Забур 132 – CARS & NASV

Священное Писание

Забур 132:1-3

Песнь 132

Песнь восхождения, Давуда.

1Как хорошо и как приятно

жить братьям вместе!

2Это – как возлитое на голову драгоценное масло,

стекающее на бороду главного священнослужителя Харуна,

стекающее на края его одежды132:2 См. Исх. 29:7; 30:22-33.;

3как если бы роса горы Хермон132:3 Хермон – гора на северной границе Исраила, известная тем, что на её склонах выпадает чрезвычайно обильная роса.

сошла на горы Сионские.

Там Вечный обещал дать Своё благословение –

вечную жизнь.

New Amharic Standard Version

መዝሙር 132:1-18

መዝሙር 132

የክብረ በዓል መዝሙር

132፥8-10 ተጓ ምብ – 2ዜና 6፥41-42

መዝሙረ መዓርግ።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ዳዊትን፣

የታገሠውንም መከራ ሁሉ ዐስብ፤

2እርሱ ለእግዚአብሔር ማለ፤

ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤

3“ወደ ቤቴ አልገባም፤

ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤

4ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣

ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤

5ለእግዚአብሔር ስፍራን፣

ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”

6እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤

በቂርያትይዓሪም132፥6 አንዳንዶቹ ያዓር ይላሉ። አገኘነው።

7“ወደ ማደሪያው እንግባ፤

እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።

8እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ፤

አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።

9ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤

ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”

10ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል፣

የቀባኸውን ሰው አትተወው።

11እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤

በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤

“ከገዛ ራስህ ፍሬ፣

በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።

12ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣

የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣

ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣

ለዘላለም ይቀመጣሉ።”

13እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፣

ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወድዷልና እንዲህ አለ፤

14“ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤

ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ።

15እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ፤

ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ።

16ለካህናቷ ድነትን አለብሳለሁ፤

ቅዱሳኗም በደስታ ይዘምራሉ።

17“በዚህም ለዳዊት ቀንድ132፥17 እዚህ ላይ ቀንድ የጥንካሬ ትእምርት ሲሆን፣ ንጉሥን ያመለክታል። አበቅላለሁ፤

ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ።

18ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባቸዋለሁ፤

እርሱ ግን በራሱ ላይ የደፋው ዘውድ ያበራል።”