ሉቃስ 23 – NASV & HHH

New Amharic Standard Version

ሉቃስ 23:1-56

1በዚያ የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ ወሰዱት፤ 2እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክል፣ ደግሞም፣ ‘እኔ ክርስቶስ23፥2 ወይም መሲሕ፤ እንዲሁም 35 እና 39 ይመ ንጉሥ ነኝ’ ሲል አገኘነው።”

3ጲላጦስም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው።

ኢየሱስም፣ “አንተው አልህ” አለው።

4ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፣ “እኔ በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ።

5እነርሱ ግን፣ “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እዚህ ድረስ መላውን ይሁዳ ሳይቀር23፥5 ወይም በመላው የአይሁድ ምድር እያወከ ነው” እያሉ አጽንተው ተናገሩ።

6ጲላጦስም ይህን ሲሰማ፣ ሰውየው የገሊላ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቀ፤ 7ኢየሱስ ከሄድሮስ ግዛት የመጣ መሆኑን ጲላጦስ ባወቀ ጊዜ፣ ሄሮድስ በዚያን ወቅት በኢየሩሳሌም ስለ ነበረ ወደ እርሱ ላከው።

8ሄሮድስም ኢየሱስን ብዙ ጊዜ ሊያየው ይፈልግ ስለ ነበር፣ ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ታምራት ሲሠራ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር። 9ብዙ ጥያቄዎችንም አቀረበለት፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰለትም። 10የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም እዚያው ቆመው በብርቱ ይወነጅሉት ነበር። 11ሄሮድስም ከወታደሮቹ ጋር ናቀው፤ አፌዙበትም፤ የክብር ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። 12ሄሮድስና ጲላጦስም በዚሁ ዕለት ተወዳጁ፤ ቀደም ሲል ግን በመካከላቸው ጥል ነበረ።

13ጲላጦስም የካህናት አለቆችን፣ ገዥዎችንና ሕዝቡን በአንድነት ሰብስቦ፣ 14እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ሰው ሕዝቡን ለዐመፅ ያነሣሣል ብላችሁ ወደ እኔ አምጥታችሁት ነበር፤ እኔም በእናንተው ፊት መርምሬው፣ ባቀረባችሁበት ክስ አንዳች ወንጀል አላገኘሁበትም። 15ደግሞም ሄሮድስ እንዲሁ ምንም ስላላገኘበት ወደ እኛ መልሶታል፤ እንደምታዩት ይህ ሰው ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር አልፈጸመም፤ 16ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ።” 17ይህን ያለው በበዓሉ አንድ እስረኛ እንዲፈታላቸው የግድ ያስፈልግ ስለ ነበረ ነው።23፥17 አንዳንድ የጥንት ቅጆች ይህን ቍጥር አይጨምሩም።

18ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ላይ፣ “ይህን ሰው ወዲያ አስወግደው! በርባንን ፍታልን!” እያሉ ጮኹ፤ 19በርባንም በከተማ ውስጥ የሕዝብ ዐመፅ በማነሣሣትና በነፍስ ግድያ የታሰረ ሰው ነበር።

20ጲላጦስም ኢየሱስን ሊፈታው ስለ ፈለገ፣ እንደ ገና ተናገራቸው፤ 21እነርሱ ግን፣ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ይጮኹ ነበር።

22ጲላጦስም ሦስተኛ ጊዜ፣ “ለምን? ይህ ሰው ምን የፈጸመው ወንጀል አለ? እኔ ለሞት የሚያበቃ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ” አላቸው።

23እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እንዲሰቀል አጥብቀው ለመኑት፤ ጩኸታቸውም በረታ። 24ስለዚህ ጲላጦስ የጠየቁት እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላለፈ። 25የሕዝብ ዐመፅ በማነሣሣትና በነፍስ ግድያ ታስሮ የነበረውን፣ እንዲፈታላቸውም የለመኑትን ያን ሰው ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን እንዳሻቸው እንዲያደርጉት አሳልፎ ሰጣቸው።

የኢየሱስ መስቀል

23፥33-43 ተጓ ምብ – ማቴ 27፥33-44ማር 15፥22-32ዮሐ 19፥17-24

26ኢየሱስንም ይዘው ሲወስዱት፣ ስምዖን የተባለውን የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ አግኝተው መስቀሉን አሸክመው ኢየሱስን ተከትሎ እንዲሄድ አስገደዱት። 27ብዙ ሕዝብና ደረታቸውን እየደቁ የሚያለቅሱለት ሴቶችም ከኋላው ይከተሉት ነበር። 28ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አላቸው፤ “እናንት የኢየሩሳሌም ሴቶች፤ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ እንጂ ለእኔ አታልቅሱ፤ 29እነሆ፤ ‘መካኖችና ያልወለዱ ማሕፀኖች፣ ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው’ የምትሉበት ጊዜ ይመጣልና። 30በዚያን ጊዜም፣

“ ‘ተራሮችን፣ “ውደቁብን!”

