约书亚记 6 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约书亚记 6:1-27

耶利哥城塌陷

1耶利哥人害怕以色列人,就把所有的城门都关得紧紧的,无人出入。 2耶和华对约书亚说:“看啊,我已经把耶利哥耶利哥王及其英勇的战士都交在你手中了。 3你所有的军队要每天绕城一圈,连续六天, 4让七个祭司拿着七个羊角号走在约柜前面。到了第七天,你们要绕城七圈,祭司要吹响号角。 5当你们听到号角长鸣时,所有的人都要高声吶喊,城墙就会坍塌,众人便可以直冲上去。” 6的儿子约书亚便召来祭司,对他们说:“你们抬起约柜,派七位祭司拿着七个羊角号走在耶和华的约柜前面。” 7他又对民众说:“你们要前去绕着城墙走,军队要走在耶和华的约柜前面。”

8听完约书亚的吩咐,七个祭司便在耶和华面前拿着羊角号边走边吹,耶和华的约柜就跟在他们后面, 9军队走在吹号的祭司前面,殿后军队跟在约柜后面。祭司一路上吹着号角。 10约书亚吩咐民众:“在我下令叫你们吶喊以前,谁也不许作声,一句话也不许说。” 11这样,约书亚使耶和华的约柜绕城一圈,然后众人各自回营休息。

12第二天,约书亚一早起来,祭司又抬起耶和华的约柜。 13七个祭司拿着七个羊角号走在耶和华的约柜前面,一边走一边吹角。军队走在祭司前面,殿后军队跟在耶和华的约柜后面。 14这一天他们又绕城一圈,然后各自回营。六天都是这样。

15第七天黎明时分,他们起来照样绕城,只是这一天他们绕城走了七次。 16走到第七次,祭司吹响了号角,约书亚吩咐民众说:“吶喊吧!因为耶和华已经将这城交给你们了。 17要把这座城和城里所有的东西毁灭,作为献给耶和华之物。只有妓女喇合和她家中所有的人可以活命,因为她曾把我们派去的探子隐藏起来。 18你们要小心,不可私拿任何应当毁灭的东西,免得你们自取灭亡,并给以色列全营带来灾祸。 19要把所有的金银和铜铁器皿分别出来献给耶和华,放进耶和华的库房里。” 20于是,民众听到号角声时,就高声呐喊,城墙便坍塌了。民众便一拥而上,占领了耶利哥城, 21用刀杀了城里所有的男女老少、牛羊和驴。

22约书亚对那两个探子说:“你们到那个妓女家里,照着你们向她起过的誓,把她和她的家人都带出来。” 23于是,那两个年轻探子便进去,把喇合和她的父母、兄弟及所有的亲人都带出来,安置在以色列人的营外。 24以色列人烧毁全城和城内一切的东西,只把金银和铜铁器皿放在耶和华的库房里。 25约书亚因为妓女喇合把两个探子隐藏起来,就饶了她和她一家人的性命。他们至今仍住在以色列人当中。

26之后,约书亚起誓说:

“重建耶利哥城的人必定在耶和华面前受咒诅,

他立地基的时候必死长子,

建城门的时候必丧幼子。”

27耶和华与约书亚同在,他的声名传遍各地。

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 6:1-27

1በዚህ ጊዜ እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ፣ ኢያሪኮ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፤ ወደ ውጭ የሚወጣም ሆነ ወደ ውስጥ የሚገባ አልነበረም።

2እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ ኢያሪኮን ከንጉሥዋና ከተዋጊዎቿ ጋር አሳልፌ በእጅህ ሰጥቻለሁ። 3ከተማዪቱን ከተዋጊዎቻችሁ ጋር አንድ ጊዜ ዙሩ፤ ይህንም ስድስት ቀን አድርጉ። 4ሰባት ካህናት፣ ሰባት ቀንደ መለከት ተሸክመው በታቦቱ ፊት ይውጡ፤ በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ መለከት እየነፉ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ። 5የማያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በምትሰሙበት ጊዜ፣ ሕዝቡ ሁሉ ከፍ ያለ ጩኸት ያሰማ፤ ከዚያም የከተማዪቱ ቅጥር ይፈርሳል፤ ሕዝቡም ወደ ላይ ይወጣል፤ እያንዳንዱም ሰው በቀጥታ ይገባል።”

6ስለዚህ የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፣ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ሰባት ካህናትም ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው። 7ሕዝቡንም፣ “ወደ ፊት ሂዱ፤ ከተማዋን ዙሩ፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ” ሲል አዘዛቸው።

