መሳፍንት 20 – NASV & NUB

New Amharic Standard Version

መሳፍንት 20:1-48

እስራኤላውያን ከብንያማውያን ጋር ተዋጉ

1ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ። 2የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ሁሉ ቍጥራቸው አራት መቶ ሺሕ በሚሆን፣ ሰይፍ በሚመዙ እግረኞች ወታደሮች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ መካከል ተገኙ። 3በዚህ ጊዜ ብንያማውያን፣ እስራኤላውያን ወደ ምጽጳ መውጣታቸውን ሰሙ፤ ከዚያም እስራኤላውያን፣ “ይህ ክፉ ድርጊት እንዴት እንደ ተፈጸመ እስቲ ንገሩን?” ተባባሉ።

4ስለዚህ የተገደለችው ሴት ባል ሌዋዊ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔና ቁባቴ በዚያ ለማደር በብንያም ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ መጣን። 5የጊብዓም ሰዎች በሌሊት ሊገድሉኝ ያደርኩበትን ቤት ከበቡት፤ ከዚያም በቁባቴ ላይ ስለ አመነዘሩባት ሞተች። 6የቁባቴንም ሬሳ ከቈራረጥሁ በኋላ እያንዳንዱን ቍራጭ፣ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ወዳለበት አገር ሰደድሁ፤ ይህን ያደረግሁትም ሰዎቹ በእስራኤል ዘንድ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ስለ ፈጸሙ ነው። 7አሁንም እናንተ እስራኤላውያን ሁሉ በጕዳዩ ላይ ተወያዩበት፤ ፍርዳችሁንም ስጡ።”

8ከዚያም ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው በመነሣት እንዲህ አሉ፤ “ከእኛ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፤ ማንኛችንም ወደ ቤታችን አንመለስም። 9ነገር ግን በጊብዓ ላይ የምናደርገው ይህ ነው፤ በዕጣው መሠረት እንዘምትበታለን። 10ከመላው የእስራኤል ነገዶችም ለሰራዊቱ ስንቅ እንዲይዙ፣ ከመቶው ዐሥር፣ ከሺው አንድ መቶ፣ ከዐሥር ሺው ደግሞ አንድ ሺሕ ሰው እንወስዳለን። ከዚያም ሰራዊቱ በብንያም ወደምትገኘው ጊብዓ በሚደርስበት ጊዜ፣ ነዋሪዎቿ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት አስነዋሪ ድርጊት ተገቢውን ቅጣት ይሰጣቸዋል።” 11ስለዚህ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በመተባበር በከተማዪቱ ላይ ዘመቱባት።

12የእስራኤል ነገዶች ለመላው የብንያም ነገድ እንዲህ በማለት መልእክተኞች ላኩ፣ “በመካከላችሁ የተፈጸመው ይህ ክፉ ድርጊት ምንድን ነው? 13አሁንም እነርሱን ገድለን ይህን ክፉ ድርጊት ከእስራኤል እንድናስወግድ፣ እነዚያን የጊብዓን ወስላቶች አሳልፋችሁ ስጡን።”

ብንያማውያን ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን አልሰሟቸውም ነበር፤ 14ስለዚህ እስራኤላውያንን ለመውጋት ከየከተሞቻቸው በአንድነት ወደ ጊብዓ መጡ። 15ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፣ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺሕ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ። 16በእነዚህም ሁሉ መካከል እያንዳንዳቸው ድንጋይ ወንጭፈው ጠጕር እንኳ የማይስቱ ሰባት መቶ ምርጥ ግራኞች ነበሩ።

17እስራኤላውያን፣ ብንያማውያንን ሳይጨምር፣ ሰይፍ የታጠቁ አራት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች አሰባሰቡ።

18እስራኤላውያን ወደ ቤቴል20፥18 ወይም ወደ እግዚአብሔር ቤት፤ በቁ 26 ላይም እንደዚሁ ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፣ “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ።

እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።

19በማግስቱም ጧት እስራኤላውያን ተነሥተው በጊብዓ አጠገብ ሰፈሩ፤ 20የእስራኤል ሰዎች ብንያማውያንን ለመውጋት ሄዱ፤ በጊብዓ ለሚያደርጉትም ውጊያ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። 21ብንያማውያን ከጊብዓ ወጡ፤ በዚያችም ዕለት ከእስራኤላውያን ሃያ ሁለት ሺሕ ሰዎች ገደሉ። 22ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ተበረታትተው በመጀመሪያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደ ገና ቦታ ቦታቸውን ያዙ። 23እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመግጠም እንደ ገና እንውጣን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።

እግዚአብሔርም፣ “አዎን፤ ውጡና ግጠሟቸው” ብሎ መለሰላቸው።

24በሁለተኛው ቀን እስራኤላውያን ወደ ብንያማውያን ተጠጉ። 25በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፣ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደ ገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ሰዎች ገደሉ።

26የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እዚያም እያለቀሱ በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ በዚያን ቀን እስኪመሽ ድረስ ጾሙ፤ በእግዚአብሔር ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት20፥26 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል። አቀረቡ። 27እስራኤላውያንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቁ፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት እዚያው ነበር፤ 28የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፣ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደ ገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ።

እግዚአብሔርም፣ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።

29ከዚያም እስራኤላውያን በጊብዓ ዙሪያ ድብቅ ጦር አኖሩ። 30በሦስተኛውም ቀን ብንያማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ጊብዓን ለመውጋት ቦታ ቦታቸውን ያዙ። 31ብንያማውያንም ሊገጥሟቸው ወጡ፤ ከከተማዪቱም ርቀው እንዲሄዱ ተደረጉ፤ እንደ በፊቱም እስራኤላውያንን ይገድሉ ጀመር። ከዚህ የተነሣም በሜዳው እንዲሁም ወደ ቤቴልና ወደ ጊብዓ በሚወስደው መንገዶች ላይ ሠላሳ ያህል ሰዎች ወድቀው ነበር።

32ብንያማውያኑ፣ “እንደ በፊቱ ይኸው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፣ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፣ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማዪቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር።

33የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ከነበሩበት ቦታ አፈግፍገው በበኣልታማር ስፍራ ስፍራቸውን ያዙ። ሸምቆ ይጠባበቅ የነበረው የእስራኤል ጦር ደግሞ ካደፈጠበት ከጊብዓ በስተ ምዕራብ20፥33 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ቩልጌት ከዚህ ጋር ይስማማሉ ነገር ግን የዕብራይስጡ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ካለው ቦታ ወጣ። 34ከዚያም ከመላው እስራኤል የተውጣጣው ዐሥር ሺሕ ጦር በጊብዓ ላይ ፊት ለፊት አደጋ ጣለ። ውጊያው ከመበርታቱ የተነሣም፣ ብንያማውያን መጥፊያቸው እየቀረበ መምጣቱን ገና አላወቁም ነበር። 35እግዚአብሔር ብንያምን በእስራኤል ፊት መታው፤ በዚያችም ዕለት እስራኤላውያን በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ አምስት ሺሕ አንድ መቶ ብንያማውያንን ገደሉ። 36ከዚህ የተነሣ ብንያማውያን ድል መሆናቸውን ተረዱ።

በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ጊብዓ ላይ ባኖሩት ድብቅ ጦር ስለ ተማመኑ የተሸነፉ በመምሰል ለብንያማውያን ቦታ ለቀቁ። 37ከዚያም ሸምቀው የነበሩት ሰዎች በድንገት እየተወረወሩ ወደ ጊብዓ ገቡ፤ በየቦታው ተሠራጭተውም መላዪቱን ከተማ በሰይፍ መቱ። 38የእስራኤል ሰዎች ያሸመቀው ጦር በከተማዪቱ ውስጥ ከባድ የጢስ ደመና ምልክት እንዲያሳይ፣ 39እስራኤላውያንም ይህን ሲያዩ ወዲያውኑ እንዲያፈገፍጉ ተስማሙ።

