New Amharic Standard Version

2 ጴጥሮስ 3:1-18

የጌታ ቀን

1ወዳጆች ሆይ፤ ይህ አሁን የምጽፍላችሁ ሁለተኛው መልእክት ነው። ሁለቱንም መልእክቶች የጻፍሁላችሁ ቅን ልቦናችሁን እንድታነቃቁ ለማሳሰብ ነው፤ 2ደግሞም ቀድሞ በቅዱሳን ነቢያት የተነገረውን ቃል እንዲሁም በሐዋርያት አማካይነት በጌታችንና በአዳኛችን የተሰጠውን ትእዛዝ እንድታስቡ ነው።

3ከሁሉ አስቀድሞ ይህን ዕወቁ፤ በመጨረሻው ዘመን የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ዘባቾች እየዘበቱ ይመጣሉ። 4እነርሱም፣ “ ‘እመጣለሁ’ ያለው ታዲያ የት አለ? አባቶች ከሞቱበት ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል” ይላሉ። 5ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ሰማያት ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው እንደሚኖሩ፣ መሬትም በውሃ መካከልና በውሃም እንደ ተሠራች ሆን ብለው ይክዳሉ፤ 6በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ። 7በዚያው ቃል ደግሞ አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር፣ ኀጢአተኞች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀዋል።

8ወዳጆች ሆይ፤ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን መሆኑን ይህን አንድ ነገር አትርሱ። 9አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።

10የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ ይመጣል፤ በዚያች ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በእሳት ይጠፋል፤ ምድርና በእርሷም ላይ ያለ ነገር ሁሉ ይቃጠላል።3፥10 በአንዳንድ ቅጅዎች ምድር ወና ትሆናለች ይላል

11እንግዲህ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ የሚጠፋ ከሆነ፣ እናንተ እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል? አዎን፣ በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት ልትኖሩ ይገባችኋል፤ 12ደግሞም የእግዚአብሔርን ቀን እየተጠባበቃችሁ መምጫውን ልታፋጥኑ3፥12 ወይም የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት በናፍቆት ስትጠብቁ ይገባል። በዚያን ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በታላቅ ትኵሳት ይቀልጣል። 13እኛ ግን ጽድቅ የሚኖርበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በተስፋ ቃሉ መሠረት እንጠባበቃለን።

14ስለዚህ ወዳጆች ሆይ፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች የምትጠባበቁ ስለ ሆናችሁ፣ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ከእርሱ ጋር በሰላም እንድትገኙ ትጉ። 15የጌታችን ትዕግሥት እናንተ እንድትድኑ እንደሆነ አስቡ፤ እንዲሁም ወንድማችን ጳውሎስ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፤ 16እርሱ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፎአል፤ በመልእክቶቹም ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ፣ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።

17እንግዲህ ወዳጆች ሆይ፤ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ፣ ጸንታችሁ ከቆማችሁበት መሠረት በዐመፀኞች ስሕተት ተስባችሁ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ። 18ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤ ለእርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን፤ አሜን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

彼得后书 3:1-18

主再来的应许

1亲爱的弟兄姊妹,我现在写给你们的是第二封信。这两封信都是为了提醒你们,激励你们保持真诚的心, 2叫你们记得从前圣先知们说的预言,以及我们的主和救主借着派到你们那里的使徒所传给你们的诫命。

3最重要的是,你们要知道在末世的时候必出现喜欢冷嘲热讽、为所欲为的人。他们说: 4“主要降临的应许在哪里?从我们的祖先长眠地下直到现在,万物依旧与创世之初一样。” 5他们故意忽略:太初,上帝凭口中的话语创造了诸天,并借着水从水中造出了地; 6后来,那个世界被水淹没而毁灭了。 7同样,现在的天地要凭上帝的话语存留到不敬虔的人被审判和毁灭的日子,那时天地要被火焚烧。

8亲爱的弟兄姊妹,有一件事你们不可忽略,就是主看一日如千年,千年如一日。 9主的应许还未实现,有人以为祂拖延,其实祂不是拖延,而是在宽容你们。祂不愿任何人灭亡,愿意人人悔改。 10不过,主再来的日子要像贼一样突然临到。那日,诸天必在一声巨响中消失,有形有质的都要被烈火焚毁,大地和其中的一切将不复存在。

11-12一切都要这样被焚毁,你们在热切等候上帝来临的日子期间,该怎样过圣洁、敬虔的生活啊!因为到那日,天要被火焚毁,有形有质的都要被烈火熔化烧尽。 13但我们等候的是上帝应许的新天新地,有公义住在其中。

14所以,亲爱的弟兄姊妹,你们既然盼望这些事,就当努力使自己在主面前毫无瑕疵,无可指责,安然无惧。 15你们要把耶稣的宽容看作是让众人得救的机会,正如我们亲爱的弟兄保罗按着上帝赐给他的智慧写信告诉你们的。 16他所有的书信都谈到这些事。一些不学无术、反复无常的人曲解了信中一些难懂的地方,就像曲解其他经文一样,他们是自取灭亡。

17因此,亲爱的弟兄姊妹,你们既然预先知道了这些事,就应该提防,不要让那些不法之徒用错谬的理论引诱你们,使你们失去原本坚固的立场。 18相反,你们要在我们的主和救主耶稣基督的恩典中不断长进,越来越认识祂。

愿荣耀归给祂,从现在直到永远。阿们!