8ኢያሱም ለሕዝቡ ከተናገረ በኋላ፣ ሰባቱ ካህናት በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው መለከታቸውን እየነፉ ወደ ፊት ቀደሙ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦትም ተከተላቸው። 9የታጠቁ ተዋጊዎችም መለከት ከሚነፉት ካህናት ፊት ቀድመው ሲሄዱ፣ ደጀን የሆኑት ጠባቂዎች ደግሞ ታቦቱን ተከተሉ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ መለከቶቹ ባለማቋረጥ ይነፉ ነበር። 10ኢያሱ ሕዝቡን፣ “የማሸበሪያ ጩኸት አታሰሙ፤ ድምፃችሁ ከፍ ብሎ አይሰማ፤ ጩኹ እስከምላችሁም ቀን ድረስ ከአፋችሁ አንዲት ቃል አትውጣ፤ የምትጮኹት ከዚያ በኋላ ነው” ሲል አዘዛቸው።

11ስለዚህ ኢያሱ የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸክመው፣ ከተማዪቱን አንድ ጊዜ እንዲዞሩ አደረገ። ከዚያም ሕዝቡ ወደ ሰፈር ተመልሰው ዐደሩ።

12ኢያሱ በማግስቱም ማልዶ ተነሣ፤ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸከሙ። 13ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እየሄዱ፣ መለከቱን ባለማቋረጥ ይነፉ ጀመር፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም እነዚህን በመቅደም ሲሄዱ፣ የደጀን ጠባቂዎቹ ደግሞ የእግዚአብሔርን ታቦት ይከተሉ ነበር፤ ካህናቱም ሳያቋርጡ መለከት ይነፉ ነበር። 14በሁለተኛውም ቀን ከተማዪቱን አንድ ጊዜ ከዞሩ በኋላ ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀን ሙሉም እንዲሁ አደረጉ።

15በሰባተኛው ቀን ገና ጎሕ ሲቀድ ተነሡ፤ እንደ በፊቱም ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ የዞሯትም በዚያን ቀን ብቻ ነው። 16በሰባተኛው ዙር ላይ ካህናቱ መለከቱን ሲነፉ፣ ኢያሱ ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፤ “እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ሰጥቷችኋልና ጩኹ 17ከተማዪቱና በውስጧ ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ስለሆነ ፈጽማችሁ ዐጥፉ6፥17 የዕብራይስጡ ቃል አንድን ሰው ወይም ነገር ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው። እኛ የላክናቸውን ሰላዮች ስለ ሸሸገች ጋለሞታዪቱ6፥17 በዚህም ሆነ በቍጥር 22 እና 25 ላይ፣ የእንግዳ ማረፊያ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። ረዓብ ብቻና ከእርሷ ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉት ሁሉ ይትረፉ። 18እናንተ ግን ዕርም ከሆኑት ነገሮች አንዳች በመውሰድ በራሳችሁ ላይ ጥፋት እንዳታመጡ እጃችሁን ሰብስቡ፤ ያለዚያ የእስራኤልን ሰፈር ለጥፋት ትዳርጋላችሁ፤ ክፉ ነገር እንዲደርስበትም ታደርጋላችሁ፤ 19ብሩና ወርቁ እንዲሁም የናሱና የብረቱ ዕቃ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ስለሆነ፣ ወደ እግዚአብሔር ግምጃ ቤት ይግባ።”

20መለከቱ ሲነፋ ሕዝቡ ጮኸ፤ የመለከቱ ድምፅ ተሰምቶ፣ ሕዝቡ በኀይል ሲጮኽ ቅጥሩ ፈረሰ፤ እያንዳንዱም ሰው ሰተት ብሎ ገባ፤ ከተማዪቱም በእጃቸው ወደቀች። 21በከተማዪቱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፣ ማለትም ወንዱንና ሴቱን፣ ወጣቱንና ሽማግሌውን፣ ከብቱንና በጕን እንዲሁም አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።

22ኢያሱ ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች፣ “ወደ ጋለሞታዪቱ ቤት ሂዱ፤ በማላችሁላትም መሠረት እርሷንና የእርሷ የሆነውን ሁሉ ከዚያ አውጡ” አላቸው። 23ስለዚህ ሁለቱ ወጣት ሰላዮች ገብተው ረዓብን፣ አባቷንና እናቷን፣ ወንድሞቿንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ ከዚያ አወጧቸው። ቤተ ዘመዶቿንም ሁሉ አውጥተው ከእስራኤል ሰፈር ውጭ አስቀመጧቸው።

24ከዚያም ከተማዪቱን በሙሉ፣ በውስጧ ያለውንም ሁሉ አቃጠሉ፤ ብሩንና ወርቁን፣ የናሱንና የብረቱን ዕቃ ግን በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አኖሩ። 25ኢያሪኮን እንዲሰልሉ ኢያሱ የላካቸውን ሰዎች ስለ ደበቀች፣ ጋለሞታዪቱን ረዓብን፣ ቤተ ሰቧንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ አዳናቸው፤ እርሷም እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤላውያን መካከል ትኖራለች።

26በዚያን ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህችን ከተማ መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤

“መሠረቷን ሲጥል፣

የበኵር ልጁ ይጥፋ፤

ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣

የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ”

ብሎ ማለ።

27ስለዚህ እግዚአብሔር ከኢያሱ ጋር ነበር፤ ዝናውም በምድሪቱ ሁሉ ላይ ወጣ።