尼希米记 3 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

尼希米记 3:1-32

重建耶路撒冷的城墙

1于是,大祭司以利亚实及其他祭司一起重建羊门,将它献给上帝,又安上门。他们重建城墙,一直建到哈米亚楼和哈楠业楼,并将它献给上帝。

2下一段由耶利哥人修建。

再下一段由音利的儿子撒刻修建。

3哈西拿的子孙修建鱼门,架上横梁,安上门,装上门闩和门锁。

4再下一段由哈哥斯的孙子、乌利亚的儿子米利末修筑。

再下一段由米示萨别的孙子、比利迦的儿子米书兰修筑。

再下一段由巴拿的儿子撒督修筑。

5再下一段由提哥亚人修筑,但他们的贵族不肯做督工所分派的工作。

6巴西亚的儿子耶何耶大比所玳的儿子米书兰修筑古门,架上横梁,安上门,装上门闩和门锁。

7再下一段由基遍米拉提米伦雅顿和其他基遍人,以及河西省省长管辖的米斯巴人修筑。

8再下一段由哈海雅的儿子金匠乌薛修筑。

再下一段由制造香料的哈拿尼雅修筑,他们修筑耶路撒冷的城墙,直到宽墙。

9再下一段由管理半个耶路撒冷户珥的儿子利法雅修筑。

10接下来,哈路抹的儿子耶大雅修筑他房子对面的那一段。

再下一段由哈沙尼的儿子哈突修筑。

11哈琳的儿子玛基雅巴哈·摩押的儿子哈述修筑另一段城墙,包括炉楼。

12再下一段由哈罗黑的儿子、管理另一半耶路撒冷沙龙和他的女儿们修筑。

13哈嫩撒挪亚的居民修筑谷门,安上门,装上门闩和门锁,之后又修建城墙四百四十五米,直到粪厂门。

14利甲的儿子、管理伯·哈基琳玛基雅修筑粪厂门,修好后安上门,装上门闩和门锁。

15各荷西的儿子、管理米斯巴沙仑修筑泉门,修好后盖上门顶,安上门,装上门闩和门锁。他还从靠近御花园的西罗亚池的城墙,一直修到大卫城下来的台阶处。

16再下一段由押卜的儿子、管理半个伯·夙尼希米修筑,他一直修到大卫墓地对面,远至人工池和勇士堂。

修筑城墙的利未人

17再下一段由巴尼的儿子利宏带领的利未人修筑。

接下来,管理半个基伊拉哈沙比雅修筑了自己的辖区。

18再下一段由他的同族兄弟、管理另一半基伊拉希拿达的儿子巴瓦伊修筑。

19再下一段由耶书亚的儿子、管理米斯巴以谢修筑,他从斜坡对面修到城墙转角的兵器库。

20再下一段由萨拜的儿子巴录修筑,他从城墙转角修到以利亚实大祭司的家门口。

21再下一段由哈哥斯的孙子、乌利亚的儿子米利末修筑,他从以利亚实家门口修到以利亚实家的尽头。

修筑城墙的祭司

22再下一段由住在周围郊区的祭司修筑。

23接下来,便雅悯哈述修筑自家对面的那一段。

再接下来,亚南尼的孙子、玛西雅的儿子亚撒利雅修筑自家旁边的那一段。

24再下一段由希拿达的儿子宾内修筑,他从亚撒利雅的房子修到城墙的转角。

25-26再接下来,乌赛的儿子巴拉修筑了城墙转角的对面和护卫院附近上宫凸出的城楼。

再下一段由巴录的儿子毗大雅与住在俄斐勒的殿役修筑,他们修到东面的水门对面和凸出的城楼那里。

其他修筑的人

27再下一段由提哥亚人修筑,他们从凸出来的大城楼对面修到俄斐勒的城墙。

28接下来,祭司修筑了马门以北的城墙,他们各自修筑自家对面的部分。

29再接下来,音麦的儿子撒督修筑自家对面的那一段。

再下一段由看守东门的、示迦尼的儿子示玛雅修筑。

30再下一段由示利米雅的儿子哈拿尼雅萨拉的第六个儿子哈嫩修筑。

接下来,比利迦的儿子米书兰修筑自家对面的那一段。

31再下一段由金匠玛基雅修筑,他修到哈米弗甲门对面的殿役和商人的房子,直到城的角楼。

32金匠和商人修筑从城的角楼到羊门的那一段。

New Amharic Standard Version

ነህምያ 3:1-32

የቅጥሩ ሠራተኞች

1ሊቀ ካህናቱ ኤልያሴብና ወንድሞቹ ካህናት ለሥራ ተነሡ፤ የበጎች በር የተባለውንም እንደ ገና ሠሩ። ቀደሱት፤ መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ላይ አቆሙ። መቶ ማማ እስከሚባለው ግንብና ሐናንኤል ማማ ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ሠርተው ቀደሱት፤ 2ቀጥሎ ያለውንም የኢያሪኮ ሰዎች ሠሩ፤ እነርሱ ከሠሩት ቀጥሎ ደግሞ የአምሪ ልጅ ዘኩር ሠራ።

3የዓሣ በሩን የሃስናአ ልጆች ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።

4የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። ከእርሱ ቀጥሎ ያለውን የሜሴዜቤል ልጅ የበራክያ ልጅ ሜሱላም መልሶ ሠራ። ከእርሱ ቀጥሎ ያለውን የበዓና ልጅ ሳዶቅ መልሶ ሠራ፤ 5የሚቀጥለውን ክፍል የቴቁሐ ሰዎች መልሰው ሠሩ፤ መኳንንቶቻቸው ግን በተቈጣጣሪ አሠሪዎቻቸው3፥5 ጌቶቻቸው፤ ወይም ገዦቻቸው ሥር ሆነው በሥራው መጠመድ አልፈለጉም።

