Ecclesiastes 2 – NIV & NASV

New International Version

Ecclesiastes 2:1-26

Pleasures Are Meaningless

1I said to myself, “Come now, I will test you with pleasure to find out what is good.” But that also proved to be meaningless. 2“Laughter,” I said, “is madness. And what does pleasure accomplish?” 3I tried cheering myself with wine, and embracing folly—my mind still guiding me with wisdom. I wanted to see what was good for people to do under the heavens during the few days of their lives.

4I undertook great projects: I built houses for myself and planted vineyards. 5I made gardens and parks and planted all kinds of fruit trees in them. 6I made reservoirs to water groves of flourishing trees. 7I bought male and female slaves and had other slaves who were born in my house. I also owned more herds and flocks than anyone in Jerusalem before me. 8I amassed silver and gold for myself, and the treasure of kings and provinces. I acquired male and female singers, and a harem2:8 The meaning of the Hebrew for this phrase is uncertain. as well—the delights of a man’s heart. 9I became greater by far than anyone in Jerusalem before me. In all this my wisdom stayed with me.

10I denied myself nothing my eyes desired;

I refused my heart no pleasure.

My heart took delight in all my labor,

and this was the reward for all my toil.

11Yet when I surveyed all that my hands had done

and what I had toiled to achieve,

everything was meaningless, a chasing after the wind;

nothing was gained under the sun.

Wisdom and Folly Are Meaningless

12Then I turned my thoughts to consider wisdom,

and also madness and folly.

What more can the king’s successor do

than what has already been done?

13I saw that wisdom is better than folly,

just as light is better than darkness.

14The wise have eyes in their heads,

while the fool walks in the darkness;

but I came to realize

that the same fate overtakes them both.

15Then I said to myself,

“The fate of the fool will overtake me also.

What then do I gain by being wise?”

I said to myself,

“This too is meaningless.”

16For the wise, like the fool, will not be long remembered;

the days have already come when both have been forgotten.

Like the fool, the wise too must die!

Toil Is Meaningless

17So I hated life, because the work that is done under the sun was grievous to me. All of it is meaningless, a chasing after the wind. 18I hated all the things I had toiled for under the sun, because I must leave them to the one who comes after me. 19And who knows whether that person will be wise or foolish? Yet they will have control over all the fruit of my toil into which I have poured my effort and skill under the sun. This too is meaningless. 20So my heart began to despair over all my toilsome labor under the sun. 21For a person may labor with wisdom, knowledge and skill, and then they must leave all they own to another who has not toiled for it. This too is meaningless and a great misfortune. 22What do people get for all the toil and anxious striving with which they labor under the sun? 23All their days their work is grief and pain; even at night their minds do not rest. This too is meaningless.

24A person can do nothing better than to eat and drink and find satisfaction in their own toil. This too, I see, is from the hand of God, 25for without him, who can eat or find enjoyment? 26To the person who pleases him, God gives wisdom, knowledge and happiness, but to the sinner he gives the task of gathering and storing up wealth to hand it over to the one who pleases God. This too is meaningless, a chasing after the wind.

New Amharic Standard Version

መክብብ 2:1-26

ምድራዊ ደስታ ከንቱ ነው

1እኔም በልቤ፣ “መልካም የሆነውን ለማወቅ፣ በተድላ እፈትንሃለሁ” አልሁ፤ ነገር ግን ያም ከንቱ ነበረ። 2ደግሞም፣ “ሣቅ ሞኝነት ነው፤ ተድላስ ምን ይጠቅማል?” አልሁ። 3አሁንም አእምሮዬ በጥበብ እየመራኝ ራሴን በወይን ጠጅ ደስ ለማሰኘት፣ ሞኝነትንም ለመያዝ ሞከርሁ፤ ሰዎች በዐጭር የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ባለው ላይ ቢሠሩት ሊጠቅማቸው የሚችል ምን እንደ ሆነ ለማየት ፈለግሁ።

