2 ቆሮንቶስ 1 – NASV & CRO

New Amharic Standard Version

2 ቆሮንቶስ 1:1-24

1በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፤

በቆሮንቶስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፤

2ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

የመጽናናት አምላክ

3የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። 4እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል። 5የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ የመብዛቱን ያህል መጽናናታችንም በክርስቶስ በኩል ይበዛልናል። 6መከራ ብንቀበል ስለ እናንተ መጽናናትና መዳን ነው። ብንጽናናም እኛ የተቀበልነውን መከራ በመቀበል በትዕግሥት እንድትጸኑ ስለ እናንተ መጽናናት ነው። 7ስለ እናንተ ያለን ተስፋ ጽኑ ነው፤ ምክንያቱም በመከራችን እንደ ተካፈላችሁ ሁሉ በመጽናናታችንም እንደምትካፈሉ እናውቃለን።

8ወንድሞች ሆይ፤ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወድዳለን፤ በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር። 9በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤ ይህም የሆነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንድንታመን እንጂ፣ በራሳችን እንዳንታመን ነው። 10እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል። 11እናንተም በጸሎታችሁ ደግፉን፤ በብዙዎች ጸሎት ስለ ተሰጠን ስጦታ ብዙ ሰዎች ስለ እኛ1፥11 ብዙ ቅጆች እናንተ ይላሉ። ምስጋና ያቀርባሉ።

ጳውሎስ ዕቅዱን ለወጠ

12እንግዲህ ትምክሕታችን ይህ ነው፤ በዚህ ዓለም በተለይም ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት፣ ከእግዚአብሔር በሆነ ቅድስናና ቅንነት እንደ ኖርን ኅሊናችን ይመሰክራል፤ ይህም በሰው ጥበብ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ነው። 13ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን ነገር አንጽፍላችሁም፤ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ። 14እናንተ በእኛ እንደምትመኩ ሁሉ እኛም በእናንተ እንደምንመካ አሁን የተረዳችሁን በከፊል ቢሆንም፣ በጌታ ኢየሱስ ቀን ሁሉን ትረዳላችሁ።

15በዚህ ርግጠኛ ስለ ነበርሁ በዕጥፍ እንድትጠቀሙ፣ በመጀመሪያ ልጐበኛችሁ ዐቅጄ ነበር። 16ወደ መቄዶንያ ስሄድ እግረ መንገዴን ልጐበኛችሁና ከመቄዶንያም በእናንተ በኩል ተመልሼ ወደ ይሁዳ ስሄድ በጕዞዬ እንድትረዱኝ ዐቅጄ ነበር። 17ይህን ሳቅድ በሚገባ ሳላስብ ያደረግሁት ይመስላችኋልን? ወይስ በዓለማዊ ልማድ አንዴ፣ “አዎን፣ አዎን” ወዲያው ደግሞ፣ “አይደለም፣ አይደለም” የምል ይመስላችኋልን?

18እግዚአብሔር ታማኝ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ለእናንተ የምንናገረው ቃላችን፣ “አዎን” እና “አይደለም” ሊሆን አይችልም፤ 19ምክንያቱም እኔም ሆንሁ ሲላስና1፥19 ግሪኩ ሲልዋኑስ ይላል። ጢሞቴዎስ፣ እኛ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ “አዎን” እና “አይደለም” አልነበረም፤ ነገር ግን በእርሱ ዘወትር፣ “አዎን” ነው። 20በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ፣ “አዎን” የሚሆኑት በእርሱ ነውና፤ እኛም በእርሱ አማካይነት ለእግዚአብሔር ክብር፣ “አሜን” የምንለው በዚህ ምክንያት ነው። 21እንግዲህ፣ እኛንም እናንተንም በክርስቶስ ጸንተን እንድንቆም የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው፤ የቀባንም እርሱ ነው፤ 22የእርሱ ለመሆናችን ማኅተሙን ያተመብን ደግሞም ወደ ፊት ለምናገኘው ነገር የመንፈሱን ዋስትና በልባችን ያኖረ እርሱ ነው።

