New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 1:1-17

ሰሎሞን ጥበብ እንዲሰጠው ጠየቀ

1፥2-13 ተጓ ምብ – 3፥4-15

1፥14-17 ተጓ ምብ – 1ነገ 10፥26-29፤ 2ዜና 9፥25-28

1አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበር፣ እጅግም ስላገነነው፣ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በመንግሥቱ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ።

2ከዚያም ሰሎሞን ለመላው እስራኤል፣ ለሻለቆች፣ ለመቶ አለቆች፣ ለዳኞች፣ ለእስራኤል መሪዎች ሁሉ እንዲሁም ለየቤተ ሰቡ አለቆች ተናገረ። 3የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የአምላክ የመገናኛ ድንኳን በዚያ ስለ ነበር፣ ሰሎሞንና መላው ጉባኤ በገባዖን ወዳለው ኰረብታ ሄዱ። 4በዚያ ጊዜ ዳዊት የአምላክን ታቦት ከቂሪያት ይዓሪም በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎ ወዳዘጋጀለት ስፍራ አምጥቶት ነበር፤ 5ይሁን እንጂ የሆር ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው መሠዊያ በገባዖን በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ለፊት ይገኝ ነበር፤ ስለዚህ ሰሎሞንና ጉባኤው ይህንኑ ፈለጉ። 6ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጥቶ በላዩ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።

7በዚያ ሌሊት እግዚአብሔር ለሰሎሞን ተገልጦ፣ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ሁሉ ጠይቀኝ” አለው።

8ሰሎሞን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ በጎነት አድርገህለታል፤ እኔንም በእግሩ ተክተህ አንግሠኸኛል። 9አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ያነገሥኸኝ ብዛቱ እንደ ትቢያ በሆነ ሕዝብ ላይ ስለ ሆነ፣ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው ተስፋ ይጽና። 10ይህን ሕዝብ ለመምራት እንድችል፣ ጥበብና ዕውቀትን ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊገዛ ይችላል?”

11እግዚአብሔርም ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “የልብህ መሻት ይህ ስለ ሆነ፣ ብልጥግናና ሀብት ወይም የጠላቶችህን ነፍስ ወይም ረጅም ዕድሜ ስላልጠየቅህ፣ ነገር ግን ባነገሥሁህ ሕዝቤ ላይ የምትገዛበትን ጥበብና ዕውቀት ስለ ጠየቅህ፣ 12ጥበብና ዕውቀት ይሰጥሃል፤ እንዲሁም ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተ በኋላም የሚነሣው የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።”

13ሰሎሞንም የመገናኛው ድንኳን ካለበት ከገባዖን ኰረብታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ።

14ሰሎሞን ሠረገሎችንና1፥14 ወይም ሠረገለኞች ተብሎ መተርጒም ይቻላል። ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና እርሱ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው። 15ንጉሡም ወርቁና ብሩ በኢየሩሳሌም እንደ ተራ ድንጋይ እንዲበዛ፣ ዝግባውም በየኰረብታው ግርጌ እንደሚገኝ የሾላ ዛፍ እንዲበዛ አደረገ። 16የሰሎሞንም ፈረሶች የመጡት ከግብፅና1፥16 በዚህና በቍጥር 17 ላይ የተጠቀሰችው በኪልቂያ አውራጃ የምትገኘው ሙዙር ልትሆን ትችላለች። ከቀዌ ነበር፤ ከቀዌ1፥16 ምናልባት ኪልቂያ ናት። የገዟቸውም የንጉሡ ነጋዴዎች ነበሩ። 17ከግብፅ ያስገቧቸውም አንዱን ሠረገላ በስድስት መቶ ሰቅል1፥17 7 ኪሎ ግራም ያህል ነው። ብር፣ አንዱን ፈረስ በአንድ መቶ አምሳ ሰቅል1፥17 1.7 ኪሎ ግራም ነው። ብር ገዝተው ነው። እነዚህንም ደግሞ ለኬጢያዊያንና ለሦርያውያን ነገሥታት ሁሉ ይሸጡላቸው ነበር።

Thai New Contemporary Bible

2พงศาวดาร 1:1-17

โซโลมอนทูลขอสติปัญญา

(1พกษ.3:4-15; 10:26-29; 2พศด.9:25-28)

1โซโลมอนโอรสของดาวิดทรงสถาปนาราชบัลลังก์ให้มั่นคงเป็นปึกแผ่น เนื่องจากพระยาห์เวห์พระเจ้าของพระองค์สถิตกับพระองค์ และทำให้พระองค์ยิ่งใหญ่กว่าผู้ใด

