出埃及记 28 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

出埃及记 28:1-43

祭司圣衣的规定

1“你要从以色列百姓当中把你的哥哥亚伦和他四个儿子——拿答亚比户以利亚撒以他玛带到你身边,立他们为祭司事奉我。 2你要为你哥哥亚伦做一件圣衣,显出他职位的荣耀和尊贵。 3你要吩咐所有我赋予智慧的巧手裁缝师为亚伦缝制衣服,使他分别出来,做圣洁的祭司事奉我。 4他们要做的圣衣包括胸牌、以弗得、外袍、杂色的内袍、礼冠和腰带。要为你哥哥亚伦及其众子做这样的圣衣,好让他们做祭司事奉我。 5要用金线和细麻线及蓝色、紫色、朱红色的线制作圣衣。

以弗得

6“以弗得要用金线和细麻线及蓝色、紫色、朱红色的线精工制作。 7要在以弗得两边用两条肩带缝合起来。 8用金线和细麻线及蓝色、紫色、朱红色的线精工制作一条带子,缝在以弗得上,连成一整件。

9“你要找两块红玛瑙,刻上以色列十二个儿子的名字, 10按他们的长幼次序,每一块宝石刻上六个名字。 11要用工匠雕刻图章的方法将他们的名字刻在两块宝石上,把宝石镶在两个金框里面。 12然后将镶着金框的宝石缝在以弗得的两条肩带上,作以色列人的纪念石。亚伦要把他们的名字放在肩上,在耶和华面前作纪念。 13要做两个金框, 14并像搓绳子一样用纯金搓成两条金链,把链子连接在镶宝石的金框上。

胸牌

15“要精心制作一个用来明白上帝旨意的胸牌,制作的方法和造以弗得一样,用金线和细麻线及蓝色、紫色、朱红色的线制作。 16胸牌是方形的,长宽各二十二厘米,分成上下两层。 17上面要镶上四行宝石:第一行是红宝石、黄玉和翠玉; 18第二行是绿宝石、蓝宝石和金刚石; 19第三行是紫玛瑙、白玛瑙和紫晶; 20第四行是水苍玉、红玛瑙和碧玉。这些宝石都要用金框围着,镶在胸牌上。 21要用刻图章的方法在每一颗宝石上刻一个以色列儿子的名字,十二颗宝石代表十二支派。

22“要用纯金拧成两条像绳子一样的链子,连在胸牌上, 23造两个金环安在胸牌两端, 24把链子穿在金环上, 25再把金链的另一端接在以弗得肩带的两个金框上。 26造两个金环,安在胸牌下端靠近以弗得内侧的两边。 27再造两个金环安在以弗得前面两条肩带的下端,靠近接缝处,在精致的以弗得腰带上方。 28再用一条蓝色的绳子系住以弗得和胸牌上面的金环,使胸牌贴在精工织成的以弗得腰带上,不会从以弗得上松脱。 29亚伦进圣所时,要佩戴这块刻着以色列众子名字的胸牌,在耶和华面前常作纪念。 30又要把乌陵和土明放在胸牌里面,亚伦到耶和华面前的时候,要佩带这胸牌,以便明白上帝的旨意,为以色列人做决定。

外袍

31“也要缝制一件蓝色的以弗得的外袍, 32袍上要留领口,还要在领口周围织领边,好像铠甲上的领口,免得领口破裂。 33外袍的底边要另外用蓝色、紫色、朱红色的线做成石榴状的饰物,石榴中间要挂金铃铛。 34一个石榴一个金铃铛,相间排列,围在外袍的底边。 35亚伦事奉的时候,要穿上这外袍,以便他进圣所到耶和华面前和出圣所的时候,铃铛会发出响声,他就不至于死。

36“你也要用纯金造一块牌子,以刻印章的方法刻上‘奉献给耶和华’的字样, 37再拿一条蓝色带子,把它系在礼冠前面。 38亚伦要把这金牌戴在额上,表示他承担以色列人献圣物时的过犯,这圣物是以色列百姓特别献上的礼物。这金牌要常常留在亚伦的额上,好使百姓蒙耶和华悦纳。

39“要用杂色的细麻线织成祭司的内袍,用细麻布做礼冠,腰带上要有刺绣, 40也要为亚伦的儿子们缝制内袍、腰带、帽子,显出他们职位的荣耀和尊贵。 41你哥哥亚伦及其众子穿上这些衣服后,你要用油膏立他们,使他们分别出来,做圣洁的祭司事奉我。

