ሕዝቅኤል 46 – NASV & NUB

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 46:1-24

1“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ለምሥራቅ ትይዩ የሆነው የውስጠኛው አደባባይ በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በወር መባቻ ቀን ይከፈት። 2ገዥው ከውጭ በኩል በመግቢያው መተላለፊያ በረንዳ በመግባት በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፤ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት46፥2 በትውፊት የድነት መሥዋዕት ይባላል፤ እንዲሁም በ17 ያቅርቡለት፤ በበሩ መግቢያ ደፍ ላይ ሆኖ ይስገድ፤ ከዚያም ይውጣ፤ በሩ ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋ። 3የምድሪቱም ሕዝብ በሰንበታትና በወር መባቻ በዓላት በእግዚአብሔር ፊት በበሩ መግቢያ ላይ ይስገዱ። 4ገዥው በሰንበት ቀን በእግዚአብሔር ፊት የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ስድስት የበግ ጠቦትና አንድ አውራ በግ ነው፤ ሁሉም እንከን የሌላቸው ይሁኑ። 5ከአውራ በጉ ጋር የሚቀርበው የእህል ቍርባን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የሚቀርበውም የእህል ቍርባን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው። 6በወር መባቻ በዓል አንድ ወይፈን፣ ስድስት የበግ ጠቦትና አንድ አውራ በግ ያቅርብ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ። 7ከወይፈኑ ጋር አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራው በግም ጋር አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የሚቀርበው የእህል ቍርባን ደግሞ ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው። 8ገዥው ሲገባ፣ በመግቢያው በር መተላለፊያ በረንዳ ይግባ፤ ሲወጣም በዚያው ይውጣ።

9“ ‘በተወሰኑት በዓላት የምድሪቱ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት በሚቀርብበት ጊዜ፣ ይሰግድ ዘንድ በሰሜን በር የገባ ሁሉ በደቡብ በር ይውጣ፤ በደቡብ በር የገባም በሰሜኑ በር ይውጣ፤ በፊት ለፊቱ ባለው በር ይመለስ እንጂ ማንም በገባበት በር አይውጣ። 10ገዥው በመካከላቸው በመሆን፣ ሲገቡ ይገባል፤ ሲወጡም ይወጣል።

11“ ‘በበዓላትና በተወሰኑት በዓላት፣ ከወይፈኑ ጋር አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራ በጉም ጋር አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የሚያቀርበው የእህል ቍርባን ግን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው። 12ገዥው በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ በምሥራቅ ትይዩ የሆነው በር ይከፈትለት፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕቱንም ሆነ የኅብረት መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይወጣል፤ በሩም ይዘጋል።

13“ ‘በየቀኑ እንከን የሌለበትን የአንድ ዓመት ጠቦት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ይህንም በየማለዳው ታቀርበዋለህ። 14ከዚህም ጋር አንድ ስድስተኛ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት መለወሻም የሚሆን የኢን መስፈሪያ ሢሶ ዘይት አድርገህ በየማለዳው የእህል ቍርባን አቅርብ፤ ይህን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ማቅረብም የዘላለም ሥርዐት ነው። 15ስለዚህ ዘወትር ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በየማለዳው የበግ ጠቦት፣ የእህል ቍርባንና ዘይት ይቅረብ።

16“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ገዥው ከርስቱ ላይ ከወንድ ልጆቹ ለአንዱ ስጦታ ቢያደርግ፣ ያ ስጦታ ለዘሩ የሚተላለፍ ነው፤ በውርስም ንብረታቸው ይሆናል። 17ይሁን እንጂ ገዥው ከርስቱ ላይ ከባሪያዎቹ ለአንዱ ቢሰጥ፣ ባሪያው ነጻ እስከሚወጣበት ዓመት ድረስ የራሱ ሊያደርገው ይችላል፤ ከዚያም ርስቱ ለገዥው ይመለስለታል፤ ርስቱም ለወንድ ልጆቹ ብቻ የሚተላለፍ ይሆናል፤ የእነርሱም ነው። 18ገዥው ከንብረታቸው በማፈናቀል፤ የትኛውንም የሕዝቡን ርስት መውሰድ አይገባውም፤ ለወንድ ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ንብረት ነው፤ ይኸውም ከሕዝቤ ማንም ከርስቱ እንዳይነቀል ነው።’ ”

19ከዚያም ያ ሰው በበሩ አጠገብ ባለው መግቢያ አድርጎ፣ ለሰሜን ትይዩ ወደሆኑት ወደ ካህናቱ የተቀደሱ ክፍሎች አመጣኝ፤ በምዕራቡም መዳረሻ ያለውን ቦታ አሳየኝ። 20እርሱም፣ “ይህ ስፍራ ሕዝቡን ለመቀደስ መሥዋዕቱን ወደ ውጩ አደባባይ እንዳያወጡ፣ ካህናቱ የበደሉን መሥዋዕትና የኀጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፣ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ቦታ ነው” አለኝ።

