ሉቃስ 21 – NASV & HHH

New Amharic Standard Version

ሉቃስ 21:1-38

መበለቷ የሰጠችው መባ

21፥1-4 ተጓ ምብ – ማር 12፥41-44

1ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታሞች በቤተ መቅደሱ መባ መሰብሰቢያ ውስጥ መባቸውን ሲጨምሩ አየ። 2ደግሞም አንዲት ድኻ መበለት ሁለት ትንንሽ የናስ ሳንቲሞች በዚያ ስትጨምር ተመለከተ። 3እንዲህም አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉም ይልቅ ይህች ድኻ መበለት የበለጠ ሰጥታለች። 4እነዚህ ሰዎች የሰጡት ከትርፋቸው ላይ ሲሆን፣ እርሷ ግን የሰጠችው በድኻ ዐቅሟ ያላትን መተዳደሪያ በሙሉ ነው።”

የዘመኑ መጨረሻ ምልክቶች

21፥5-36 ተጓ ምብ – ማቴ 24ማር 13

21፥12-17 ተጓ ምብ – ማቴ 10፥17-22

5ከደቀ መዛሙርት አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ በውብ ድንጋዮችና በስእለት ስጦታዎች እንዳማረ ሲነጋገሩ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ 6“ይህ የምታዩት ሁሉ ሳይፈርስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደ ተካበ የማይቀርበት ጊዜ ይመጣል።”

7እነርሱም፣ “መምህር ሆይ፤ እንግዲህ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? ደግሞም ይህ እንደሚሆን ምልክቱ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።

8እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች፣ ‘እኔ እርሱ ነኝ’ በማለት፣ ደግሞም፣ ‘ጊዜው ቀርቧል’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እናንተ ግን እነርሱን አትከተሏቸው። 9ስለ ጦርነትና ስለ ሕዝብ ዐመፅ ስትሰሙ አትደንግጡ፤ ይህ አስቀድሞ መሆን የሚገባው ነውና፤ መጨረሻው ግን ወዲያውኑ አይሆንም።”

10ቀጥሎም እንዲህ አላቸው፤ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ 11ታላቅ የመሬት መናወጥ ይሆናል፤ ራብና ቸነፈር በተለያየ ስፍራ ይከሠታል፤ አስፈሪ ነገር እንዲሁም ከሰማይ ታላቅ ምልክት ይሆናል።

12“ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን ሰዎች ይይዟችኋል፤ ያሳድዷችኋል፤ ወደ ምኵራብና ወደ ወህኒ ቤት ያስገቧችኋል፤ በነገሥታትና በገዥዎች ፊት ያቀርቧችኋል፤ ይህም ሁሉ በስሜ ምክንያት ይደርስባችኋል። 13ይህም ለመመስከር ጥሩ ዕድል ይሆንላችኋል። 14ስለዚህ ምን መልስ እንሰጣለን በማለት አስቀድማችሁ እንዳትጨነቁ ይህን ልብ በሉ፤ 15ተቃዋሚዎቻችሁ ሁሉ ሊቋቋሙትና ሊያስተባብሉት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁና። 16ወላጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ጓደኞቻችሁ እንኳ ሳይቀሩ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤ 17ስለ ስሜም በሰዎች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። 18ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጕር አንዷ እንኳ አትጠፋም፤ 19ጸንታችሁም በመቆም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።

20“ኢየሩሳሌም በጦር ሰራዊት ተከብባ በምታዩበት ጊዜ፣ ጥፋቷ መቃረቡን ዕወቁ። 21በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤ በከተማ ያሉትም ከዚያ ይውጡ፤ በገጠር ያሉትም ወደ ከተማዪቱ አይግቡ፤ 22የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይህ የበቀል ጊዜ ነውና። 23በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይመጣል፤ ስለዚህ በዚያን ወቅት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ እናቶች ወዮላቸው! 24በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብም ሁሉ በምርኮ ይወሰዳሉ፤ ኢየሩሳሌምም የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።

25“በፀሓይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክት ይሆናል፤ ከባሕሩና ከሞገድ ድምፅ የተነሣ፣ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ይጨነቃሉ፤ ይታወካሉም። 26የሰማያት ኀይላት ስለሚናወጡ፣ ሰዎች በፍርሀትና በዓለም ላይ ምን ይመጣ ይሆን እያሉ በመጠባበቅ ይዝላሉ። 27በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ በኀይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። 28እናንተም እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ተቃረበ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ወደ ላይ ቀና አድርጉ።”

29ቀጥሎም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ “በለስንና ዛፎችን ሁሉ ተመልከቱ፤ 30ቅጠሎቻቸው አቈጥቍጠው ስታዩ፣ በዚያን ጊዜ በጋ መቃረቡን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 31እንዲሁ ደግሞ እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች ዕወቁ።

32“እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።21፥32 ወይም ዘር 33ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።

34“እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤ 35ይህ በመላው ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ይደርሳልና። 36ስለዚህ ከሚመጣው ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ ሁልጊዜ ተግታችሁ ጸልዩ።”

37ኢየሱስም ቀን ቀን በቤተ መቅደስ እያስተማረ፣ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደ ተባለ ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር። 38ሕዝቡም ሁሉ ሊሰሙት ማልደው ወደ ቤተ መቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

Habrit Hakhadasha/Haderekh

הבשורה על-פי לוקס 21:1-38

1ישוע עמד בבית־המקדש והביט בעשירים שמביאים את תרומותיהם אל תיבת האוצר. 2בין התורמים הרבים הבחין גם באלמנה עניה שתרמה שתי פרוטות.