ብንያማውያንን ማጥቃት እንደ ጀመሩ፣ ሠላሳ እስራኤላውያንን ስለ ገደሉ፣ “እንደ መጀመሪያው የጦርነት ጊዜ እያሸነፍናቸው ነው” አሉ። 40ነገር ግን የጢሱ ዐምድ ከከተማዪቱ መነሣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ዞረው የመላዪቱ ከተማ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ። 41ከዚያም እስራኤላውያን ዞረው አጠቋቸው፤ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ጥፋት እንደ ደረሰባቸው ስላወቁ እጅግ ደነገጡ። 42ስለዚህም ጀርባቸውን አዙረው ከእስራኤላውያን ፊት ወደ ምድረ በዳው ሸሹ፤ ሆኖም ከጦርነት ማምለጥ አልቻሉም፤ ከየከተሞቹ የወጡ እስራኤላውያንም በዚያው ገደሏቸው። 43ብንያማውያንንም ከበቧቸው፤ አሳደዷቸው፤ ከጊብዓ በስተ ምሥራቅ ትይዩ ባለውም ስፍራ በቀላሉ20፥43 የዕብራይስጡ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም። አሸነፏቸው፤ 44በጦርነቱም ላይ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ብንያማውያን ወደቁ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ። 45ብንያማውያን ጀርባቸውን አዙረው በምድረ በዳው በኩል ወደ ሬሞን ዐለት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እስራኤላውያን በመንገድ ላይ አምስት ሺሕ ሰው ገደሉባቸው፤ እስከ ጊድአምም ድረስ ተከታትለው ሁለት ሺሕ ሰዎች በተጨማሪ ገደሉ።

46በዚያች ዕለት ሰይፍ የታጠቁ ሃያ አምስት ሺሕ ብንያማውያን በጦር ሜዳ ወደቁ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ። 47ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ጀርባቸውን አዙረው በምድረ በዳው ውስጥ ወዳለው ወደ ሬሞን ዐለት ሸሹ፤ በዚያም አራት ወር ተቀመጡ። 48ከዚያም እስራኤላውያን ወደ ብንያም ምድር ተመልሰው ከተሞቻቸውን በሙሉ እንዲሁም እንስሳቱንና በዚያ ያገኙትን ሁሉ በሰይፍ መቱ፤ በመንገዳቸው ያገኙትን ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።

Swedish Contemporary Bible

Domarboken 20:1-48

Israel anfaller Benjamins stam

1Israeliterna drog då ut allesammans, från Dan till Beer Sheva, och samlades inför Herren i Mispa. 2Hela folkets, alla Israels stammars, ledare trädde fram inför Guds folk, 400 000 väpnade män till fots. 3Ryktet om mobiliseringen av de israelitiska trupperna i Mispa nådde snart Benjamin. Israeliterna sa: ”Berätta hur detta illdåd gick till!”

4”Jag kom med min bihustru till Giva i Benjamin för att stanna där över natten”, sa leviten, den mördade kvinnans man. 5”Samma kväll kom män från staden och omringade huset. Mig tänkte de döda och min bihustru kränkte de så att hon dog. 6Då styckade jag hennes döda kropp och sände ut delarna över hela landet, för dessa män hade begått en avskyvärd och skamlig gärning i Israel. 7Nu, israeliter, ni som är samlade här, nu vill jag höra er dom!”

8De svarade alla som en man: ”Ingen av oss tänker gå tillbaka eller vända om hem. 9Vi anfaller Giva så som lotten avgör. 10I alla Israels stammar tar vi ut tio man av hundra, hundra av tusen och tusen av tiotusen. De ska förse oss med proviant. Resten ska förinta Giva som straff för deras skamliga gärning de begått i Israel.”

11Hela nationen förenades i förbund med varandra mot staden.

12Israels stammar skickade budbärare till hela Benjamins stam och ställde krav: ”Ni är skyldiga till ett oerhört brott! 13Utlämna dessa onda män från Giva, så att vi kan avrätta dem och rena Israel från all ondska.” Men folket i Benjamin ville inte höra på sina israelitiska bröder. 14I stället samlades de från sina städer till Giva för att strida mot israeliterna. 15Benjaminiterna mönstrade 26 000 väpnade män, förutom de 700 utvalda som bodde där. 16Bland dessa fanns det 700 vänsterhänta som kunde träffa ett hårstrå med sina slungstenar utan att missa. 17Det övriga Israel, utom Benjamins stam, mönstrade 400 000 krigsmän beväpnade med svärd.