4ታላላቅ ነገሮችን አከናወንሁ፤ ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይንንም ተከልሁ፤ 5አትክልትን ተከልሁ፤ የመዝናኛ ስፍራዎችን አዘጋጀሁ፤ በእነዚህም ላይ ፍሬ የሚያፈሩ የዛፍ ዐይነቶችን ሁሉ ተከልሁባቸው፤ 6የሚለመልሙ ዛፎችን፣ ለቦይ የሚሆኑ የውሃ ማጠራቀሚያዎችን ሠራሁ። 7ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤቴም የተወለዱ ሌሎች ባሪያዎች ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ይልቅ ብዙ የከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎች ነበሩኝ። 8ለራሴም ብርንና ወርቅን፣ የነገሥታትና የአውራጃዎችን ሀብት አካበትሁ፤ ወንድና ሴት አዝማሪዎች፣ የሰው መደሰቻ የሆኑ ቅምጦች2፥8 በዕብራይስጥ የዚህ ሐረግ ትርጕም አይታወቅም ነበሩኝ። 9ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሆንሁ፤ በዚህ ሁሉ ጥበቤ ከእኔ ጋር ነበረች።

10ዐይኔ የፈለገውን ሁሉ አልከለከልሁትም፤

ለልቤም ምድራዊ ደስታን አልነፈግሁትም፤

ልቤ በሠራሁት ሁሉ ደስ አለው፤

ይህም የድካሜ ሁሉ ዋጋ ነበረ።

11ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሁሉ፣

ለማግኘትም የደከምሁትን ድካም ሁሉ ሳስብ፣

ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነበር፤

ከፀሓይ በታች ምንም ትርፍ አልነበረም።

ጥበብና ሞኝነት ከንቱ ናቸው

12ከዚያም ጥበብን፣

እብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ሐሳቤን መለስሁ፤

አስቀድሞ ከተደረገው በቀር፣

ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል?

13ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ ሁሉ፣

ጥበብም ከሞኝነት እንደሚበልጥ ተመለከትሁ።

14የጠቢብ ሰው ዐይኖች ያሉት በራሱ ውስጥ ነው፤

ሞኝ ግን በጨለማ ውስጥ ይራመዳል፤

ሆኖም የሁለቱም ዕድል ፈንታ፣

አንድ መሆኑን ተገነዘብሁ።

15ከዚያም በልቤ፣

“የሞኙ ዕድል ፈንታ በእኔም ላይ ይደርሳል፤

ታዲያ ጠቢብ በመሆኔ ትርፌ ምንድን ነው?” አልሁ።

በልቤም፣

“ይህም ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ።

16ጠቢቡም ሰው እንደ ሞኙ ለዘላለም አይታወስምና፤

በሚመጡት ዘመናት ሁለቱም ይረሳሉ።

ለካ፣ ጠቢቡም እንደ ሞኙ መሞቱ አይቀርም!

ጥረት ከንቱ ነው

17ስለዚህ ከፀሓይ በታች የሚሠራው ሥራ አሳዛኝ ስለ ሆነብኝ ሕይወትን ጠላሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። 18ከፀሓይ በታች የደከምሁበትን ነገር ሁሉ ጠላሁት፣ ከኋላዬ ለሚመጣው የግድ እተውለታለሁና። 19እርሱ ጠቢብ ወይም ሞኝ ይሆን እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከፀሓይ በታች ድካሜንና ችሎታዬን ባፈሰስሁበት ሥራ ሁሉ ላይ ባለቤት ይሆንበታል፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። 20ስለዚህ ከፀሓይ በታች በደከምሁበት ነገር ሁሉ ላይ ልቤ ተስፋ መቍረጥ ጀመረ፤ 21ምክንያቱም ሰው ሥራውን በጥበብ፣ በዕውቀትና በብልኀት ሠርቶ፣ ከዚያ ያለውን ሁሉ ለሌላ ላልለፋበት ሰው ይተውለታል። ይህም ደግሞ ከንቱና ትልቅ ጕዳት ነው። 22ሰው ከፀሓይ በታች በሚደክምበት ጥረትና ልፋት ሁሉ ትርፉ ምንድን ነው? 23በዘመኑ ሁሉ ሥራው ሥቃይና ሐዘን ነው፤ በሌሊትም እንኳ ቢሆን አእምሮው አያርፍም። ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

24ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት፣ በሥራውም ከመርካት ሌላ የሚሻለው ነገር የለውም፤ ይህም ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደሚሰጥ አየሁ፤ 25ከእርሱ ዘንድ ካልሆነ ማን መብላትና መደሰት ይችላል? 26እግዚአብሔር፣ ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።