הבשורה על-פי יוחנן 10 – HHH & NASV

Habrit Hakhadasha/Haderekh

הבשורה על-פי יוחנן 10:1-42

1”אני אומר לכם באמת,“ המשיך ישוע, ”מי שמסרב להיכנס למכלאת הצאן דרך השער, ובוחר להיכנס בדרך הצדדית, הוא גנב או שודד. 2האדם שנכנס דרך השער הוא רועה הצאן. 3השומר יפתח לו את השער, עדר הצאן ישמע ויכיר את קולו, והרועה יוביל את הצאן החוצה כשהוא נוקב בשם כל כבשה. 4הרועה הולך בראש והעדר נוהר אחריו, כי הוא מזהה את הרועה ומכיר את קולו. 5הצאן לא תלכנה אחרי אדם זר, אלא תברחנה מפניו, כי קולו אינו מוכר להן.“

6אלה ששמעו משל זה מפי ישוע לא הבינו למה התכוון, 7ולכן ישוע הסביר להם: ”אמן אני אומר לכם: אני השער של מכלאת הצאן. 8כל אלה שבאו לפני היו גנבים ושודדים, אולם הצאן לא שמעו בקולם. 9כן, אנוכי השער. הנכנסים דרכי יוושעו וימצאו מרעה עשיר בבואם ובצאתם. 10הגנב בא לגנוב, להרוג ולהשמיד, ואילו אני באתי להעניק חיים בשפע.

11”אני הרועה הטוב, ורועה טוב מקריב את חייו למען צאנו. 12כאשר רועה שכיר יראה זאב מתקרב, הוא יברח ויעזוב את הצאן לאנחות, כי העדר אינו שייך לו, והזאב יחטוף ויפזר את הצאן. 13הרועה השכיר יברח, משום שאינו אלא שכיר ואין הוא דואג לצאן באמת.

14”אני הרועה הטוב; אני מכיר את צאני והן מכירות אותי, 15כשם שאבי מכיר אותי ואני מכיר את אבי; ואני מקריב את חיי למען הצאן. 16יש לי עדר נוסף שאינו מהמכלאה הזאת. עלי להנהיג גם אותו, והצאן שומעות בקולי; כך יהיה עדר אחד ורועה אחד.

17”אבי אוהב אותי משום שאני מקריב את חיי כדי שאקבל אותם חזרה. 18איש אינו יכול להרוג אותי ללא הסכמתי. אני מקריב את חיי מרצוני, מפני שיש לי זכות וכוח להקריב את חיי כשאני רוצה בכך, ואף זכות וכוח להשיבם לעצמי. אלוהים הוא המעניק לי זכות זאת.“

19דבריו אלה שוב גרמו למחלוקת בין מנהיגי היהודים. 20חלקם אמר: ”או שהוא יצא מדעתו, או שנכנס בו שד! מדוע אתם מקשיבים לו?“

21אחרים אמרו: ”הוא אינו נשמע כמי שנכנס בו שד. האם שד יכול לפקוח עיני עיוורים?“

22בחג החנוכה, בחורף, 23התהלך ישוע בבית־המקדש באגף הנקרא ”אולם שלמה“. 24היהודים הקיפוהו מכל עבר ושאלו: ”עד מתי בכוונתך לסקרן אותנו? אם אתה הוא המשיח, מדוע אינך אומר זאת בפירוש?“

25”כבר אמרתי לכם, אבל לא האמנתם לי“, השיב ישוע. ”המעשים שאני עושה בשם אבי מאשרים זאת. 26אולם אינכם מאמינים לי, כי אינכם שייכים לצאני. 27אני מכיר את צאני, צאני מכירות את קולי והן הולכות אחרי. 28אני מעניק להן חיי נצח והן לא תאבדנה. איש לא יחטוף אותן ממני, 29כי אבי נתן לי אותן, והוא חזק וגיבור מכולם. משום כך לא יוכל איש לחטוף אותן ממני. 30אבי ואני אחד אנחנו!“

31שוב החלו מנהיגי היהודים להשליך עליו אבנים.

32”הראיתי לכם הרבה מעשים טובים בשם אבי, איזה מהם גרם לכך שתשליכו עלי אבנים?“ שאל ישוע.

33”איננו משליכים עליך אבנים בגלל המעשים הטובים שעשית, אלא בגלל שאתה מגדף את האלוהים; למרות שאתה אדם, אתה עושה את עצמך לאלוהים!“

34”אך הכתובים שלכם אומרים: ’אלוהים אתם‘,10‏.34 י 34 תהלים פב 6 והכוונה היא לבני־האדם“, השיב ישוע. 35”אם האנשים שאליהם מדברים הכתובים מכונים ’אלוהים‘, והכתוב הוא דבר אמת, 36מדוע קוראים אתם ’מגדף‘ למי שקדשו האב ונשלח לעולם הזה על־ידו, ושטוען כי הוא בן האלוהים? 37אם איני עושה מעשים כפי שעושה אבי, אל תאמינו לי. 38אולם אם אני אכן עושה את מעשי אבי, האמינו לפחות למעשים גם אם אינכם מאמינים לי, ואז תשוכנעו שאבי שוכן בי ואני בו.“

39הם שוב רצו לתפוס את ישוע, אולם הוא התחמק מידיהם. 40ישוע חזר לעבר הירדן, למקום שבו הטביל יוחנן לראשונה. הוא נשאר שם זמן־מה, 41ואנשים רבים הלכו אחריו.

