历代志下 3 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志下 3:1-17

建造圣殿

1所罗门耶路撒冷摩利亚山上动工兴建耶和华的殿,殿址在耶布斯阿珥楠的麦场,就是大卫指定的地方。耶和华曾在那里向他父亲大卫显现。 2所罗门在执政第四年二月二日动工建殿。 3按照古时的尺度,他建造的上帝殿宇的地基长二十七米,宽九米。 4殿前的门廊长九米,与殿的宽度一样,高九米3:4 高九米”希伯来文是“高五十四米”。,里面都贴上纯金。 5大殿里镶上松木板,贴上纯金,又刻上棕树和链子。 6所罗门用宝石和巴瓦音的纯金装饰殿。 7殿的栋梁、墙壁、门槛和门扇也都贴上金子;墙上还刻上基路伯天使。

8所罗门又动工建造至圣所,长九米,宽九米,与殿的宽度一样,里面共贴了二十一吨纯金。 9所用的金钉重六百克。楼房也都贴上了金子。 10他又在至圣所制造两个基路伯天使的翅膀,包上金子。 11-13两个基路伯天使的翅膀共九米长,每个翅膀长二点二五米。两个基路伯天使面向大殿站立,他们展开的翅膀共九米长,各有一个翅膀触到殿墙,一个翅膀互相连接。 14他用蓝色、紫色和朱红色的线以及细麻织成幔子,并在上面绣上基路伯天使。

15所罗门在殿前造了两根柱子,每根高八米,上面的柱冠高二点二五米。 16他也造了链子3:16 他也造了链子”希伯来文是“他在圣所内造了链子”。,装饰在柱冠上。他又造了一百个石榴,安在链子上。 17这两根柱子一左一右立在殿的入口处,他给右边那根取名叫雅斤,给左边那根取名叫波阿斯

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 3:1-17

ሰሎሞን ቤተ መቅደስ ሠራ

3፥1-14 ተጓ ምብ – 1ነገ 6፥1-29

1ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ዳዊት ባዘጋጀው ቦታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ። 2በነገሠም በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመረ።

3ሰሎሞን ለመቅደሱ ሕንጻ የጣለው መሠረት በቀድሞው ስፍር ልክ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ3፥3 ርዝመቱ 27 ሜትር ወርዱ 9 ሜትር ያህል ነው። ነበር። 4በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ላይ ያለው በረንዳ3፥4 በዚህና በቍጥር 8፡11 እንዲሁም 13 ላይ 9 ሜትር ያህል ነው። ርዝመቱ በቤተ መቅደሱ ወርድ ልክ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ከፍታውም ሃያ3፥4 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን አንድ መቶ ሃያ ይላል። ክንድ ነበር። ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው። 5የቤተ መቅደሱን ዋና ክፍል በጥድ ዕንጨት አልብሶ በተጣራ ወርቅ ለበጠው፤ የዘንባባና የሰንሰለት አምሳልም ቀረጸበት። 6ቤተ መቅደሱን በከበረ ድንጋይ አስጌጠው፤ የተጠቀመበትም ወርቅ የፈርዋይም ወርቅ ነበር። 7የጣራውን ተሸካሚዎች፣ መቃኖችን፣ የቤተ መቅደሱን ግድግዳና መዝጊያዎች በወርቅ ለበጠ፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቤልን ምስል ቀረጸ።

8እንደዚሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ሠራ፤ ርዝመቱ ከቤተ መቅደሱ ወርድ ጋር እኩል ሲሆን፣ ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ስፋቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡንም በስድስት መቶ3፥8 21 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። መክሊት የተጣራ ወርቅ ለበጠው። 9የወርቅ ምስማሮቹም አምሳ3፥9 0.6 ኪሎ ግራም ያህል ነው። ሰቅል ይመዝኑ ነበር፤ የላይኛውንም ክፍሎች እንደዚሁ በወርቅ ለበጠ።

10በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሁለት ኪሩቤል ምስል አስቀርጾ በወርቅ ለበጣቸው። 11ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ3፥11 በዚህና በቍጥር 15 ላይ 2.3 ሜትር ያህል ነው። ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው አምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 12እንደዚሁም የሁለተኛው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሆኖ በአንጻሩ ያለውን የቤተ መቅደስ ግድግዳ ሲነካ፣ አምስት ክንድ የሆነው ሌላው ክንፉ ደግሞ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። 13የተዘረጋው የእነዚህ ኪሩቤል ክንፍ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል አዙረው3፥13 ወይም፣ ወደ ቤተ መቅደሱ እያዩ ተብሎ መተርጐም ይቻላል በእግራቸው ቆመዋል።

14ደግሞም ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከደማቅ ቀይ ፈትልና ከቀጭን በፍታ መጋረጃ ሠርቶ፣ የኪሩቤልን ምስል በጥልፍ ጠለፈበት።

15በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በአንድነት ቁመቱ ሠላሳ አምስት ክንድ3፥15 16 ሜትር ያህል ነው። የሆነ፣ በእያንዳንዱም ላይ አምስት ክንድ ጕልላት ያለው ሁለት ዐምድ ሠራ። 16እርስ በርሳቸው የተጠላለፉ ሰንሰለቶች ሠርቶ3፥16 ወይም፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሰንሰለት ሠርቶ ተብሎ መተርጐም ይችላል፤ በዕብራይስጡ የዚህ ሐረግ ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ከዐምዶቹ ጫፍ ጋር አገናኛቸው፤ ከዚያም መቶ የሮማን ፍሬዎች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አያያዛቸው።

17ዐምዶቹንም አንዱን በደቡብ፣ ሌላውን በሰሜን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በደቡብ በኩል ያለውን፣ “ያኪን”፣3፥17 ምናልባት ያኪን ማለት፣ እርሱ አነጻ ማለት ሊሆን ይችላል። በሰሜን በኩል ያለውንም፣ “ቦዔዝ”3፥17 ምናልባት ቦዔዝ ማለት ብርታት በእርሱ ውስጥ ነው ማለት ሊሆን ይችላል። ብሎ ጠራቸው።