ኰረብቶችንም፣ “ሰውሩን!” ’ ይላሉ።

31እንግዲህ በርጥብ ዕንጨት እንዲህ ካደረጉ፣ በደረቁ ምን ያደርጉ ይሆን?”

32ከእርሱ ጋር እንዲገደሉ ሌሎች ሁለት ወንጀለኞችን ወሰዷቸው። 33ቀራንዮ23፥33 በግሪክ ቋንቋ የራስ ቅል ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ይባላል። የተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ሰቀሉት፤ ወንጀለኞቹንም አንዱን በቀኙ፣ ሌላውን በግራው ሰቀሏቸው። 34ኢየሱስም፣ “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው”23፥34 አንዳንድ የጥንት ቅጆች፣ ይህ ዐረፍተ ነገር የላቸውም። አለ። እነርሱም ልብሱን በዕጣ ተከፋፈሉት።

35ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። ገዦችም፣ “ሌሎችን አዳነ፤ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ እርሱ ከሆነ፣ እስቲ ራሱን ያድን” እያሉ አፌዙበት።

36ወታደሮችም ቀርበው ያፌዙበት ነበር፤ የሖመጠጠ የወይን ጠጅ እየሰጡትም፣ 37“አንተ የአይሁድ ንጉሥ ከሆንህ፣ ራስህን አድን” ይሉት ነበር።

38ከራሱም በላይ፣ “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው” የሚል ጽሑፍ ነበር።

39ከተሰቀሉት ወንጀለኞችም አንዱ እየተሳደበ፣ “አንተ ክርስቶስ አይደለህምን? እስቲ፣ ራስህንም እኛንም አድን” ይለው ነበር።

40ሌላኛው ወንጀለኛ ግን እንዲህ ሲል ገሠጸው፤ “ተመሳሳይ ፍርድ እየተቀበልህ ሳለህ፣ ከቶ እግዚአብሔርን አትፈራምን? 41እኛ ላደረግነው ነገር ቅጣት እየተቀበልን ስለሆነ፣ ተገቢ ፍርድ ላይ ነን፤ ይህ ሰው ግን አንዳች ክፉ ነገር አላደረገም።”

42ደግሞም፣ “ኢየሱስ ሆይ፤ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ”23፥42 አንዳንድ ቅጆች በንጉሥነት ሥልጣንህ ስትመጣ ይላሉ። አለው።

43ኢየሱስም፣ “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” አለው።

የኢየሱስ መሞት

23፥44-49 ተጓ ምብ – ማቴ 27፥45-56ማር 15፥33-41

44ጊዜው ስድስት ሰዓት ያህል ነበር፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስም በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ፤ 45የፀሓይ ብርሃን ተከልክሏልና። የቤተ መቅደሱም መጋረጃ ተቀድዶ ለሁለት ተከፈለ። 46ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ፣ “አባት ሆይ፤ መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ” አለ፤ ይህንም ብሎ ሞተ።

47የመቶ አለቃውም የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በርግጥ ጻድቅ ነበር” ብሎ እግዚአብሔርን አመሰገነ። 48ይህንኑ ለማየት በስፍራው ተሰብስበው የነበሩ ሰዎችም ሁሉ የሆነውን ነገር በተመለከቱ ጊዜ ደረታቸውን እየደቁ ተመለሱ። 49ነገር ግን ኢየሱስን በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ እንዲሁም ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት ሴቶች ይህን እየተመለከቱ ከሩቅ ቆመው ነበር።

የኢየሱስ መቀበር

23፥50-56 ተጓ ምብ – ማቴ 27፥57-61ማር 15፥42-47ዮሐ 19፥38-42

50የአይሁድ ሸንጎ አባል የሆነ፣ አንድ ዮሴፍ የሚባል በጎና ጻድቅ ሰው ነበር። 51ይህ ሰው በሸንጎው ምክርና ድርጊት አልተባበረም ነበር፤ እርሱም አርማትያስ የምትባል የአይሁድ ከተማ ሰው ሲሆን፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት ይጠባበቅ ነበር። 52ይህም ሰው ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው፤ 53በተፈቀደለትም ጊዜ፣ ሥጋውን አውርዶ በበፍታ ገነዘው፤ ከድንጋይ ተፈልፍሎ በተሠራና ገና ማንም ባልተቀበረበት መቃብር ውስጥ አስቀመጠው። 54ዕለቱ የመዘጋጃ ቀን ነበረ፤ ሰንበትም ሊገባ ነበር።