3”אומר לכם את האמת,“ העיר ישוע, ”האלמנה הענייה הזאת תרמה יותר מכל העשירים האלה גם יחד! 4כי העשירים תרמו סכומים קטנים ביחס לרכוש הרב שיש להם, ואילו האלמנה הזאת נתנה את כל מה שהיה לה.“

5אחדים מתלמידיו העירו את תשומת לבו לעבודת האבנים המהודרת של בית־המקדש, ולחפצים היקרים שתרמו האנשים.

6”אתם יכולים להתפעל מהמראה בינתיים,“ אמר להם ישוע, ”אולם יבוא היום שהכול ייהרס; אף אבן לא תישאר במקומה.“

7”רבי, מתי יקרה הדבר?“ שאלו התלמידים. ”האם נקבל אזהרה מראש?“ 8השיב ישוע: ”אל תניחו לאיש לרמות אתכם. אנשים רבים יבואו ויטענו כי הם המשיח, ויודיעו שהקץ קרוב. אבל אל תאמינו להם. 9כאשר תשמעו על מהומות ומלחמות, אל תיבהלו ואל תאבדו את עשתונותיכם. כי אמנם תפרוצנה מלחמות, אבל הקץ לא יבוא מיד. 10מדינות וממלכות תילחמנה זו בזו, 11בארצות רבות תתחוללנה רעידות אדמה אדירות ומגפות, ויהיה רעב גדול; בשמים ייראו מראות נוראים ואותות גדולים.

12”אולם לפני שיתרחשו כל הדברים האלה ירדפו אתכם, ישפטו אתכם בבתי־כנסת, ישליכו אתכם לכלא ויעמידו אתכם לפני מלכים ושליטים למען שמי. 13זאת תהיה הזדמנות עבורכם להעיד עלי. 14אל תדאגו כיצד תתגוננו בפני האשמותיהם, 15כי אשים בפיכם את המילים המתאימות, ואתן לכם חכמה שאויביכם לא יוכלו להתמודד איתה ולסתור אותה. 16גם האנשים הקרובים אליכם ביותר – הוריכם, אחיכם, חבריכם וקרובי משפחתכם – יבגדו בכם ויביאו למאסרכם, ויהיו ביניכם כאלה שימותו. 17כולם ישנאו אתכם משום שאתם שייכים לי, 18אולם אף שערה אחת לא תיפול מראשכם! 19בנאמנותכם ובעמידתכם האיתנה תושיעו את נפשותיכם.

20”כאשר תראו את ירושלים מוקפת אויבים דעו שחורבנה קרוב. 21אז תושבי יהודה יברחו אל ההרים; על תושבי ירושלים להשתדל לברוח מהעיר, ואוי לתושבי הסביבה שינסו להיכנס לירושלים! 22יהיו אלה ימי נקם אשר נועדו לקיים את נבואות התנ״ך. 23אוי לנשים ההרות ולמניקות באותם ימים, מפני שצרה גדולה תבוא על הארץ, ואלוהים ישפוך את זעמו על העם הזה. 24רבים ייהרגו בחרב האויב או יוגלו לכל קצוות תבל, וירושלים תיפול בידי גויים אשר ידכאו אותה עד שתסתיים תקופת שלטון הגויים במועד שקבע ה׳.

25”אותות מבשרי רעה יופיעו בשמש, בירח ובכוכבים, ואילו על פני האדמה – עמים שלמים יתייאשו ויפחדו מגעש הים והגלים הסוערים. 26אנשים יתעלפו מאימה ופחד מפני המאורעות שיבואו על העולם, משום שכוחות השמים יתמוטטו. 27ואז יראו אנשי הארץ את בן־האדם בא בענן, בגבורה ובכבוד רב.21‏.27 כא 27 דניאל ז 13‏-14 28כאשר יתחילו כל הדברים האלה להתרחש, התעודדו והרימו את ראשכם, כי ישועתכם קרובה!“

29אחר כך סיפר להם ישוע את המשל הבא: ”הביטו בעץ התאנה או בכל עץ אחר. 30כאשר העץ מלבלב יודעים אתם שקרב הקיץ בלי שיאמרו לכם זאת. 31כאשר כל מה שסיפרתי לכם יתחיל להתרחש, דעו לכם שמלכות האלוהים קרובה.

32”אני אומר לכם: כל הדברים האלה יתרחשו לפני שיחלוף הדור הזה. 33השמים והארץ יחלפו, אבל דברי לא יחלפו.

34”היזהרו לכם – אל תאבדו את הראש בשכרות, בבזבזנות, בתענוגות ובדאגות מחייה, פן יבוא עליכם היום ההוא במפתיע, כמלכודת. 35היום ההוא יבוא על כל יושבי תבל! 36משום כך שימרו תמיד על ערנותכם, והתפללו שאלוהים יעניק לכם כוח לצאת בשלום מכל העתיד להתרחש, ולהתייצב לפני בן־האדם.“ 37‏-38יום־יום הלך ישוע ללמד בבית־המקדש, והעם היה מתאסף בהמונים משעות הבוקר המוקדמות כדי להקשיב לדבריו. בלילות נהג ישוע ללכת לישון על הר הזיתים.