马太福音 19 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

马太福音 19:1-30

论休妻

1耶稣说完这番话,就离开加利利来到约旦河对岸的犹太地区。 2有一大群人跟着祂,祂就在那里医好了他们的病。

3有几个法利赛人到耶稣那里想试探祂,便问祂:“丈夫可以用任何理由休妻吗?”

4耶稣回答说:“你们没有读过吗?太初,造物主造了男人和女人,并且说, 5‘因此,人要离开父母,与妻子结合,二人成为一体。’ 6这样,夫妻不再是两个人,而是一体了。因此,上帝配合的,人不可分开。”

7他们追问:“那么,为什么摩西说,只要给妻子休书,就可以休她呢?”

8耶稣说:“因为摩西知道你们铁石心肠,所以才准你们休妻。但起初并不是这样。 9我告诉你们,除非是妻子不贞,否则,任何人休妻另娶,就是犯通奸罪19:9 有古卷在此处有“娶被休女子的人也犯了通奸罪”。。”

10门徒对耶稣说:“如果夫妻关系是这样,还不如不结婚。”

11耶稣说:“这话不是每个人都能接受的,只有那些得到这种恩赐的人才能接受。 12人不结婚的原因很多,有些是因为先天的缺陷,有些是被人阉了,也有些是为了天国而自己放弃结婚的权利。谁能接受,就让他接受吧。”

耶稣为小孩子祝福

13有人带着小孩子来见耶稣,请求耶稣为他们按手祷告,却受到门徒的责备。

14耶稣说:“让小孩子到我这里来,不要阻止他们,因为天国属于这样的人。” 15于是祂为他们按手祷告,然后才离开那里。

有钱的青年

16有一个人来请教耶稣:“老师,我该做什么善事才能获得永生呢?”

17耶稣说:“你为什么问我做什么善事?只有上帝是善的,你要得永生,就必须遵守祂的诫命。”

18那人问:“什么诫命呢?”

耶稣答道:“不可杀人,不可通奸,不可偷盗,不可作伪证, 19要孝敬父母,并且爱邻如己。”

20那青年说:“这些我早已遵守了,还缺什么呢?”

21耶稣告诉他:“如果你想做到纯全,就去变卖所有的产业,送给穷人,你就必有财宝存在天上,然后你来跟从我。” 22那青年听后,便忧伤地走了,因为他有许多产业。

23事后,耶稣对门徒说:“我实在告诉你们,有钱人进天国很困难。 24我再告诉你们,骆驼穿过针眼比有钱人进上帝的国还容易呢!”

25门徒听了,惊奇地问:“这样,谁能得救呢?”

26耶稣看着他们说:“对人而言,这不可能;但对上帝而言,凡事都可能。”

27彼得问道:“你看,我们已经撇下一切来跟从你了,将来会有什么奖赏呢?”

28耶稣说:“我实在告诉你们,到万物更新、人子坐在祂荣耀的宝座上时,你们这些跟从我的人也要坐在十二个宝座上,审判以色列的十二个支派。 29无论谁为我的名而撇下房屋、弟兄、姊妹、父母、儿女或田地,都要得到百倍的赏赐,而且承受永生。 30然而,许多为首的将要殿后,殿后的将要为首。”

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 19:1-30

ስለ መፋታት የቀረበ ጥያቄ

19፥1-9 ተጓ ምብ – ማር 10፥1-12

1ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፣ ገሊላን ትቶ ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደ። 2ብዙ ሕዝብም ተከተለው፤ በዚያም ፈወሳቸው።

3ፈሪሳውያንም ሊፈትኑት ቀርበው፣ “ለመሆኑ ለአንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ሚስቱን መፍታት ተፈቅዷልን?” ሲሉ ጠየቁት።

4እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን? 5እንዲህም አለ፤ ‘ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፣ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’ የተባለው በዚህ ምክንያት አይደለምን? 6ከእንግዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።”

7እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ሙሴ አንድ ወንድ የፍቺውን የምስክር ወረቀት ሰጥቶ ሚስቱን እንዲያሰናብት ለምን አዘዘ?” አሉት።

8ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሴ የልባችሁን ጥንካሬ አይቶ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ፈቀደላችሁ እንጂ ከመጀመሪያው እንዲህ አልነበረም፤ 9እላችኋለሁ፤ በትዳሯ ላይ ዝሙት ፈጽማ እስካልተገኘች ድረስ፣ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ ሴት የሚያገባ ሁሉ አመንዝራ ይሆናል፤ እርሷንም አመንዝራ ያደርጋታል፣ የተፈታችውንም ሴት የሚያገባ ያመነዝራል።”

10ደቀ መዛሙርቱም፣ “የባልና የሚስት ጕዳይ እንዲህ ከሆነ አለማግባት ይሻላል” አሉት።

11ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ከተሰጣቸው በስተቀር ይህን ትምህርት ማንም ሊቀበል አይችልም፤ 12ምክንያቱም አንዳንዶች ጃንደረባ ሆነው ይወለዳሉ፤ ሌሎች በሰው እጅ ተሰልበው ጃንደረባ ይሆናሉ፤ ደግሞም ለመንግሥተ ሰማይ ሲሉ ራሳቸውን ጃንደረባ የሚያደርጉ አሉ። ይህን መቀበል የሚችል ይቀበል።”

ኢየሱስ ሕፃናትን ባረካቸው

19፥13-15 ተጓ ምብ – ማር 10፥13-16ሉቃ 18፥15-17

13ከዚያም እጆቹን በላያቸው ላይ ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሕፃናትን ወደ እርሱ አቀረቧቸው። ደቀ መዛሙርቱ ግን ሕፃናቱን ያመጡትን ሰዎች ገሠጿቸው።

14ኢየሱስም፣ “ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማይ እንደ እነርሱ ላሉት ናትና” አላቸው። 15እጁንም ከጫነባቸው በኋላ ከዚያ ስፍራ ተነሥቶ ሄደ።

የሀብታሙ ጥያቄ

19፥16-29 ተጓ ምብ – ማር 10፥17-30ሉቃ 18፥18-30

16ከዚያም አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፤ የዘላለምን ሕይወት አገኝ ዘንድ ምን መልካም ነገር ልሥራ” ሲል ጠየቀው።

17ኢየሱስም፣ “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንዱ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ከፈለግህ ግን ትእዛዞቹን ጠብቅ” አለው።

18ሰውየውም፣ “የትኞቹን ትእዛዞች?” ሲል ጠየቀ።

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አትግደል፣ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ 19አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ።”

20ጕልማሳውም ሰው፣ “እነዚህንማ ጠብቄአለሁ፤ ከዚህ ሌላ የሚጐድለኝ ምን አለ?” አለው።

21ኢየሱስም፣ “ፍጹም ለመሆን ከፈለግህ፣ ሄደህ ንብረትህን ሁሉ ሸጠህ፣ ገንዘቡን ለድኾች ስጥ፤ በሰማይም ሀብት ታገኛለህ። ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።

22ጕልማሳው ሰውየም ይህን ሲሰማ፣ ብዙ ሀብት ስለ ነበረው እያዘነ ሄደ።

23ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለሀብታም ወደ መንግሥተ ሰማይ መግባት እጅግ አስቸጋሪ ነው። 24ደግሜ እላችኋለሁ፤ ሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።”

25ይህን ሲሰሙ፣ ደቀ መዛሙርቱ እጅግ በመገረም፣ “እንግዲያስ ማን ሊድን ይችላል?” ሲሉ ጠየቁ።

26ኢየሱስም እየተመለከታቸው፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉም ነገር ይቻላል” አላቸው።

27ጴጥሮስም መልሶ፣ “እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል፤ ታዲያ ምን እናገኝ ይሆን?” አለው።

28ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ በሚመጣው አዲስ ዓለም የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም የተከተላችሁኝ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ፣ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ ትፈርዳላችሁ። 29ስለ ስሜ ብሎ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን19፥29 አንዳንድ ቅጆች እናትን ወይም ሚስትን ይላሉ።፣ ልጆችን ወይም ዕርሻን የሚተው ሁሉ መቶ ዕጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። 30ነገር ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች፣ ብዙ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።