6አሮጌውን3፥6 ወይም የይሻናን በር የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም መልሰው ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ ማያያዣዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ። 7ከእነርሱም ቀጥሎ የዕድሳቱ ሥራ የተከናወነው በኤፍራጥስ ማዶ በሚገኘው አገረ ገዥ ሥልጣን ሥር ባሉት በገባዖንና በምጽጳ ሰዎች በገባዖናዊው በመልጥያና በሜሮኖታዊው በያዶን ነበር። 8ከወርቅ አንጥረኞች አንዱ የሆነው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል የሚቀጥለውን ክፍል ሠራ፤ ከሽቱ ቀማሚዎች አንዱ የሆነው ሐናንያ ደግሞ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን መልሶ ሠራ። እነርሱም “ሰፊው ቅጥር” ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ኢየሩሳሌምን መልሰው ሠሩ። 9ከዚያ የሚቀጥለውን ክፍል የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዥ የሆነው የሆር ልጅ ረፋያ መልሶ ሠራ። 10የኤርማፍ ልጅ ይዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ፤ የአሰበንያ ልጅ ሐጡስ ደግሞ ከእርሱ ቀጥሎ ያለውን መልሶ ሠራ። 11የካሪም ልጅ መልክያና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ ሌላውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሠሩ። 12የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዥ የሆነው የአሎኤስ ልጅ ሰሎም ከሴት ልጆቹ ጋር በመሆን ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ።

13“የሸለቆ በር” ተብሎ የሚጠራውን የሐኖንና የዛኖ ነዋሪዎች ዐደሱት፤ መልሰው ሠሩት፤ ከሠሩትም በኋላ መዝጊያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ፤ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹንም አበጁ። እንዲሁም “የቈሻሻ መጣያ በር” ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን አንድ ሺሕ ክንድ3፥13 450 ሜትር ያህል ነው። ቅጥር መልሰው ሠሩ።

14“የቈሻሻ መጣያ በር” ተብሎ የሚጠራው የቤት ሐካሪም አውራጃ ገዥ የሆነው የሬካብ ልጅ መልክያ መልሶ ሠራ፤ መልሶ ከሠራ በኋላም መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖረ።

15የምጽጳ አውራጃ የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም “የምንጭ በር” ተብሎ የሚጠራውን መልሶ ሠራ፤ መልሶ ከሠራም በኋላ ከድኖ መዝጊያዎቹን በየቦታቸው አኖረ፤ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹንም አበጀ። “የንጉሥ አትክልት ቦታ” ተብሎ በሚጠራው አጠገብ የሚገኘውን የሼላን መዋኛ ግንብም፣ ከዳዊት ከተማ ጀምሮ ቍልቍል እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ መልሶ ሠራ። 16ከእርሱም በኋላ የቤት ጹር አውራጃ እኩሌታ ገዥ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር ትይዩ እስከ ሰው ሠራሹ ኵሬና “የጀግኖች ቤት” ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን መልሶ ሠራ።

