሔር መታመን

የሰሎሞን መዝሙረ መዓርግ።

1እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣

ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤

እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣

ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።

2የዕለት ጕርስ ለማግኘት በመጣር፣

ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣

አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤

እርሱ ለሚወድዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።127፥2 ወይም ተኝተው ሳሉ ምግብ ያዘጋጅላቸዋል።

3እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤

የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።

4በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣

በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።

5ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣

የተባረከ ሰው ነው፤

ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣

አይዋረዱም።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 127:1-5

第 127 篇

頌讚上帝的美善

所羅門上聖殿朝聖之詩。

1若不是耶和華建造房屋,

建造者的工作都是徒勞。

若不是耶和華保護城池,

守城者保持警覺也是徒然。

2你早起晚睡,

為生活操勞也是徒然,

唯有耶和華所愛的人才能安眠。

3兒女是耶和華所賜的禮物,

孩子是祂所給的賞賜。

4人年輕時生的兒女猶如戰士手中的箭。

5袋中裝滿了箭的人有福了!

他們在城門與仇敵爭論時,

必不致蒙羞。