መሳፍንት 18 – NASV & PCB

New Amharic Standard Version

መሳፍንት 18:1-31

ዳናውያን ሰዎች በላይሽ ሰፈሩ

1በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ የዳን ነገድም በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስተ ድርሻውን ገና ስላልወሰደ፣ የሚሰፍርበትን የራሱን ርስት ይፈልግ ነበር። 2ስለዚህ ዳናውያን ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ አምስት ኀያላን ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ወደዚያ ላኩ፤ እነዚህም ነገዶቻቸውን ሁሉ የሚወክሉ ነበሩ። የላኳቸውም ሰዎች፣ “ሂዱ፤ ምድሪቱን ሰልሉ” አሏቸው።

መልእክተኞቹም ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር ገቡ፤ ወደሚያድሩበትም ወደ ሚካ ቤት መጡ። 3በሚካ ቤት አጠገብ እንደ ደረሱም የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ ዐወቁ፤ ስለዚህ ወደዚያ ጐራ ብለው፣ “ወደዚህ ያመጣህ ማን ነው? እዚህ ምን ትሠራለህ? የመጣኸውስ ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።

4እርሱም፣ “ሚካ ይህን አደረገልኝ፤ ቀጠረኝ፤ ካህኑም ሆንሁ” አላቸው።

5እነርሱም፣ “መንገዳችን መቃናት አለመቃናቱን እንድናውቅ እባክህ እግዚአብሔርን ጠይቅልን” አሉት።

6ካህኑም፣ “በሰላም ሂዱ፤ መንገዳችሁን እግዚአብሔር አቃንቶላችኋል” ብሎ መለሰላቸው።

7ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ሥጋት በጸጥታ18፥7 በዕብራይስጡ የዚህ ሐረግ ትርጉም በትክክል አይታወቅም። እንደሚኖሩ ሁሉ፣ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለመኖሩ ሕዝቡ ባለጠጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር18፥7 በዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ሲስማማ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን ከአራም ስዎች ጋር ይላል። ግንኙነት አልነበረውም።

8ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል እንደ ተመለሱ ወገኖቻቸው፣ “የሄዳችሁበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው።

9መልእክተኞቹም እንዲህ አሏቸው፤ “ምድሪቱ እጅግ መልካም መሆኗን አይተናል፤ እንግዲህ ተነሡ! ሄደን እንዋጋቸው፤ ተነሡ እንጂ ዝም ትላላችሁን? ወደዚያው ሄዳችሁ ምድሪቱን ለመያዝ አታመንቱ፤ 10እዚያ ስትደርሱም ያለ ሥጋት የሚኖር ሕዝብ፣ እግዚአብሔር በእጃችሁ የሚሰጣችሁን አንዳች ነገር ያልጐደላትን ሰፊ ምድር ታገኛላችሁ።”

11ከዚያ በኋላም ከዳን ወገን ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሡ። 12ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚሁ የተነሣ ነው። 13ከዚያም ተጕዘው ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር በመሄድ ወደ ሚካ ቤት መጡ።

14የላይሽን ምድር ሰልለው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ለወንድሞቻቸው፣ “ከእነዚሁ ቤቶች በአንዱ ኤፉድ፣ ተራፊም፣ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ዕወቁበት” አሏቸው። 15ስለዚህ ወጣቱ ሌዋዊ ወደሚኖርበት ወደ ሚካ ቤት ጐራ ብለው ሰላምታ አቀረቡለት። 16ለጦርነት ተዘጋጅተው የመጡት ስድስት መቶ የዳን ሰዎች በቅጥሩ በር መግቢያ ላይ ቆመው ነበር። 17ካህኑ ለጦርነት ከተዘጋጁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጥሩ በር ላይ ቆሞ ሳለ፣ ምድሪቱን ለመሰለል መጥተው የነበሩትን አምስት ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ በመግባት የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ።

18እነዚህ ሰዎች ወደ ሚካ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል በሚወስዱበት ጊዜ ካህኑ፣ “ምን ማድረጋችሁ ነው?” አላቸው።

19እነርሱም፣ “ዝም በል! አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋር ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተ ሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት። 20ይህም ካህኑን ደስ አሰኘው፤ እርሱም ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና የተቀረጸውን ምስል ይዞ ከሕዝቡ ጋር ሄደ። 21እነርሱም ሕፃናታቸውን፣ የከብቶቻቸውን መንጋና ሀብታቸውን ሁሉ ወደ ፊት በማስቀደም ተመልሰው ሄዱ።