17ከእርሱ ቀጥሎ ሌዋውያኑ በባኒ ልጅ በሬሁ ሥር ሆነው የዕድሳት ሥራ ሠሩ። ከእርሱ ቀጥሎ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ ሐሸብያ አውራጃውን መልሶ ሠራ። 18ከእርሱ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ደግሞ የሌላው የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና በእርሱም ሥር የነበሩት የአገሩ ሰዎች መልሰው ሠሩ። 19ከእርሱም ቀጥሎ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በሚያወጣውና እስከ ማእዘኑ በሚደርሰው ትይዩ ያለውን ሌላ ክፍል የምጽጳ ገዥ የኢያሱ ልጅ ኤጽር መልሶ ሠራ። 20ከእርሱም ቀጥሎ የዘባይ ልጅ ባሮክ ከማእዘኑ ጀምሮ እስከ ሊቀ ካህኑ እስከ ኤልያሴብ ቤት መግቢያ ያለውን ሌላ ክፍል በትጋት መልሶ ሠራ። 21ከእርሱ ቀጥሎ ከኤልያሴብ ቤት መግቢያ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ያለውን ሌላ ክፍል የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት መልሶ ሠራ።

22ከእርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ከአካባቢው የመጡት ካህናት መልሰው ሠሩ። 23ከእነርሱ ቀጥሎ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መልሰው ሠሩ፤ ከእነርሱም ቀጥሎ የሐናንያ ልጅ የመዕሤያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን መልሶ ሠራ። 24ከእርሱም ቀጥሎ ከዓዛርያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማእዘኑና እስከ ማእዘኑም ጫፍ ያለውን ሌላውን ክፍል የኤንሐደድ ልጅ ቢንዊ መልሶ ሠራ፤ 25የኡዛይ ልጅ ፋላል ከቅጥሩ ማእዘን ትይዩና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ካለው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን መልሶ ሠራ። ከእርሱም ቀጥሎ የፋሮስ ልጅ ፈዳያና 26በዖፌል ኰረብታ ላይ የሚኖሩት የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች “የውሃ በር” ተብሎ ከሚጠራው ትይዩ ጀምሮ በስተ ምሥራቅ እስከሚገኘው ግንብ ድረስ መልሰው ሠሩ። 27ከእነርሱ ቀጥሎ የቴቁሐ ሰዎች ከታላቁ ግንብ ትይዩ ጀምሮ እስከ ዖፌል ቅጥር ድረስ ያለውን ሌላ ክፍል መልሰው ሠሩ።

28“የፈረስ በር” ተብሎ ከሚጠራው በላይ ያለውን ደግሞ ካህናቱ እያንዳንዳቸው በየመኖሪያ ቤታቸው ትይዩ ያለውን መልሰው ሠሩ። 29ከእነርሱም ቀጥሎ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ። ከእርሱ ቀጥሎ ያለውን “የምሥራቅ በር” ጠባቂ የሆነው የሴኬንያ ልጅ ሸማያ መልሶ ሠራ። 30ከእርሱ ቀጥሎ ያለውን ሌላ ክፍል ደግሞ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኖን መልሰው ሠሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የበራክያ ልጅ ሜሱላም ከመኖሪያው ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ። 31ከእርሱ ቀጥሎ ከወርቅ አንጥረኞች አንዱ መልክያ በመቈጣጠሪያው በር ትይዩ እስከሚገኘው እስከ ቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና እስከ ነጋዴዎቹ ቤት፣ እንዲሁም ከማእዘኑ በላይ እስከሚገኘው ክፍል ያለውን መልሶ ሠራ፤ 32ከማእዘኑ በላይ ከሚገኘው ክፍል ጀምሮ እስከ በጎች በር ያለውን ደግሞ ወርቅ አንጥረኞቹና ነጋዴዎቹ መልሰው ሠሩ።