23ወደ ቆሮንቶስ ተመልሼ ያልመጣሁት እንዳላሳዝናችሁ ብዬ ነው፤ ይህ እውነት ካልሆነ እግዚአብሔር ይመስክርብኝ። 24ጸንታችሁ የምትቆሙት በእምነት ስለሆነ፣ ደስ እንዲላችሁ ከእናንተ ጋር እንሠራለን እንጂ በእምነታችሁ ላይ ለመሠልጠን አይደለም።

Knijga O Kristu

2 Korinćanima 1:1-24

Pozdravi

1Pišu vam Pavao, apostol Krista Isusa Božjom voljom, i brat Timotej. Pišemo Božjoj crkvi u Korintu i svima svetima u cijeloj Ahaji. 2Neka vam je milost i mir od našega Boga Oca i Gospodina Isusa Krista.

Bog pruža utjehu svima

3Slava Bogu, Ocu našega Gospodina Isusa Krista. On je izvor svakog milosrđa i Bog koji nas tješi. 4On nas tješi u svim nevoljama, da bismo i mi mogli druge tješiti u nevoljama istom utjehom kojom Bog tješi nas. 5Koliko se obilno patnje za Krista izlijevaju na nas, toliko je preobilna i naša utjeha u Kristu. 6Podnosimo li nevolje, to je zaradi vaše utjehe i spasenja. Primamo li utjehu, to je zato da bismo vas mogli hrabriti kako biste strpljivo mogli podnositi iste patnje koje i mi podnosimo. 7Čvrsto vjerujemo da ćete, kao što s nama dijelite patnje, također dijeliti s nama i Božju utjehu.

8Željeli bismo da znate, braćo, kakve su nas nevolje zapale u Aziji. Opteretile su nas preko svake mjere, toliko preko naše snage da smo već bili izgubili nadu da ćemo preživjeti. 9Smatrali smo se već osuđenima na smrt, ali sve se to zbilo zato da se ne bismo uzdali u sebe, već u Boga koji uskrisuje mrtve. 10Od tolike nas je smrtne pogibli izbavio onaj u kojega se uzdamo da će nas i dalje izbavljati! 11I vi pomažete moleći za nas, da bi mnogi mogli zahvaljivati za uslišane molitve mnogih.

Pavlova promjena plana

12Možemo s pouzdanjem i s čistom savješću reći da smo prema svima, a posebice prema vama, postupali sveto i iskreno u svemu što smo činili, ne oslanjajući se na tjelesnu mudrost, već na Božju milost. 13-14Nismo vam pisali ništa što ne biste mogli pročitati ili razumjeti. Nadam se da ćete nas, kao što ste nas djelomice već razumjeli, jednoga dana potpuno razumjeti. Tako ćemo i mi vama, kao i vi nama, biti na ponos u dan našega Gospodina Isusa.

15U tome sam pouzdanju kanio doći tako da primite dvostruki blagoslov: 16svratiti najprije k vama na putu u Makedoniju, a zatim i vraćajući se iz Makedonije, kako biste me mogli otpraviti na put u Judeju.

17Jesam li, dakle, o tome lakomisleno odlučio, ili sam poput ljudi iz svijeta koji kažu “da”, a zapravo misle “ne”? 18Bog mi je svjedok da nisam takav. Moje “da” znači “da” 19jer u Isusa Krista, Božjega Sina o kojemu smo vam Timotej, Silvan i ja propovijedali, nema dvojbe između “da” i “ne”; naprotiv, on je Božje “da”, Božja potvrda. 20U njemu su tako ostvarena sva Božja obećanja; zato možemo reći “Amen” kad proslavljamo Boga kroz Krista. 21Bog je taj koji i vas i nas čini snažnima u Kristu i koji nas je pomazao. 22Obilježio nas je pečatom da smo njegovo vlasništvo i u srca nam stavio zalog: Svetoga Duha.

23Prizivam Boga za svjedoka da vam govorim istinu: nisam ponovno došao u Korint samo zato što vas nisam htio ražalostiti oštrim prijekorom. 24Jer, ne bismo vam htjeli naređivati što i kako da vjerujete, već surađivati s vama da biste bili radosni, jer vi u vjeri čvrsto stojite.