Job 1 – NIVUK & NASV

New International Version – UK

Job 1:1-22

Prologue

1In the land of Uz there lived a man whose name was Job. This man was blameless and upright; he feared God and shunned evil. 2He had seven sons and three daughters, 3and he owned seven thousand sheep, three thousand camels, five hundred yoke of oxen and five hundred donkeys, and had a large number of servants. He was the greatest man among all the people of the East.

4His sons used to hold feasts in their homes on their birthdays, and they would invite their three sisters to eat and drink with them. 5When a period of feasting had run its course, Job would make arrangements for them to be purified. Early in the morning he would sacrifice a burnt offering for each of them, thinking, ‘Perhaps my children have sinned and cursed God in their hearts.’ This was Job’s regular custom.

6One day the angels1:6 Hebrew the sons of God came to present themselves before the Lord, and Satan1:6 Hebrew satan means adversary. also came with them. 7The Lord said to Satan, ‘Where have you come from?’

Satan answered the Lord, ‘From roaming throughout the earth, going to and fro on it.’

8Then the Lord said to Satan, ‘Have you considered my servant Job? There is no-one on earth like him; he is blameless and upright, a man who fears God and shuns evil.’

9‘Does Job fear God for nothing?’ Satan replied. 10‘Have you not put a hedge around him and his household and everything he has? You have blessed the work of his hands, so that his flocks and herds are spread throughout the land. 11But now stretch out your hand and strike everything he has, and he will surely curse you to your face.’

12The Lord said to Satan, ‘Very well, then, everything he has is in your power, but on the man himself do not lay a finger.’

Then Satan went out from the presence of the Lord.

13One day when Job’s sons and daughters were feasting and drinking wine at the eldest brother’s house, 14a messenger came to Job and said, ‘The oxen were ploughing and the donkeys were grazing nearby, 15and the Sabeans attacked and made off with them. They put the servants to the sword, and I am the only one who has escaped to tell you!’

16While he was still speaking, another messenger came and said, ‘The fire of God fell from the heavens and burned up the sheep and the servants, and I am the only one who has escaped to tell you!’

17While he was still speaking, another messenger came and said, ‘The Chaldeans formed three raiding parties and swept down on your camels and made off with them. They put the servants to the sword, and I am the only one who has escaped to tell you!’

18While he was still speaking, yet another messenger came and said, ‘Your sons and daughters were feasting and drinking wine at the eldest brother’s house, 19when suddenly a mighty wind swept in from the desert and struck the four corners of the house. It collapsed on them and they are dead, and I am the only one who has escaped to tell you!’

20At this, Job got up and tore his robe and shaved his head. Then he fell to the ground in worship 21and said:

‘Naked I came from my mother’s womb,

and naked I shall depart.1:21 Or shall return there

The Lord gave and the Lord has taken away;

may the name of the Lord be praised.’

22In all this, Job did not sin by charging God with wrongdoing.

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 1:1-22

መግቢያ

1ዖፅ በሚባል አገር የሚኖር ኢዮብ የተባለ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነበር። 2እርሱም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት። 3ሀብቱም ሰባት ሺሕ በጎች፣ ሦስት ሺሕ ግመሎች፣ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ እንስት አህዮች ነበረ፤ እጅግ ብዙ ባሮችም ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ከሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ።

4ወንዶች ልጆቹም ተራ በተራ በየቤታቸው ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ከእነርሱም ጋር እንዲበሉና እንዲጠጡ ሦስቱን እኅቶቻቸውን ይጋብዙ ነበር። 5የግብዣው ጊዜ ካለፈ በኋላ ኢዮብ ልኮ ያስመጣቸውና፣ “ምናልባት ልጆቼ ኀጢአት ሠርተው፣ እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” በማለት ጧት በማለዳ ስለ እያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ ያነጻቸው ነበር፤ ኢዮብ ይህን ዘወትር ያደርግ ነበር።

የመጀመሪያው የኢዮብ ፈተና

6አንድ ቀን መላእክት1፥6 በዕብራይስጡ የእግዚአብሔር ልጆች ይላል። በእግዚአብሔር ፊት ሊቆሙ በመጡ ጊዜ፣ ሰይጣንም1፥6 ሰይጣን ማለት ከሳሽ ማለት ነው። መጥቶ በመካከላቸው ቆመ። 7እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “ከወዴት መጣህ?” አለው።

ሰይጣንም፣ “በምድር ሁሉ ዞርሁ፤ ወዲያና ወዲህም ተመላለስሁባት” ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ።

8እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው የለም” አለው።

9ሰይጣንም፣ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን? 10በእርሱና በቤተ ሰቦቹ፣ ባለው ንብረትስ ሁሉ ዙሪያ ዐጥር ሠርተህለት የለምን? የበጎቹና የላሞቹ መንጋ ምድርን ሁሉ እስኪሞሉ ድረስ የእጁን ሥራ ባርከህለታል። 11እስቲ፣ እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ንካበት፤ በርግጥ ፊት ለፊት ይረግምሃል።”

12እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው፤ እርሱን ራሱን ግን እንዳትነካው” አለው።

ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።

13አንድ ቀን የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፤ 14መልእክተኛም ወደ ኢዮብ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በሬዎች እያረሱ፣ አህዮችም በአጠገባቸው እየጋጡ ሳሉ፣ 15ሳባውያን ጥቃት አድርሰውባቸው ይዘዋቸው ሄዱ፤ አገልጋዮቹንም በሰይፍ ገደሉ። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።”

16እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወረደች፤ በጎችንና አገልጋዮችንም በላች፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው።

17እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “ከለዳውያን በሦስት ቡድን መጥተው ጥቃት አደረሱ፤ ግመሎችህንም ይዘው ሄዱ፤ አገልጋዮቹን በሰይፍ ገደሉ፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው።

18እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው እየበሉና እየጠጡ ሳሉ፣ 19እነሆ፤ ታላቅ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ መጣ፤ የቤቱንም አራት ማእዘናት መታ፤ እርሱም በልጆቹ ላይ ወድቆ ገደላቸው። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።” 20ኢዮብም ተነሣ፤ ልብሱን ቀደደ፤ ራሱን ተላጨ፤ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፤ 21እንዲህም አለ፤

“ዕራቍቴን ከእናቴ ማሕፀን ወጣሁ፤

ዕራቍቴንም እሄዳለሁ።1፥21 ወይም ወደዚያ እመለሳለሁ

እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ነሣ፤

የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን።”

22በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ አልበደለም፤ በእግዚአብሔርም ላይ ክፉ አልተናገረም።