裤子

42“要用细麻布为他们做裤子,以遮盖下体,裤子要从腰部到大腿。 43亚伦父子们进出会幕或到圣所的祭坛事奉的时候,都要穿上裤子,免得因为触犯圣礼而死亡。这是亚伦及其子孙永远当遵守的条例。

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 28:1-43

ልብሰ ተክህኖ

1“ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ከእስራኤላውያን መካከል ወንድምህ አሮንን ከወንዶች ልጆቹ ከናዳብ፣ ከአብዩድ፣ ከአልዓዛርና ከኢታምር ጋር ወደ አንተ አቅርባቸው። 2ለእርሱም ማዕረግና ክብር ለመስጠት ለወንድምህ ለአሮን የተቀደሱ መጐናጸፊያዎችን አብጅለት። 3ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ የተለየ ይሆን ዘንድ ጥበብ ለሰጠኋቸው በዚህ ጕዳይ ላይ ጥበበኛ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ለአሮን መጐናጸፊያዎችን እንዲሠሩለት ንገራቸው። 4የሚሠሯቸው መጐናጸፊያዎች የደረት ልብስ ኤፉድ ቀሚስ፣ ጥልፍ ሸሚዝ፣ ጥምጥምና መታጠቂያ ናቸው፤ ካህን ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ የተቀደሱ መጐናጸፊያዎችን ለአሮንና ለወንድ ልጆቹ ይሠራሉ። 5ወርቅ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና እንዲሁም ቀጭን በፍታ ይጠቀሙ።

ኤፉድ

28፥6-14 ተጓ ምብ – ዘፀ 39፥2-7

6“የጥልፍ ዐዋቂዎች ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ ይሥሩት። 7መተሳሰር እንዲችል ሆኖ፣ ዳርና ዳር ከሚገኙት ከሁለቱ ጐኖች ጋር የተያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት። 8በጥበብ የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ከኤፉድ ጋር አንድ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።

9“ሁለት የመረግድ ድንጋዮች ውሰድና የእስራኤልን ልጆች ስሞቻቸውን ቅረጽባቸው። 10እንደ ልደታቸው ቅደም ተከተል ስድስቱን ስሞች በአንዱ ድንጋይ ላይ የቀሩትንም ስሞች በሌላው ላይ ቅረጽባቸው። 11የቅርጽ ሠራተኛ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ፤ ከዚያም ድንጋዮቹን በወርቅ ፈርጥ ክፈፋቸው፤ 12ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ በኤፉዱ ትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ጋር አያይዛቸው፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቹን በትከሻው ላይ ይሸከማቸው። 13የወርቅ ፈርጦችን አብጅ፤ 14እንደ ገመድ ያሉ ሁለት በንጹሕ ወርቅ የተጐነጐኑ ድሪዎችን አብጅተህ ከፈርጡ ጋር አያይዛቸው።

የደረት ኪስ

28፥15-28 ተጓ ምብ – ዘፀ 39፥8-21

15“የፍርድ መስጫውን የደረት ኪስ ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው አድርገህ አብጀው፤ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ አብጀው። 16ርዝመቱ አንድ ስንዝር፣ ስፋቱ አንድ ስንዝር28፥16 ወደ 22 ሴንቲ ሜትር ያህል ነው። ሆኖ ባለ አራት ማእዘንና በድርቡ የታጠፈ ይሁን። 17ከዚያም በላዩ ላይ በአራት ረድፍ የከበሩ ድንጋዮች አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርዲዮን፣ ቶጳዝዮን፣ የሚያበረቀርቅ ዕንቍ፤ 18በሁለተኛውም ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር28፥18 ወይም፣ ላፒስ ላዙሊ፣ አልማዝ፤ 19በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤ 20በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ28፥20 የእነዚህ የከበሩ ማዕድኖች ትክክለኛ ማንነት በትክክል አይታወቅም። አድርግበት፤ በወርቅ ፈርጥም ክፈፋቸው። 21የዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስሞች እንደ ማኅተም የተቀረጸባቸው ለእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ይሁኑ።