55ከገሊላ ጀምሮ ከኢየሱስ ጋር የመጡት ሴቶችም ተከትለው መቃብሩን አዩ፤ ሥጋውንም እንዴት እንዳስቀመጡት ተመለከቱ። 56ከዚያም ተመልሰው ሽቱና ቅባት አዘጋጁ፤ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት በሰንበት ቀን ዐረፉ።

Habrit Hakhadasha/Haderekh

הבשורה על-פי לוקס 23:1-56

1ראשי הכוהנים, הסופרים, זקני העם וחברי הסנהדרין הוליכו את ישוע אל פילטוס, 2ומיד החלו להאשים אותו: ”האיש הזה מסית את העם לא לשלם מס לקיסר הרומאי, וטוען שהוא המשיח, כלומר מלך!“

3”האם אתה מלך היהודים?“ שאל פילטוס את ישוע. ”אתה אומר“, ענה ישוע.

4פילטוס פנה אל ראשי הכוהנים ואל ההמון וקרא: ”מה אתם רוצים ממנו? הוא לא עבר על שום חוק!“

5אולם הם התעקשו: ”אבל הוא מסית את העם בכל אזור יהודה נגד השלטון. הוא החל בכך בגליל, ועכשיו הוא בא לירושלים.“

6”האם הוא תושב הגליל?“ שאל פילטוס.

7”כן“, השיבו לו. מאחר שהגליל היה במחוז שיפוטו של הורדוס, החליט פילטוס לשלוח את ישוע אליו. מלבד זאת, באותה העת היה הורדוס בירושלים.

8הורדוס שמח מאוד לראות את ישוע, מכיוון ששמע עליו ניסים ונפלאות, ומזה זמן רב השתוקק לפגוש אותו פנים אל פנים ולחזות בניסים שחולל.

9הורדוס שאל את ישוע שאלות רבות, אולם ישוע לא השיב דבר. 10בינתיים ראשי הכוהנים והסופרים הטיחו את האשמותיהם בישוע.

11גם הורדוס וחייליו בזו לישוע וצחקו לו; הם הלבישו אותו גלימת פאר ושלחוהו חזרה אל פילטוס. 12הורדוס ופילטוס, שהיו עד אז אויבים, הפכו באותו יום לידידים.

13פילטוס אסף את ראשי הכוהנים, ומנהיגים אחרים ואת העם, 14והודיע להם: ”הבאתם לפני את האיש הזה וטענתם שהוא מסית את העם למרוד בשלטון. חקרתי אותו היטב בנוכחותכם ולא מצאתי כל יסוד להאשמותיכם! 15גם הורדוס לא מצא כל אשמה בישוע, ולכן שלח אותו אלינו. האיש הזה לא עשה כל מעשה שדינו מוות! 16משום כך אלקה אותו בשוט ואשחרר אותו.“ 17מדי שנה בחג הפסח, נהג פילטוס לשחרר אסיר יהודי אחד.

18אך כולם צעקו פה אחד: ”קחו אותו מכאן! שחרר לנו את בר־אבא!“ 19(בר־אבא היה במאסר באשמת רצח והסתה למרד בירושלים). 20פילטוס רצה לשחרר את ישוע, ולכן ניסה להתווכח עם הקהל. 21אבל הקהל התעקש: ”צלוב אותו! צלוב אותו!“

22פילטוס שאל אותם פעם שלישית: ”מדוע? מה הוא עשה? לא מצאתי כל סיבה להוציאו להורג. אלקה אותו בשוט ואשחרר אותו.“ 23אבל הם המשיכו לצעוק ולהפציר בו לצלוב את ישוע, וצעקותיהם הכריעו את הנידון.

24פילטוס נכנע לדרישתם ודן את ישוע למוות. 25על־פי בקשתם שחרר את בר־אבא, שהיה אסור באשמת רצח ומרידה, ומסר לידיהם את ישוע כדי שיעשו בו כרצונם.

