2 ቆሮንቶስ 2 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

2 ቆሮንቶስ 2:1-17

1እንግዲህ ላሳዝናችሁ ስላልፈለግሁ ወደ እናንተ ዳግመኛ ላለመምጣት ወሰንሁ፤ 2እኔ ባሳዝናችሁም እንኳ፣ ከእናንተው ካሳዘንኋችሁ በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን አለ? 3ባለፈው ጊዜ እንደዚያ የጻፍሁላችሁ ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ በማለት ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ደስታ የሁላችሁ ደስታ እንደሚሆን አምናለሁ። 4እንደዚያ ስጽፍላችሁ በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፣ በብዙም እንባ ውስጥ ነበርሁ፤ ይህንም ያደረግሁት ለእናንተ ያለኝን ጽኑ ፍቅር እንድታውቁ በማለት እንጂ እናንተን ለማሳዘን አልነበረም።

በደለኛን ይቅር ማለት

5ማንም ሰውን ቢያሳዝን፣ ነገር ማግነን አይሁንብኝና፣ ያሳዘነው እኔን ብቻ ሳይሆን በመጠኑም ቢሆን ሁላችሁንም ነው። 6እንደዚህ ያለው ሰው ብዙዎች የወሰኑበት ቅጣት በቂው ነው። 7ደግሞም ከልክ በላይ ዐዝኖ ተስፋ እንዳይቈርጥ፣ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባችኋል። 8ስለዚህ አሁንም የምትወድዱት መሆናችሁን እንድትገልጹለት እለምናችኋለሁ። 9የጻፍሁላችሁም፣ የሚያጋጥማችሁን ፈተና መቋቋማችሁንና በሁሉም ነገር ታዛዦች መሆናችሁን ለማወቅ ነበር። 10እናንተ ይቅር የምትሉትን ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ፤ በርግጥ ይቅር የምለው ነገር ካለ፣ በክርስቶስ ፊት ይቅር የምለው ስለ እናንተ ስል ነው። 11ይህንም የምናደርገው ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ የእርሱን ዕቅድ አንስተውምና።

የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች

12የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ ወደ ጢሮአዳ በሄድሁ ጊዜ፣ ጌታ በር ከፍቶልኝ ነበር፤ 13ይሁን እንጂ ወንድሜን ቲቶን እዚያ ስላላገኘሁት መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ ተሰናብቻቸው ወደ መቄዶንያ ሄድሁ።

14ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ በድል አድራጊነት እያዞረ ለሚመራን፣ የዕውቀቱንም መዐዛ በእኛ አማካይነት በየስፍራው ለሚገልጥ አምላክ ምስጋና ይሁን፤ 15ምክንያቱም በሚድኑትና በሚጠፉት መካከል ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዐዛ ነን። 16ለሚጠፉት ወደ ሞት የሚወስድ የሞት ሽታ፣ ለሚድኑት ግን ወደ ሕይወት የሚወስድ የሕይወት ሽታ ነን፤ ታዲያ፣ ለዚህ ብቁ የሚሆን ማን ነው? 17እኛ እኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

哥林多后书 2:1-17

爱之深责之切

1我已经决定了,下次到你们那里时不再使大家忧伤。 2如果我使你们忧伤,那么除了因我而忧伤的你们,还有谁能使我喜乐呢? 3我曾为这事写信给你们,免得我到你们那里时,那些本该使我喜乐的人反而使我忧伤。我也深信你们会以我的喜乐为你们的喜乐。 4我万分难过、泪流满面地给你们写了前一封信,并非要使你们忧伤,而是要你们明白我是多么疼爱你们。

要饶恕犯罪的人

5那个令人痛心的人与其说使我忧伤,倒不如说使你们大家都有几分忧伤。我只说几分忧伤,是怕说得太重,他受不了。 6这样的人受了众人的谴责也就够了。 7你们现在要饶恕他、安慰他,免得他忧伤过度而一蹶不振。 8我劝你们要让他确实知道你们仍然爱他。 9为此,我也曾写信给你们,想知道你们是否凡事顺服。 10你们饶恕谁,我也饶恕谁。我若饶恕,是为了你们的缘故在基督面前饶恕的, 11免得撒旦乘虚而入,因为我们并非不知道它的诡计。

基督的香气

12我前往特罗亚传扬基督的福音时,主为我打开了传福音的大门。 13那时,因为没有找到提多弟兄,我心里不安,便辞别众人来到马其顿

14感谢上帝,祂常常在基督里率领我们走在凯旋的行列中,又借着我们到处散发那因认识基督而有的香气。 15不论是在得救的人当中还是在灭亡的人当中,对上帝来说,我们都是基督的馨香之气。 16对灭亡的人而言,这香气是叫人死亡的香气;对得救的人来说,这香气却是叫人得生命的香气。谁能担当这样的重任呢? 17我们并不像许多人为了谋利而出卖上帝的道。我们是上帝差遣的,在上帝面前靠着基督诚诚实实地讲道。