”יוחנן לא חולל נסים,“ אמרו זה לזה, ”אולם כל מה שאמר על האיש הזה היה אמת.“ 42אנשים רבים במקום ההוא האמינו כי ישוע באמת המשיח.

New Amharic Standard Version

ዮሐንስ 10:1-42

እረኛና መንጋው

1“እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች ጕረኖ በበሩ ሳይሆን፣ በሌላ በኩል ዘልሎ የሚገባ ሌባና ነጣቂ ነው። 2በበሩ የሚገባ ግን እርሱ የበጎቹ እረኛ ነው፤ 3በር ጠባቂው በሩን ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ። የራሱንም በጎች በየስማቸው እየጠራ ያወጣቸዋል። 4የራሱ የሆኑትንም ሁሉ ካወጣ በኋላ ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል። 5እንግዳ የሆነውን ግን ድምፁን ስለማያውቁ ከእርሱ ይሸሻሉ እንጂ ፈጽሞ አይከተሉትም።” 6ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን ምን እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም።

7ስለዚህ ኢየሱስ ዳግም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ። 8ከእኔ በፊት የመጡት ሁሉ ሌቦችና ቀማኞች ነበሩ፤ በጎቹ ግን አልሰሟቸውም። 9በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል10፥9 ወይም በደኅና ይጠበቃል፤ ይገባል፤ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል። 10ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።

11“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል፤ 12ተቀጣሪው እረኛ ግን በጎቹ የእርሱ ስላልሆኑ፣ ተኵላ ሲመጣ ጥሏቸው ይሸሻል፤ ተኵላውም በጎቹን ይነጥቃል፤ ይበትናቸዋልም። 13የሚሸሸውም ተቀጣሪ ስለ ሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው።

14“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን ዐውቃለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፤ 15ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው ነው። ሕይወቴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ። 16ከዚህ ጕረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት አለብኝ። እነርሱም ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ። 17መልሼ ለማንሣት ሕይወቴን አሳልፌ ስለምሰጥ አባቴ ይወድደኛል። 18ሕይወቴን በራሴ ፈቃድ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ አሳልፌ ለመስጠትም ሆነ ለማንሣት ሥልጣን አለኝ፤ ይህን ትእዛዝ የተቀበልሁትም ከአባቴ ነው።”

19ከዚህም ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ተፈጠረ። 20ብዙዎቹም፣ “ጋኔን ያደረበት እብድ ነው፤ ለምን ትሰሙታላችሁ?” አሉ።

21ሌሎች ግን፣ “ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው ንግግር አይደለም፤ ጋኔን የዐይነ ስውርን ዐይን መክፈት ይችላልን?” አሉ።

የአይሁድ አለማመን

22በኢየሩሳሌምም የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል10፥22 ዕብራይስጡ “ኑካ” ይላል። ሆነ፤ ጊዜውም ክረምት ነበረ፤ 23ኢየሱስም በቤተ መቅደስ ግቢ፣ በሰሎሞን መመላለሻ ያልፍ ነበር፤ 24አይሁድም ከብበውት፣ “እስከ መቼ ልባችንን አንጠልጥለህ ታቈየናለህ? አንተ ክርስቶስ10፥24 ወይም መሲሑ ከሆንህ በግልጽ ንገረን” አሉት።

25ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ታምራትም ስለ እኔ ይናገራሉ፤ 26እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም፤ 27በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፤ 28እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም። 29እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል10፥29 ብዙ የጥንት ቅጆች አባቴ የሰጠኝ ከሁሉ ይበልጣል ይላሉ።፤ ከአባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም። 30እኔና አብ አንድ ነን።”

31አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ፤ 32ኢየሱስ ግን፣ “ከአብ የሆኑ ብዙ ታላላቅ ታምራትን አሳየኋችሁ፤ ታዲያ ከእነዚህ ስለ የትኛው ትወግሩኛላችሁ?” አላቸው።

33አይሁድም፣ “የምንወግርህ፣ ተራ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ በማድረግ፣ የስድብ ቃል ስለ ተናገርህ ነው እንጂ ከእነዚህ ስለ የትኛውም አይደለም” ብለው መለሱለት።

34ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “በሕጋችሁ፣ ‘እናንት አማልክት ናችሁ አልሁ’ ተብሎ አልተጻፈምን? 35የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን ‘አማልክት’ ካላቸውና መጽሐፍም ሊሻር የማይቻል ከሆነ፣ 36ታዲያ፣ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ለራሱ ለይቶ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን፣ ተሳድበሃል ብላችሁ ለምን ትወነጅሉኛላችሁ? 37አባቴ የሚያደርገውን ባላደርግ አትመኑኝ፤ 38የማደርገው ከሆነ ግን እኔን ባታምኑኝ እንኳ፣ አብ በእኔ እንዳለ እኔም በአብ እንዳለሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ታምራቱን እመኑ።” 39እንደ ገናም ሊይዙት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከእጃቸው አመለጠ።

40ከዚያም ኢየሱስ፣ ቀደም ሲል ዮሐንስ ያጠምቅበት ወደ ነበረበት፣ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ተመለሰ፤ በዚያም ሰነበተ፤ 41ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጡ። እነርሱም፣ “ዮሐንስ አንድም ታምራዊ ምልክት አላደረገም፤ ነገር ግን ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ” አሉ። 42በዚያም ስፍራ ብዙዎች በኢየሱስ አመኑ።