22“ለደረት ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ ሆኖ የተጌጠ ጕንጕን አብጅለት። 23ለእርሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አብጅተህ ከደረት ኪሱ ሁለት ጐኖች ጋር አያይዘው። 24ሁለቱን የወርቅ ጕንጕኖች በደረት ኪሱ ጐኖች ላይ ካሉት ቀለበቶች ጋር አያይዛቸው። 25ሌሎቹን የጕንጕን ጫፎች በፊት ላይ ካለው ኤፉድ በትከሻው ላይ ካሉት ንጣዮች ጋር በማጋጠም ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋር አያይዛቸው። 26ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አበጅተህ ከኤፉዱ ቀጥሎ ባለው በውስጠኛ ጠርዝ ላይ፣ በሌላ በኩል ካሉት ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋር አያይዛቸው። 27ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶች አበጅተህ ከኤፉዱ መታጠቂያ ከፍ ብሎ ከመጋጠሚያው አጠገብ ካለው በኤፉዱ ፊት ለፊት፣ በትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ግርጌ ጋር አያይዘው። 28የደረት ኪሱም ቀለበቶች፣ የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋር እንዳይላቀቅ፣ ከመታጠቂያው ጋር በማገናኘት በሰማያዊ ገመድ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር ይያያዙ።

29“አሮን ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም። 30ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በሚገባበት ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆኑ ዘንድ ኡሪሙንና ቱሚሙን በደረት ኪሱ አድርግ፤ ስለዚህ አሮን ሁልጊዜ ለእስራኤላውያን የፍርድ መስጫውን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በልቡ ላይ ይሸከማል።

ሌሎቹ አልባሳት

28፥31-43 ተጓ ምብ – ዘፀ 39፥22-31

31“የኤፉዱ ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ጨርቅ ይሁን፤ 32ከላይ በኩል በመካከሉ ዐንገትጌ አድርገህ አብጀው፤ እንዳይቀደድም በማስገቢያው ዙሪያ እንደ ክሳድ ያለ ዝምዝም ጠርዝ28፥32 በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትክክለኛ ፍችው አይታወቅም። ሥራለት። 33በጨርቁ ጠርዝ ዙሪያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ሮማኖቹን፣ በመካከሉም የወርቅ ሻኵራዎችን አብጅ። 34የወርቅ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በጨርቁ ጠርዝ ዙሪያ በመፈራረቅ ይሆናሉ። 35አሮንም በአገልግሎቱ ጊዜ ይህን መልበስ አለበት፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወደ መቅደሱ በገባና ከመቅደሱ ሲወጣ እንዳይሞት የሻኵራዎቹ ድምፅ ይሰማል።

36“ከንጹሕ ወርቅ ዝርግ ሳሕን አበጅተህ፣ ‘ቅዱስ እግዚአብሔር (ያህዌ)’ በማለት በማኅተም ላይ እንደሚቀረጽ ቅረጸው። 37ከመጠምጠሚያው ጋር እንዲያያዝ ሰማያዊ ፈትል እሰርበት፤ እርሱም በመጠምጠሚያው ፊት በኩል ይሁን። 38ይህም በአሮን ግንባር ላይ ይሆናል፤ እስራኤላውያን ለይተው በሚያቀርቧቸው በማናቸውም የተቀደሱ ስጦታዎች ውስጥ ያለውን በደል ይሸከማል፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሁልጊዜ በአሮን ግንባር ላይ ይሆናል።

39“ሸሚዙን ከቀጭን በፍታ ሥራ፤ መጠምጠሚያውንም ከቀጭን በፍታ አብጀው፤ መታጠቂያውንም ጥልፍ ጠላፊ የሠራው ይሁን። 40የአሮን ወንድ ልጆች ክብርና ማዕረግ እንዲኖራቸው ሸሚዞችን፣ መታጠቂያዎችን፣ የራስ ማሰሪያዎችን አብጅላቸው። 41እነዚህን ልብሶች ለአሮንና ለወንድ ልጆቹ ካለበስህ በኋላ ቅባቸው፤ ካናቸው፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ቀድሳቸው።

42“ከወገብ ጀምሮ እስከ ጭን የሚደርስ ሰውነትን የሚሸፍን ከበፍታ የተሠራ የውስጥ ቍምጣ አብጅ። 43አሮንና ወንድ ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ በደል ፈጽመው እንዳይሞቱ እነዚህን መልበስ አለባቸው።

“ለአሮንና ለትውልዶቹ ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።