箴言 21 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

箴言 21:1-31

1耶和華掌管君王的心,

易如支配壟溝的流水。

2人自以為行事正確,

但耶和華衡量人心。

3秉公行義比獻祭更蒙耶和華喜悅。

4高傲的眼,狂妄的心,惡人的燈,

都是罪惡。

5勤勞者的計劃必致富足,

行事急躁的人必致貧困。

6騙來的財如過眼雲霧,

使人掉進死亡的陷阱。

7惡人的暴力必毀滅自己,

因為他們行事不公不義。

8犯罪的人行徑扭曲,

純潔的人行為正直。

9寧願住在房頂的一角,

也不跟爭鬧之妻同屋。

10惡人貪戀邪惡,

對鄰舍殘忍無情。

11懲罰嘲諷者,愚人得智慧;

訓誡智者,他便長見識。

12公義的上帝鑒察惡人的家,

祂必使他們滅亡。

13掩耳不聽窮人呼求的,

他將來求救也無人管。

14暗中送的禮物能平息憤怒,

塞進懷裡的賄賂止息盛怒。

15正義得到伸張,

義人喜、惡人怕。

16人偏離明智之道,

終必與陰魂為伍。

17貪圖享受必窮困,

奢華宴樂難富足。

18惡人作義人的贖價,

奸徒替正直人受苦。

19寧願獨居曠野,

不跟吵鬧易怒的女子同住。

20智者家中積存寶物和油,

愚人將所有的揮霍一空。

21追求公義與慈愛的,

必尋得生命、公義和尊榮。

22智者攀上勇士的城池,

摧毀他們倚仗的堅壘。

23管住口舌,免遭禍患。

24嘲諷者狂妄自大,

行事驕橫無比。

25懶人的慾望害死自己,

因為他的手不肯做工。

26懶人整天貪得無厭,

義人施捨毫不吝嗇。

27惡人的祭物已經可憎,

何況他懷著惡意來獻!

28作偽證的終滅亡,

道實情的常發言。

29惡人虛張聲勢,

正直人謹慎行事。

30任何智慧、悟性和謀略,

都不能對抗耶和華。

31馬為爭戰之日預備,

勝敗由耶和華決定。

New Amharic Standard Version

ምሳሌ 21:1-31

1የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤

እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል።

2ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤

እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።

3ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣

በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።

4ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣

የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው።

5የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤

ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።

6በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣

በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።21፥6 አንዳንድ የዕብራይስጥ ጽሑፎች፣ የሰብዓ ሊቃናትና የቩልጌት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ጽሑፎች ግን ሞትን ለሚሹ በንኖ እንደሚጠፋ ተን ነው ይላሉ።

7ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤

ቅን ነገር ማድረግ አይወድዱምና።

8የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤

የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።

9ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣

በጣራ ላይ ጥግ ይዞ መኖር ይሻላል።

10ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤

ባልንጀራውም ከእርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።

11ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤

ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል።

12ጻድቁ21፥12 ወይም ጻድቁ ሰው የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤

ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።

13ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣

እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።

14በስውር የተደረገ ስጦታ ቍጣን ያበርዳል፤

በጕያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቍጣን ጸጥ ያደርጋል።

15ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሰኘዋል፤

ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።

16የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣

በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

17ቅንጦትን የሚወድድ ይደኸያል፤

የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድድም ባለጠጋ አይሆንም።

18ክፉ ሰው ለጻድቅ፣

ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።

19ከጨቅጫቃና ከቍጡ ሚስት ጋር ከመኖር፣

በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።

20በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤

ተላላ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።

21ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤

ሕይወትን ብልጽግናንና21፥21 ወይም ጽድቅን ክብርን ያገኛል።

22ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤

መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።

23አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣

ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል።

24ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው “ፌዘኛ” ይባላል፤

በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

25ታካችን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤

እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።

26ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤

ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።

27የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤

በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!

28ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤21፥28 ወይም የታዛዥ ሰው ቃል ግን ጸንቶ ይኖራል

እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።

29ክፉ ሰው በዐጕል ድፍረት ይቀርባል፤

ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል።

30እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣

አንዳችም ጥበብ፣ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።

31ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤

ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።