2โซโลมอนตรัสแก่อิสราเอลทั้งปวง ไม่ว่าจะเป็นแม่ทัพนายกอง ตุลาการ ผู้นำในอิสราเอลหรือหัวหน้าตระกูลต่างๆ 3แล้วโซโลมอนกับชุมนุมประชากรทั้งหมดขึ้นไปยังสถานบูชาบนที่สูงในกิเบโอน เพราะเต็นท์นัดพบขององค์พระผู้เป็นเจ้าซึ่งโมเสสผู้รับใช้ของพระองค์ได้สร้างขึ้นในถิ่นกันดารนั้นอยู่ที่นั่น 4ดาวิดได้อัญเชิญหีบพันธสัญญาของพระเจ้าจากเมืองคีริยาทเยอาริมมายังสถานที่ซึ่งดาวิดเตรียมไว้ เพราะทรงตั้งเต็นท์สำหรับหีบนั้นในกรุงเยรูซาเล็ม 5ส่วนแท่นทองสัมฤทธิ์ซึ่งเบซาเลลบุตรอูรีผู้เป็นบุตรของเฮอร์ได้สร้างขึ้นอยู่ในกิเบโอนตรงหน้าพลับพลาขององค์พระผู้เป็นเจ้า โซโลมอนและชุมนุมประชากรจึงมาทูลถามพระองค์ที่นั่น 6โซโลมอนขึ้นไปยังแท่นทองสัมฤทธิ์ต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าในเต็นท์นัดพบ และถวายสัตว์หนึ่งพันตัวเป็นเครื่องเผาบูชา

7คืนนั้นพระเจ้าทรงปรากฏแก่โซโลมอนและตรัสกับเขาว่า “จงขอสิ่งที่เจ้าต้องการเถิด แล้วเราจะให้เจ้า”

8โซโลมอนกราบทูลพระเจ้าว่า “พระองค์ได้ทรงสำแดงพระกรุณาอย่างยิ่งต่อดาวิดราชบิดาของข้าพระองค์ และทรงตั้งข้าพระองค์เป็นกษัตริย์แทน 9บัดนี้ข้าแต่พระเจ้าพระยาห์เวห์ ขอทรงยืนยันคำมั่นสัญญาที่ทรงให้ไว้กับดาวิดราชบิดาของข้าพระองค์ เพราะทรงตั้งข้าพระองค์ขึ้นเป็นกษัตริย์เหนือชนชาติซึ่งมีจำนวนมากมายเหมือนฝุ่นธุลี 10ขอโปรดประทานสติปัญญาและความรอบรู้เพื่อข้าพระองค์จะได้นำชนชาตินี้ เพราะใครเล่าจะสามารถปกครองชนชาติอันยิ่งใหญ่ของพระองค์นี้ได้?”

11พระเจ้าตรัสกับโซโลมอนว่า “ในเมื่อเจ้ามีใจปรารถนาเช่นนี้ และเจ้าไม่ได้ขอความมั่งคั่ง ทรัพย์สมบัติ หรือเกียรติ ไม่ได้ขอเอาชีวิตศัตรู และไม่ได้ขออายุยืนยาว แต่ขอสติปัญญาและความรอบรู้ เพื่อที่จะปกครองประชากรของเรา ซึ่งเราได้ตั้งเจ้าให้เป็นกษัตริย์เหนือพวกเขา 12ฉะนั้นเราจะให้สติปัญญาและความรอบรู้ที่เจ้าขอไว้ และเราจะให้ทรัพย์สมบัติ ความมั่งคั่ง และเกียรติแก่เจ้าอย่างที่ไม่เคยมีมาก่อน และจะไม่มีกษัตริย์องค์ใดเสมอเหมือนเจ้า”

13โซโลมอนจึงเสด็จจากสถานบูชาบนที่สูงในกิเบโอน จากหน้าเต็นท์นัดพบไปยังกรุงเยรูซาเล็ม และทรงปกครองเหนืออิสราเอล

14โซโลมอนทรงสะสมรถม้าศึกและม้า พระองค์ทรงมีรถม้าศึก 1,400 คัน และม้า 12,000 ตัว1:14 หรือพลรถรบ 12,000 คน ซึ่งพระองค์ทรงเก็บบางส่วนไว้ที่หัวเมืองซึ่งใช้เก็บรถม้าศึก และบางส่วนอยู่กับพระองค์ที่กรุงเยรูซาเล็ม 15พระองค์ทรงทำให้เงินและทองในกรุงเยรูซาเล็มมีมากมายเหมือนก้อนหิน และมีไม้สนซีดาร์ดาษดื่นเหมือนต้นมะเดื่อแถบเชิงเขา 16ม้าของโซโลมอนนั้นนำเข้าจากอียิปต์1:16 หรืออาจจะเป็นมูศูร์ซึ่งเป็นเขตหนึ่งในซิลิเซีย เช่นเดียวกับข้อ 17และจากคูเอ1:16 คงจะเป็นซิลิเซีย คือพ่อค้าหลวงซื้อมาจากคูเอ 17รถม้าศึกแต่ละคันที่นำเข้าจากอียิปต์มีราคาเท่ากับเงินหนัก 600 เชเขล1:17 1 เชเขล คือเงินหนักประมาณ 11.5 กรัม มีค่าเท่ากับค่าแรงสองเดือน (ทั้งสองแห่งในข้อนี้) ม้าราคาตัวละ 150 เชเขล พวกเขายังส่งออกไปขายต่อให้กษัตริย์ทั้งปวงของชาวฮิตไทต์และของชาวอารัมด้วย