21ከዚያም ወደ ውጩ አደባባይ አመጣኝ፤ በአራቱም ማእዘን ዙሪያ መራኝ፤ በእያንዳንዱም ማእዘን ሌላ አደባባይ አየሁ። 22በውጩ አደባባይ ባለው በአራቱ ማእዘን የታጠሩ46፥22 በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። አደባባዮች አሉ፤ ርዝመታቸው አርባ ክንድ፣ ወርዳቸውም ሠላሳ ክንድ ነበር፤ በአራቱም ማእዘን ያሉት አደባባዮች እኩል ናቸው። 23ከሥሩ ዙሪያውን ምድጃ የነበረበት፣ በአራቱም አደባባዮች ውስጥ ዙሪያ የድንጋይ ዕርከን ነበር። 24እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ፣ በቤተ መቅደሱ የሚያገለግሉቱ፣ የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ስፍራዎች ናቸው።”

Swedish Contemporary Bible

Hesekiel 46:1-24

Särskilda offer i templet

1Så säger Herren, Herren: Den inre förgårdens östra port ska vara stängd under de sex arbetsdagarna men öppen på sabbaten och nymånadsfesten. 2Fursten ska komma in utifrån genom portens förhus och ställa sig vid dörrposten. Prästerna ska offra hans brännoffer och gemenskapsoffer. Han ska tillbe vid portens tröskel och sedan gå ut. Porten får inte stängas förrän på kvällen. 3Folket i landet ska tillbe Herren vid ingången till denna port på sabbaterna och nymånadsfesterna.

4Det brännoffer som fursten bär fram till Herren på sabbatsdagen ska bestå av sex felfria lamm och en felfri bagge. 5Matoffret som han bär fram ska vara en efa mjöl för baggen och ett mått som han själv bestämmer för lammen, samt en hin olja för varje efa.46:5-7,11,14 För måtten se not till 45:10-14 och 45:24.

6På nymånadsfesten ska han offra en felfri ungtjur, sex lamm och en bagge, alla felfria. 7Som matoffer ska han offra en efa för tjuren, en efa för baggen och för lammen vad han själv bestämmer, samt en hin olja för varje efa.

8När fursten kommer ska han gå in genom portens förhus och ut igen samma väg. 9Men när folket i landet kommer inför Herren vid högtiderna, ska den som har gått in genom norra porten för att tillbe gå ut genom södra porten. Den som har gått in genom södra porten ska gå ut genom den norra. Ingen får gå tillbaka ut genom samma port som han kom in, utan man måste alltid gå ut genom den motsatta porten. 10Fursten ska vara med dem, komma in med dem och gå ut med dem.

11Vid högtider och fester ska matoffret vara en efa mjöl för tjuren, en efa för baggen och så mycket för lammen som han själv bestämmer, samt en hin olja för varje efa. 12När fursten vill bära fram ett frivilligt offer till Herren, ett brännoffer eller ett gemenskapsoffer, ska den östra porten öppnas för honom, så att han kan bära fram sitt brännoffer och gemenskapsoffer precis som på sabbaten. Sedan ska han gå ut igen, och porten ska stängas efter honom.

13Du ska dagligen ge ett årsgammalt felfritt lamm som brännoffer till Herren. Varje morgon ska du offra ett sådant. 14Du ska också som matoffer varje morgon ge en sjättedels efa mjöl och en tredjedels hin olja att fukta mjölet med. Denna förordning för Herrens matoffer ska gälla som en bestående stadga för alltid. 15Lammet, matoffret och oljan ska bäras fram varje morgon som ett regelbundet brännoffer.

16Så säger Herren, Herren: Om fursten ger någon av sina söner en del av sin egendom som gåva, ska den tillhöra hans söner. Det ska vara deras egendom som de ärvt. 17Men om han ger en del av sin egendom som gåva till någon av sina tjänare, får denne behålla den fram till friåret. Då återgår den till fursten. Det är bara hans söner som får behålla hans egendom. 18Fursten får inte heller ta något av folkets arvedel eller tvinga bort dem från deras egendom. Han ska ge sina söner av sin egendom, för att ingen bland mitt folk ska behöva skiljas från sin egendom.’ ”

19Sedan förde han mig genom ingången vid sidan om porten till prästernas heliga rum som låg mot norr. Längst bort vid västra ändan syntes en plats. 20Han sa till mig: ”Det här är platsen där prästerna kokar skuldoffret och syndoffret och bakar matoffret, för att slippa bära dem till den yttre förgården och därmed helga folket.”

21Därefter förde han mig ut till den yttre förgården och runt till dess fyra hörn. I varje hörn syntes en gård. 22I den yttre förgårdens fyra hörn fanns det slutna gårdar, 20 meter långa och 15 meter breda, alla gårdarna i de fyra hörnen var lika stora. 23Utmed insidan av de fyra gårdarna fanns på alla sidor en mur, och nertill i muren runt omkring hade man byggt eldstäder för kokning. 24Han sa till mig: ”I dessa kök kokar tempeltjänarna folkets slaktoffer.”