26בהוליכם את ישוע אל מקום הצליבה פגשו בדרך את שמעון הקוריני, שחזר מן השדה, ואילצוהו ללכת אחרי ישוע ולשאת את צלבו. 27בין הקהל הרב שהלך אחרי ישוע היו גם נשים רבות שספדו עליו. 28ישוע פנה אליהן ואמר: ”בנות ירושלים, אל תבכינה עלי, כי אם על עצמכן ועל ילדיכן, 29כי תבוא העת שבה נשים שאין להן ילדים תיחשבנה לבנות מזל.23‏.29 כג 29 כלשונו: ”הנה ימים באים ויאמרו: ’אשרי העקרות ואשרי המעיים אשר לא ילדו ואשרי השדיים אשר לא הניקו‘.“ 30בעת ההיא יתחננו בני־האדם לפני ההרים שיפלו עליהם ויכסו אותם, ולפני הגבעות – שתקבורנה אותם. 31שהרי אם זהו גורלו של אדם חף מפשע, מה נורא יהיה גורלם של האשמים באמת!“23‏.31 כג 31 כלשונו: ”אם ככה יעשו בעץ הלח, מה ייעשה ביבש?“

32יחד עם ישוע הובלו למוות גם שני פושעים. 33בהגיעם אל המקום שנקרא ”מקום הגולגולת“ – הם צלבו את השלושה: את ישוע במרכז, ואת שני הפושעים לימינו ולשמאלו.

34”אבי, סלח להם,“ קרא ישוע, ”כי אינם יודעים מה הם עושים!“ בינתיים ערכו החיילים הגרלה וחילקו ביניהם את בגדי ישוע. 35ההמון עמד והביט במתרחש, ואילו מנהיגי העם לעגו לו וקראו: ”הוא ’הושיע‘ כל־כך הרבה אנשים? אם הוא באמת המשיח בחיר האלוהים, הבה נראה כיצד יושיע את עצמו!“

36גם החיילים התלו בו; הם נתנו לו לשתות חומץ 37וקראו: ”אם אתה באמת מלך היהודים, הושע את עצמך!“

38מעל ראשו של ישוע תלו שלט: ”זהו מלך היהודים“.

39אחד הפושעים שהיה תלוי לצידו של ישוע לעג לו ואמר: ”אם אתה באמת המשיח, מדוע אינך מציל את עצמך ואותנו לפני שיהיה מאוחר מדי?“

40הפושע השני גער בחברו ואמר: ”האם גם במותך אינך ירא את האלוהים? 41אנחנו נענשים בעונש שמגיע לנו על מעשינו הרעים, אולם האדם הזה חף מפשע!“ 42הוא פנה אל ישוע ואמר: ”ישוע, זכור אותי כשתבוא אל מלכותך.“

43”עוד היום אתה תהיה איתי בגן־עדן“, ענה לו ישוע.

44בשעה שתים־עשרה בצהריים כיסה חושך את כל הארץ למשך שלוש שעות. 45אור השמש חשך, והפרוכת התלויה לפני קודש הקודשים בבית־המקדש נקרעה לשניים.

46לאחר מכן קרא ישוע בקול גדול: ”אבי, אני מפקיד את רוחי בידך.“ ונפח את נשמתו.

47קצין רומאי אחד, אשר ראה את המתרחש, נמלא יראת אלוהים וקרא: ”האיש הזה באמת היה צדיק!“

48משנוכחו האנשים שבאו לחזות בצליבה כי ישוע מת, הצטערו צער רב והלכו לבתיהם. 49כל חבריו וידידיו של ישוע, וביניהם הנשים שהלכו אחריו מהגליל, עמדו במרחק מה והביטו במתרחש.

50‏-51בין ידידיו של ישוע היה גם אדם בשם יוסף מהעיירה היהודית רמתיים. יוסף היה איש טוב וישר והאמין בביאת המשיח. למרות שהיה חבר הסנהדרין לא הסכים עם החלטתם ופעולתם.

52יוסף הלך אל פילטוס וביקש ממנו את גופתו של ישוע. 53לאחר שהוריד את הגופה מן הצלב עטף אותה יוסף בסדין, וקבר אותה בקבר חדש חצוב בסלע, שטרם נקבר בו איש. 54כל זה התרחש ביום שישי בערב, לפני כניסת השבת.

55הנשים אשר באו עם ישוע מהגליל הלכו אחרי יוסף וראו היכן שקבר את הגופה. 56לאחר מכן הלכו והכינו מרקחת בשמים, אולם לא שבו מיד אל הקבר, כי בינתיים נכנסה השבת והן לא רצו לחלל אותה.