撒迦利亚书 5 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

撒迦利亚书 5:1-11

飞行的书卷

1我又举目观看,见有书卷在飞。 2天使问我:“你看见什么?”我说:“我看见飞行的书卷,长十米,宽五米。” 3他说:“这是临到全天下的咒诅,因为书卷一面写着‘凡偷盗的必被清除’,另一面写着‘凡起假誓的必被清除’。” 4万军之耶和华说:“我要使这咒诅进入盗贼和奉我的名起假誓者的家,住在他们家里,毁灭他们的家,不留一木一石。”

量器中的女子

5与我说话的天使又来对我说:“你举目观看,看看出现了什么?” 6我问道:“这是什么?”他说:“这是一个量器。”接着他又说:“里面盛着世人的罪。” 7只见量器的铅盖打开了,里面坐着一个女子。 8天使说:“这是罪恶。”他把女子推回量器中,盖上铅盖。 9我又举目观看,见有两个女子展翅飞来,她们的翅膀像鹳鸟的翅膀。她们把量器提到空中。 10我问与我说话的天使:“她们要把量器带到哪里?” 11他说:“要带到示拿5:11 示拿”巴比伦的别名。,在那里为它建造房屋,建好后就把它安置在底座上。”

New Amharic Standard Version

ዘካርያስ 5:1-11

በራሪው የመጽሐፍ ጥቅልል

1እንደ ገናም ተመለከትሁ፤ በዚያም በፊቴ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ።

2እርሱም፣ “ምን ታያለህ?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም፣ “ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ5፥2 ዕብራይስጡ፣ ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ 10 ክንድ ወይም ርዝማኔው ዘጠኝ ሜትር፣ ስፋቱ አራት ተኩል ሜትር ይሆናል። ዐሥር ክንድ የሆነ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አያለሁ” አልሁት። 3እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ በምድር ሁሉ ላይ የሚወጣ ርግማን ነው፤ በአንደኛው በኩል እንደ ተጻፈው የሚሰርቅ ሁሉ ይጠፋል፤ በሌላው በኩል ደግሞ እንደ ተጻፈው በሐሰት የሚምል ሁሉ ይጠፋልና። 4እግዚአብሔር ጸባኦት ‘እኔ ርግማኑን አመጣዋለሁ፤ እርሱም ወደ ሌባው ቤትና በስሜ በሐሰት ወደሚምለው ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ይቀመጣል፤ ቤቱን፣ ዕንጨቱንና ድንጋዩን ያጠፋል’ ይላል።”

በቅርጫት ውስጥ ያለች ሴት

5ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደ ላይ ተመልከት፤ ይህ የሚመጣው ምን እንደ ሆነ እይ” አለኝ።

6እኔም፣ “ምንድን ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢፍ መስፈሪያ5፥6 ከ7-11 ካለው ጭምር፣ የእህል መስፈሪያ ወይም ቍና ማለት ነው። ነው” አለኝ። ቀጥሎም “ይህ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ያለው የሕዝቡ በደል5፥6 ወይም መምሰል ማለት ሊሆን ይችላል። ነው” አለኝ።

7ከዚያም ከእርሳስ የተሠራው ክዳን ተነሣ፤ የኢፍ መስፈሪያ ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። 8እርሱም፣ “ይህች ርኩሰት ናት” ብሎ ወደ ኢፍ መስፈሪያ መልሶ አስገባት፤ የእርሳሱንም ክዳን ወደ ቅርጫቱ አፍ ገፍቶ ገጠመው።

9ከዚያም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ከፊቴ ሁለት ሴቶች ነበሩ፤ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበር፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።

10ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውንም መልአክ፣ “ቅርጫቱን የሚወስዱት ወዴት ነው?” አልሁት።

11እርሱም፣ “ቤት ሊሠሩለት ወደ ባቢሎን5፥11 ዕብራይስጡ ሺናር ይለዋል። ምድር ይወስዱታል፤ በተዘጋጀም ጊዜ ወስደው በቦታው ያስቀምጡታል” አለኝ።