22ከሚካ ቤት ጥቂት ራቅ እንዳሉም፣ የሚካ ጎረቤቶች ለርዳታ ተጠርተው ተሰበሰቡ፤ የዳን ሰዎችንም ተከታትለው ደረሱባቸው። 23ከበሰተ ኋላቸው ሆነው ሲጮኹባቸውም፣ የዳን ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ሚካን፣ “ሰዎችህን ለውጊያ አሰባስበህ መምጣትህ ምን ሆንህና ነው?” አሉት።

24እርሱም፣ “እንዴት፣ ‘ምን ሆንህ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።

25የዳን ሰዎች፣ “አትሟገተን፤ ያለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጕዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተ ሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት። 26የዳን ሰዎች ይህን ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም የማይችላቸው መሆኑን በማየት ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።

27ከዚያም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወስደው ወደ ላይሽ በመሄድ፣ በሰላምና ያለ ሥጋት ይኖር የነበረውን ሕዝብ በሰይፍ መቱት፤ ከተማዪቱንም በእሳት አቃጠሏት። 28የሚኖሩት ከሲዶና በጣም ርቀው ስለ ነበርና ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸው የሚታደጋቸው አንድም አልነበረም፤ ከተማዪቱም የምትገኘው በቤትሮዓብ አጠገብ ነበረ።

የዳንም ሰዎች ከተማዪቱን እንደ ገና ሠርተው መኖሪያቸው አደረጓት። 29ከተማዪቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት፤ ቀድሞ ግን ስሟ ላይሽ ይባል ነበር። 30እዚያም የዳን ሰዎች ለራሳቸው ጣዖታት አቆሙ፤ የሙሴ ልጅ፣18፥30 ጥንታዊው የዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት፣ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም እንዲሁም የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን ምናሴ ይላል። የጌርሳም ልጅ ዮናታንና የእርሱም ልጆች ምድሪቱ እስከ ተማረከችበት ጊዜ ድረስ ለዳን ነገድ ካህናት ሆኗቸው፤ 31ስለዚህም ሚካ የሠራቸውን ጣዖታት፣ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ባለማቋረጥ አመለኳቸው።

Persian Contemporary Bible

داوران 18:1-31

ميخا و قبيلهٔ دان

1در آن زمان بنی‌اسرائيل پادشاهی نداشت. قبيلهٔ دان سعی می‌كردند مكانی برای سكونت خود پيدا كنند، زيرا سكنهٔ سرزمينی را كه برای آنها تعيين شده بود هنوز بيرون نرانده بودند. 2پس افراد قبيلهٔ دان پنج نفر از جنگاوران خود را از شهرهای صرعه و اِشتائُل فرستادند تا موقعيت سرزمينی را كه قرار بود در آن ساكن شوند، بررسی نمايند. آنها وقتی به كوهستان افرايم رسيدند به خانهٔ ميخا رفتند و شب را در آنجا گذراندند. 3در آنجا صدای آن لاوی جوان را شنيدند و او را شناختند. پس به طرف او رفته، از وی پرسيدند: «در اينجا چه می‌كنی؟ چه كسی تو را به اينجا آورده است؟»

4لاوی جوان گفت: «ميخا مرا استخدام كرده تا كاهن او باشم.»

5آنها گفتند: «حال كه چنين است، از خدا سؤال كن و ببين آيا در اين مأموريت، ما موفق خواهيم شد يا نه.» 6كاهن پاسخ داد: «البته موفق خواهيد شد، زيرا كاری كه شما می‌كنيد منظور نظر خداوند است.»

7پس آن پنج مرد روانه شده، به شهر لايش رفتند و ديدند كه مردم آنجا مثل صیدونی‌ها در صلح و آرامش و امنيت به سر می‌برند، زيرا در اطرافشان قبيله‌ای نيست كه بتواند به ايشان آزاری برساند. آنها از بستگان خود در صيدون نيز دور بودند و با آبادی‌های اطراف خود رفت و آمدی نداشتند.