18Före striden drog de israelitiska trupperna upp till Betel för att rådfråga Gud. ”Vilken stam ska anföra oss i striden mot Benjamins folk?” frågade de. ”Juda ska gå först”, svarade Herren.

19Tidigt nästa morgon bröt israeliterna upp och slog läger utanför Giva. 20De drog ut till strid mot Benjamins män och ställde upp sig mot dem utanför Giva. 21Men benjaminiterna rusade ut och dödade under den dagen 22 000 israeliter.

22Den israelitiska hären fattade nytt mod och ställde upp sig på samma ställe som första dagen, 23efter att ha gått upp och klagat inför Herren ända till kvällen och rådfrågat honom: ”Ska vi fortsätta att strida mot vår bror Benjamin?” ”Ja!” svarade då Herren. 24Alltså drog israeliterna ut nästa dag mot benjaminiterna 25och även den dagen ryckte benjaminiterna ut, så att de förlorade ytterligare 18 000 man, allesammans beväpnade med svärd.

26Då drog alla israeliterna, hela armén, upp till Betel och grät inför Herren och fastade till kvällen och offrade brännoffer och gemenskapsoffer åt Herren. 27De rådfrågade Herren. Guds förbundsark fanns där på den tiden 28och Pinechas, Elasars son och Arons sonson, gjorde tjänst inför Herren. De frågade: ”Ska vi gå ut igen och strida mot vår bror Benjamin eller inte?” Herren svarade: ”Ja, gör det! Jag ska ge honom i ditt våld i morgon.”

29Då lade sig Israels soldater i bakhåll runt Giva 30och gick sedan på den tredje dagen ut mot benjaminiterna och gjorde sig i ordning för strid utanför Giva så som de gjort tidigare. 31Benjamins trupper kom ut ur staden och lurades bort från staden. Då började Benjamin precis som tidigare att angripa fiender utmed vägarna över fälten till Betel och till Giva och lyckades döda ett trettiotal israeliter.

32Då ropade man i Benjamins armé: ”Vi besegrar dem igen!” Men de israelitiska soldaterna hade i förväg gjort upp att de skulle dra sig tillbaka och locka dem bort från staden ut till vägarna. 33Alla israeliterna drog sig tillbaka och ställde upp sig i Baal Tamar och de som fanns i bakhåll strömmade fram från sina ställen väster om Giva. 34De 10 000 israelitiska elitsoldaterna gick till anfall mot Giva och Benjamin förstod inte hur stor faran för nederlag i själva verket var.

35Herren lät Israel besegra Benjamin och Israels armé dödade 25 100 man i Benjamin den dagen, alla beväpnade män.

36Nu insåg benjaminiterna sitt nederlag. Israels män drog sig alltså tillbaka från Benjamin, för de litade på sitt bakhåll vid Giva. 37De som låg i bakhåll rusade in i staden och dödade alla som fanns där med svärd. 38Israeliterna hade kommit överens med dem som låg i bakhåll att de skulle sända ett stort rökmoln från staden. 39Israeliterna gjorde helt om i striden och då slog benjaminiterna ihjäl ett trettiotal av dem och sa: ”Vi har slagit dem precis som förra gången.” 40Men rökmolnet steg från staden och när benjaminiterna vände sig om, såg de att staden stod i lågor. 41Israeliterna vände nu helt om och benjaminiterna greps av skräck, eftersom de insåg att olyckan var över dem. 42De flydde ut i öknen för israeliterna, men de kunde inte undgå striden, för männen som varit i staden kom och slog ner dem. 43De omringade och krossade benjaminiterna och förföljde dem utan uppehåll till en plats öster om Giva. 44I Benjamins armé dog 18 000 tappra krigare i striden. 45När de vände och flydde ut i öknen bort mot Rimmons klippa, dödades 5 000 utmed vägen och de förföljde benjaminiterna och dödade ytterligare 2 000 närmare Gidom.

46Benjamins stam förlorade den dagen 25 000 tappra krigare som varit beväpnade med svärd. 47De 600 som fanns kvar, flydde alltså till öknen till Rimmons klippa där de stannade i fyra månader. 48Men Israels armé återvände och dödade allt och alla, även boskapen, som tillhörde Benjamin och brände ner varje stad i hela området.