箴言 知恵の泉 6 – JCB & NASV

Japanese Contemporary Bible

箴言 知恵の泉 6:1-35

6

愚かな者にならないように

1わが子よ。見ず知らずの人の保証人になり、

借金の肩代わりをすることになったら、

それは深刻な問題です。

2あなたは自分が承諾したことによって、

罠に陥ったのです。

3もしそうなったら、すぐに手を打ちなさい。

プライドを捨て、恥をかくことを覚悟して

相手のところへ飛んで行き、

証書から名前を消してもらいなさい。

4先に延ばさず、今すぐしなさい。

眠るのはそのあとにしなさい。

5鹿が猟をする者の手を逃れ、

鳥が網から逃れるように、うまく逃れるのです。

6怠け者よ、蟻を見ならいなさい。

蟻のやり方を見て学びなさい。

7蟻には、働けと命じる支配者がいません。

8それでも夏の間懸命に働き、冬の食糧を集めます。

9ところが、あなたがたは眠ってばかりいます。

いったいいつ目を覚ますのですか。

10「まだしばらく寝かせてほしい」と言っていますが、

その「ほんの少し」が問題なのです。

11のんびり眠っている間に

泥棒のように貧しさが近づいてきて、

気がついたときには手遅れです。

12-13悪者は、どうしようもない人間です。

彼らは平気でうそをつき、

仲間には目くばせや合図で企みを伝えます。

14反抗心が人一倍強く、悪いことばかり考え、

いさかいを巻き起こすのです。

15しかし、あっという間に身を滅ぼし、

倒れたら二度と立ち直れません。

16-19神のきらいなものが六つ、いいえ七つあります。

高慢な態度、うそをつくこと、人殺し、

悪だくみ、悪事に熱中すること、

偽証、仲たがいの種をまくことです。

20若者よ。親の言いつけを守りなさい。

21一瞬たりとも忘れないように、

親の教えをしっかり心に刻み込みなさい。

22昼も夜も彼らの助言に従えば、いつも安全です。

朝、目を覚ましたら、教えどおりに一日を始めなさい。

23危険だとわかっていればこそ、

前もって忠告してくれるのです。

だから忠告を聞き、良き人生を送りなさい。

24そうすれば、悪い女の甘いお世辞に

惑わされることもありません。

25彼女の美しさに心を奪われてはなりません。

誘惑するような目つきにだまされてはいけません。

26彼女におぼれると金を巻き上げられ、

人妻にうつつを抜かすと身を滅ぼすからです。

27火をかかえ込めばやけどをし、

28熱く燃える炭火の上を歩けば、やけどを負います。

29同じように、人妻と汚らわしい関係を結ぶ者も

罰を免れません。

30空腹のあまり盗みをしてしまったとしたら、

言い訳の余地があるかもしれません。

31しかし、盗みは盗みです。

償いにたくさんの罰金を払わなければなりません。

持ち物を全部売り払ってでも、

支払わなければならないのです。

32人妻と関係する者は愚かな者で、

自分で自分を滅ぼします。

33身も心も傷つき、取り返しのつかない恥をかくのです。

34嫉妬に狂った彼女の夫はあなたに復讐し

35どんな償いをしても赦しません。

New Amharic Standard Version

ምሳሌ 6:1-35

ከተላላነት መራቅ

1ልጄ ሆይ፤ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፣

ስለ ሌላውም ሰው እጅ መትተህ ቃል ብትገባ፣

2በተናገርኸው ነገር ብትጠመድ፣

ከአፍህ በወጣውም ቃል ብትያዝ፣

3ልጄ ሆይ፤ ራስህን ለማዳን ይህን አድርግ፤

በጎረቤትህ እጅ ስለ ወደቅህ፣

ሄደህ ራስህን አዋርድ፤

ጎረቤትህን አጥብቀህ ነዝንዘው።

4ዐይኖችህ እንቅልፍ አይያዛቸው፣

ሽፋሽፍቶችህም አያንጐላጁ።

5ከዐዳኝ እጅ እንዳመለጠች ሚዳቋ፣

ከአጥማጅ ወጥመድ እንዳፈተለከች ወፍ ራስህን አድን።

6አንተ ታካች፤ ወደ ጕንዳን ሂድ፤

ዘዴውን አስተውለህ ጠቢብ ሁን፤

7አዛዥ የለውም፤

አለቃም ሆነ ገዥ የለውም፤

8ሆኖም ግን በበጋ ምግቡን ያከማቻል፤

በመከርም ወቅት ቀለቡን ይሰበስባል።

9አንተ ታካች፤ እስከ መቼ ትተኛለህ?

ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?

10ጥቂት ማንቀላፋት፤ ጥቂት ማንጐላጀት፤

እጅን አጣጥፎ “እስቲ ጥቂት ልረፍ” ማለት፤

11ድኽነት እንደ ወንበዴ፣

ዕጦትም መሣሪያ እንደ ታጠቀ ሰው6፥11 ወይም እንደ ቦዘኔ ወይም ዕጦት እንደ ለማኝ ከተፍ ይልብሃል።

12ወሮበላና ጨካኝ፣

ነውረኛ አንደበቱን ይዞ የሚዞር፣

13በዐይኑ የሚጠቅስ፣

በእግሩ ምልክት የሚሰጥ፣

በጣቶቹ የሚጠቍም፣

14በልቡ ተንኰል ክፋትን የሚያውጠነጥን፣

ምንጊዜም ጠብ ይጭራል።

15ስለዚህ በቅጽበት መዓት ይወርድበታል፤

በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

16እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤

የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦

17ትዕቢተኛ ዐይን፣

ሐሰተኛ ምላስ፣

ንጹሕ ደም የሚያፈስሱ እጆች፣

18ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣

ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣

19በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣

በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።

ከዝሙት መራቅ

20ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ትእዛዝ አክብር፤

የእናትህንም ትምህርት አትተው።

21ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤

በዐንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።

22በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤

በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤

በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል።

23እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤

ይህችም ትምህርት ብርሃን፣

የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት፤

24እርሷም ከምግባረ ብልሹ ሴት፣

ልዝብ አንደበት ካላት ዘልዛላ ሴት ትጠብቅሃለች።

25ውበቷን በልብህ አትመኝ፤

በዐይኗም አትጠመድ፤

26ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤

አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።

27ለመሆኑ ልብሱ ሳይቃጠል፣

በጕያው እሳት መያዝ የሚችል ሰው አለን?

28አንድ ሰው እግሮቹ ሳይቃጠሉ፣

በፍም ላይ መሄድ ይችላልን?

29ከሰው ሚስት ጋር የሚተኛም እንደዚሁ ነው፤

የሚደርስባትም ከቅጣት አያመልጥም።

30ሌባ በተራበ ጊዜ ራቡን ለማስታገሥ ቢሰርቅ፣

ሰዎች አይንቁትም።

31በቤቱ ያለውን ሀብት ሁሉ የሚጠይቀው ቢሆንም፣

ከተያዘ ሰባት ዕጥፍ መክፈል አለበት።

32የሚያመነዝር ሰው ግን ማመዛዘን ይጐድለዋል፤

እንዲህ የሚያደርግ ሁሉ ራሱን ያጠፋል።

33መደብደብና ውርደት ዕጣው ነው፤

ኀፍረቱም ከቶ አይወገድም፤

34ቅናት የባልን ቍጣ ይቀሰቅሳልና፤

በሚበቀልበትም ጊዜ ምሕረት አያደርግም።

35ምንም ዐይነት ካሳ አይቀበልም፤

የቱንም ያህል ብዙ ቢሆን መማለጃን እሺ አይልም።