8وقتی آن پنج جنگاور به صرعه و اِشتائُل نزد قبيلهٔ خود بازگشتند، مردم از آنها پرسيدند: «وضع آن ديار چگونه است؟»

9‏-10آنها گفتند: «سرزمينی است حاصلخيز و وسيع كه نظير آن در دنيا پيدا نمی‌شود؛ مردمانش حتی آمادگی آن را ندارند كه از خودشان دفاع كنند! پس منتظر چه هستيد، برخيزيد تا به آنجا حمله كنيم و آن را به تصرف خود درآوريم زيرا خدا آن سرزمين را به ما داده است.»

11با شنيدن اين خبر، از قبيلهٔ دان ششصد مرد مسلح از شهرهای صرعه و اِشتائُل به سوی آن محل حركت كردند. 12آنها ابتدا در غرب قريهٔ يعاريم كه در يهودا است اردو زدند (آن مكان تا به امروز هم «اردوگاه دان» ناميده می‌شود)، 13سپس از آنجا به كوهستان افرايم رفتند. هنگامی كه از كنار خانهٔ ميخا می‌گذشتند، 14آن پنج جنگاور به همراهان خود گفتند: «خانه‌ای در اينجاست كه در آن ايفود18‏:14 نگاه کنيد به 17‏:4و5.‏ و تعداد زيادی بت وجود دارد. خودتان می‌دانيد چه بايد بكنيم!»

15‏-16آن پنج نفر به خانهٔ ميخا رفتند و بقيهٔ مردان مسلح در بيرون خانه ايستادند. آنها با كاهن جوان سرگرم صحبت شدند. 17سپس در حالی که كاهن جوان بيرون در با مردان مسلح ايستاده بود آن پنج نفر وارد خانه شده ايفود و بتها را برداشتند.

18كاهن جوان وقتی ديد كه بتخانه را غارت می‌كنند، فرياد زد: «چه می‌كنيد؟»

19آنها گفتند: «ساكت شو و همراه ما بيا و كاهن ما باش. آيا بهتر نيست به جای اينكه در يک خانه كاهن باشی، كاهن يک قبيله در اسرائيل بشوی؟» 20كاهن جوان با شادی پذيرفت و ايفود و بتها را برداشته، همراه آنها رفت.

21سپاهيان قبيلهٔ دان دوباره رهسپار شده، بچه‌ها و حيوانات و اثاثيه خود را در صف اول قرار دادند. 22پس از آنكه مسافت زيادی از خانهٔ ميخا دور شده بودند، ميخا و تنی چند از مردان همسايه‌اش آنها را تعقيب كردند. 23آنها مردان قبيلهٔ دان را صدا می‌زدند كه بايستند.

مردان قبيلهٔ دان گفتند: «چرا ما را تعقيب می‌كنيد؟»

24ميخا گفت: «كاهن و همهٔ خدايان مرا برده‌ايد و چيزی برايم باقی نگذاشته‌ايد و می‌پرسيد چرا شما را تعقيب می‌كنم!»

25مردان قبيلهٔ دان گفتند: «ساكت باشيد و گرنه ممكن است افراد ما عصبانی شده، همهٔ شما را بكشند.» 26پس مردان قبيلهٔ دان به راه خود ادامه دادند. ميخا چون ديد تعداد ايشان زياد است و نمی‌تواند حريف آنها بشود، به خانهٔ خود بازگشت.

27مردان قبيلهٔ دان، با كاهن و بتهای ميخا به شهر آرام و بی‌دفاع لايش رسيدند. آنها وارد شهر شده، تمام ساكنان آن را كشتند و خود شهر را به آتش كشيدند. 28هيچكس نبود كه به داد مردم آنجا برسد، زيرا از صيدون بسيار دور بودند و با همسايگان خود نيز روابطی نداشتند كه در موقع جنگ به ايشان كمک كنند. شهر لايش در وادی نزديک بيت‌رحوب واقع بود.

مردم قبيلهٔ دان دوباره شهر را بنا كرده، در آن ساكن شدند. 29آنها نام جد خود دان، پسر يعقوب را بر آن شهر نهادند. 30ايشان بتها را در جای مخصوصی قرار داده، يهوناتان (پسر جرشوم و نوهٔ موسی) و پسرانش را به عنوان كاهنان خود تعيين نمودند. خانوادهٔ يهوناتان تا زمانی كه مردم به اسارت برده شدند، خدمت كاهنی آنجا را به عهده داشتند. 31در تمام مدتی كه عبادتگاه مقدس در شيلوه قرار داشت، قبيلهٔ دان همچنان بتهای ميخا را می‌پرستيدند.