创世记 8 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

创世记 8:1-22

洪水消退

1上帝眷顾挪亚及方舟里的野兽和牲畜,使风吹在大地上,水便开始消退。 2深渊的泉源和天上的水闸都关闭了,大雨也停了。 3地上的洪水慢慢消退,过了一百五十天,水退下去了。 4七月十七日,方舟停在亚拉腊山上。 5水继续消退,到十月一日,山顶都露出来了。

6又过了四十天,挪亚打开方舟的窗户, 7放出一只乌鸦。它一直在空中飞来飞去,直到地上的水都干了。 8后来,挪亚放出一只鸽子,以便了解地面的水是否已经消退。 9但遍地都是水,鸽子找不到歇脚的地方,就飞回了方舟,挪亚伸手把鸽子接进方舟里。 10过了七天,挪亚再把鸽子放出去。 11到了黄昏,鸽子飞回来,嘴里衔着一片新拧下来的橄榄叶,挪亚便知道地上的水已经退了。 12等了七天,他又放出鸽子,这一次,鸽子没有回来。

13挪亚六百零一岁那年的一月一日,地上的水干了。挪亚打开方舟的盖观望,看见地面都干了。 14到了二月二十七日,大地完全干了。 15上帝对挪亚说: 16“你与妻子、儿子和儿媳可以出方舟了。 17你要把方舟里的飞禽走兽及爬虫等所有动物都带出来,让它们在地上多多繁殖。” 18于是,挪亚与妻子、儿子和儿媳都出了方舟。 19方舟里的飞禽走兽和爬虫等所有地上的动物,都按种类出了方舟。

挪亚献祭

20挪亚为耶和华筑了一座坛,在上面焚烧各种洁净的牲畜和飞鸟作为燔祭。 21耶和华闻到这燔祭的馨香,心想:“虽然人从小就心存恶念,但我再不会因为人的缘故而咒诅大地,再不会毁灭一切生灵。 22只要大地尚存,播种收割、夏热冬寒、白昼黑夜必永不停息。”

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 8:1-22

1እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅንና በመርከቧ ውስጥ ከእርሱ ጋር የነበሩትን የዱርና የቤት እንስሳት ሁሉ ዐሰበ፤ በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም ጐደለ። 2የጥልቁ ምንጮችና የሰማይ ውሃ መስኮቶች ተዘጉ፤ ዝናቡም መዝነቡን አቆመ። 3ውሃው ከምድር ላይ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ፤ ከመቶ አምሳ ቀን በኋላም ጐደለ። 4በሰባተኛው ወር፣ በዐሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቧ በአራራት ተራሮች ላይ ዐረፈች። 5ውሃው እስከ ዐሥረኛው ወር ድረስ እየቀነሰ መጣ፤ በዐሥረኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የተራሮቹ ጫፎች ታዩ።

6ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቧን መስኮት ከፍቶ፣ 7ቍራን ወደ ውጭ ላከ፤ ቍራውም ውሃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። 8ከዚያም በኋላ፣ ኖኅ ውሃው ከምድር ገጽ ጐድሎ እንደ ሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤ 9ነገር ግን ውሃው የምድርን ገጽ ገና እንደ ሸፈነ ስለ ነበር፣ ተመልሳ ኖኅ ወዳለበት መርከብ መጣች፤ እርሱም እጁን ዘርግቶ ተቀበላት፤ ወደ መርከቢቱም አስገባት። 10ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደ ገና ላካት። 11እርሷም ወደ ማታ ተመለሰች፤ እነሆም የለመለመ የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ነበር፤ ያን ጊዜ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጕደሉን ዐወቀ። 12ሰባት ቀንም ቈይቶ ርግቧን እንደ ገና ላካት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቧ ወደ እርሱ አልተመለሰችም።

13ኖኅ በተወለደ በ 601 ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ። 14ኖኅ በመርከቡ ላይ ያለውን ክዳን አንሥቶ ተመለከተ፤ የመሬቱም ገጽ እንደ ደረቀ አየ። በሁለተኛው ወር፣ በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች።

15ከዚያም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅን እንዲህ አለው፤ 16“አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቧ ውጡ። 17እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲበዙ፣ ከአንተ ጋር ያሉትን እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ይዘሃቸው ውጣ።”

18ኖኅም ከልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር ወጣ። 19እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር የሚንቀሳቀሱ ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ።

20ከዚያም ኖኅ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያው ላይ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ፣ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት ወፎች የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤ 21እግዚአብሔርም (ያህዌ) ደስ የሚያሰኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም8፥21 ወይም ስለሆነ በእርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጡራንን ዳግመኛ አላጠፋም።

22“ምድር እስካለች ድረስ፣

የዘር ወቅትና መከር፣

ሙቀትና ቅዝቃዜ

በጋና ክረምት፣

ቀንና ሌሊት፣

አይቋረጡም።”