ሕዝቅኤል 25 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 25:1-17

በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ አሞናውያን አድርገህ፣ ትንቢት ተናገርባቸው፤ 3እንዲህም በላቸው፤ ‘የጌታ፣ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፣ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፣ የይሁዳም ቤት ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ፣ “ዕሠይ” ብላችኋልና፣ 4ለምሥራቅ ሕዝብ ትገዙ ዘንድ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ እነርሱም በመካከላችሁ ይሰፍራሉ፤ ድንኳኖቻቸውንም በዚያ ይተክላሉ፤ ፍሬያችሁን ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ። 5የራባን ከተማ የግመሎች መሰማሪያ፣ አሞንንም የበጎች መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 6ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ በልባችሁ ክፋት ሁሉ፣ በእስራኤል ውድቀት ላይ በመደሰት በእጃችሁ አጨብጭባችኋልና፤ በመዝለልም ጨፍራችኋልና 7ክንዴን በእናንተ ላይ አነሣለሁ፤ በአሕዛብ እንድትበዘበዙ አደርጋለሁ፤ ከሕዝቦች መካከል አውጥቼ፣ ከአገሮችም ለይቼ አጠፋችኋለሁ፤ እደመስሳችኋለሁም። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”

በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት

8“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሞዓብና ሴይር፣ “እነሆ የይሁዳ ቤት እንደ ሌሎቹ አሕዛብ ሁሉ ሆነ” ብለዋልና፤ 9በምድሪቱ ድንበር ላይ ካሉትና ክብሯ ከሆኑት ከተሞች ከቤት የሺሞት፣ ከበአልሜዎንና ከቂርያታይም ጀምሬ የሞዓብን ዐምባ እገልጣለሁ። 10ሞዓባውያንንም ከአሞናውያን ጋር ይገዙላቸው ዘንድ፣ ለምሥራቅ ሕዝብ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አሞናውያን በአሕዛብ ዘንድ ከእንግዲህ መታሰቢያ አይኖራቸውም። 11ሞዓብንም እቀጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት

12“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ኤዶም የይሁዳን ቤት ተበቅሏልና፤ በዚህም በደለኛ ሆኗልና፤ 13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ክንዴን በኤዶም ላይ አነሣለሁ፤ ሰዎቹንና እንስሶቻቸውን እገድላለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማንም ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ። 14በሕዝቤ በእስራኤል አማካይነት ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እነርሱም እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ሕዝብ ላይ ያደርጋሉ፤ ኤዶማውያንም በቀሌን ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

በፍልስጥኤም ላይ የተነገረ ትንቢት

15“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ፍልስጥኤማውያን በቂም ተነሣሥተው በክፉ ልብ ተበቅለዋልና፣ ይሁዳንም በቈየ ጠላትነት ለማጥፋት ፈልገዋልና፤ 16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ክንዴን በፍልስጥኤማውያን ላይ አነሣለሁ፤ ከሊታውያንንም እቈርጣለሁ፤ በባሕሩ ጠረፍ ላይ የቀሩትንም አጠፋለሁ። 17በታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በመዓቴም እቀጣቸዋለሁ፤” በምበቀላቸውም ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

New International Reader’s Version

Ezekiel 25:1-17

A Prophecy Against Ammon

1A message from the Lord came to me. The Lord said, 2“Son of man, turn your attention to the Ammonites. Prophesy against them. 3Tell them, ‘Listen to the message of the Lord and King. He says, “You laughed when my temple was made ‘unclean.’ You also laughed when the land of Israel was completely destroyed. You mocked the people of Judah when they were taken away as prisoners. 4So I am going to hand you over to the people of the east. They will set up their tents in your land. They will camp among you. They will eat your fruit. They will drink your milk. 5I will turn the city of Rabbah into grasslands for camels. Ammon will become a resting place for sheep. Then you will know that I am the Lord.” ’ ” 6The Lord and King says, “You clapped your hands. You stamped your feet. Deep down inside, you hated the land of Israel. You were glad because of what happened to it. 7So I will reach out my powerful hand against you. I will give you and everything you have to the nations. I will bring you to an end among the nations. I will destroy you. Then you will know that I am the Lord.”

A Prophecy Against Moab

8The Lord and King says, “Moab and Edom said, ‘Look! Judah has become like all the other nations.’ 9So I will let Moab’s enemies attack its lower hills. They will begin at the border towns. Those towns include Beth Jeshimoth, Baal Meon and Kiriathaim. They are the glory of that land. 10I will hand Moab over to the people of the east. I will also give the Ammonites to them. And the Ammonites will no longer be remembered among the nations. 11I will punish Moab. Then they will know that I am the Lord.”

A Prophecy Against Edom

12The Lord and King says, “Edom got even with Judah. That made Edom very guilty.” 13The Lord continues, “I will reach out my hand against Edom. I will kill its people and their animals. I will completely destroy it. They will be killed by swords from Teman all the way to Dedan. 14I will use my people Israel to pay Edom back. They will punish Edom because my anger against it is great. They will know how I pay back my enemies,” announces the Lord and King.

A Prophecy Against the Philistines

15The Lord and King says, “Deep down inside them, the Philistines hated Judah. So the Philistines tried to get even with them. They had been Judah’s enemies for many years. So they tried to destroy them.” 16The Lord continues, “I am about to reach out my hand against the Philistines. I will wipe out the Kerethites. I will destroy those who remain along the coast. 17You can be sure that I will pay them back. I will punish them because my anger against them is great. When I pay them back, they will know that I am the Lord.”