New Amharic Standard Version

2 ሳሙኤል 23:1-39

የዳዊት የመጨረሻ ቃል

1የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤

“በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣

ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣

የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣

የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤

2የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤

ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።

3የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤

የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤

ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣

በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣

4እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣

እንዳለው ብርሃን ነው፤

በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣

ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’

5“የእኔስ ቤት በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክል አይደለምን?

ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣

ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን?

ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣

መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን?

6ነገር ግን ክፉ ሰዎች ሁሉ፣

በእጅ እንደማይሰበሰብ እንደ እሾኽ ይጣላሉ።

7እሾኽ የሚነካ ሁሉ፣

የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤

ባሉበትም ቦታ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።

የኀያላኑ የዳዊት ሰዎች ጀብዱ

23፥8-39 ተጓ ምብ – 1ዜና 11፥10-41

8የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን23፥8 የታሕክሞን ሰው ማለት ሐክሞናዊ ማለት ሊሆን ይችላል። (1ዜና 11፥11 ይመ)። ሰው ዮሴብ በሴትቤት23፥8 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች ግን፣ ኢያሱስቴ ይላሉ፣ ይኸውም፣ ያሾብዓም ነው (1ዜና 11፥11 ይመ)። የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው።23፥8 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ (1ዜና 11፥11 ይመ)፤ ዕብራይስጡና አብዛኞቹ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች ግን ስምንት መቶ ሰዎችን የገደለው አዜናዊው አዲኑ ነበር ይላሉ።

9ከእርሱ ቀጥሎ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ ኤልዔዘር ነበረ፤ እርሱም ለጦርነት አንድ ላይ ተሰብስበው23፥9 1ዜና 11፥13 ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ በዚያ ተሰበሰቡ ይላል የነበሩትን ፍልስጥኤማውያንን በተገዳደሩ ጊዜ፣ ከዳዊት ጋር ከነበሩት ከሦስቱ ኀያላን ሰዎች አንዱ ነበር። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ሸሹ። 10እርሱ ግን የቆመበትን ስፍራ አለቀቀም፤ እጁ እስኪዝልና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ታላቅ ድልን ሰጠ። የሸሸውም ሰራዊት ወደ ኤልዔዘር የተመለሰው የተገደሉትን ሰዎች ለመግፈፍ ብቻ ነበር።

11ከእርሱም ቀጥሎ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፤ ፍልስጥኤማውያንም ሌሒ በተባለ ስፍራ ምስር በሞላበት አንድ ዕርሻ ላይ፣ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ፣ የእስራኤል ሰራዊት ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ 12ሣማ ግን የቆመበትን ስፍራ አለቀቀም፤ ጦርነቱንም ተቋቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ፤ በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ታላቅ ድል ሰጠ።

13በመከር ወራት፣ የፍልስጥኤም ሰራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ። 14በዚያም ጊዜ ዳዊት በምሽግ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሰራዊት በቤተልሔም ነበረ፤ 15ዳዊትም በናፍቆት፣ “በቤተልሔም በር አጠገብ ካለችው ጒድጓድ ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ። 16ስለዚህ ሦስቱ ኀያላን በፍልስጥኤማውያን ሰራዊት መካከል ሰንጥቀው በማለፍ፣ በቤተልሔም በር አጠገብ ካለችው ጒድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን አልጠጣውም፤ ይልቁን በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት አድርጎ አፈሰሰው፤ 17“እርሱም፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” አለ፤ ዳዊትም ሊጠጣው አልፈለገም። እንግዲህ ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር።

18የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ23፥18 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች (እንዲሁም 1ዜና 11፥20 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ሁለት የዕብራይስጥ ቅጆችና የሱርስቱ ትርጒም፣ ሠላሳ ይላሉ። ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ እርሱም ዝናን ያተረፈ ሰው ነበረ። 19አቢሳ ከሦስቱ ይልቅ እጅግ የከበረ አልነበረምን? ከእነርሱ እንደ አንዱ ባይሆንም አለቃቸው ነበረ።

20የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ እርሱም ሁለት በጣም የታወቁ የሞዓብን ሰዎች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጒድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፤ 21ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብፃዊ ገድሎአል፤ ግብፃዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም፣ በናያስ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ወደ እርሱ ሄደ፤ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን በመንጠቅ በገዛ ጦሩ ገደለው።

22የዮዳሄ ልጅ የበናያስ ጀግንነት እንደዚህ ያለ ነበረ፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣ 23ከሠላሳዎቹ ሁሉ በላይ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።

24ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙ ባቸዋል፤

የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣

የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

25አሮዳዊው ሣማ፣

አሮዳዊው ኤሊቃ፣

26ፈሊጣዊው ሴሌስ፣

የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣

27ዓናቶታዊው አቢዔዜር፤

ኩሳታዊው ምቡናይ23፥27 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች (እንዲሁም 1ዜና 11፥29 ይመ) ግን፣ ሲባካይ ይላሉ።

28አሆሃዊው ጸልሞን፣

ነጦፋዊው ማህራይ፣

29የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ23፥29 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆችና ቩልጌት (እንዲሁም 1ዜና 11፥30 ይመ) ግን፣ ሔሌድ ይላሉ።

ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣

30ጲርዓቶናዊው በናያስ፣

የገዓስ ሸለቆ ሰው ሂዳይ23፥30 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች (እንዲሁም 1ዜና 11፥32 ይመ) ግን፣ ሁራይ ይላሉ።

31ዓረባዊው አቢዓልቦን፣

በርሑማዊው ዓዝሞት፣

32ሸዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣

የአሳን ልጆች፤ ዮናታን የተባለው፣

33የአሮዳዊው የሣማ ልጅ23፥33 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች (እንዲሁም 1ዜና 11፥34 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ልጅ የሚለውን አይጨምርም።

የአሮዳዊው የሻራር23፥33 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች (እንዲሁም 1ዜና 11፥35 ይመ) ግን፣ ሳካር ይላሉ። ልጅ አሒአም፤

34የማዕካታዊው የአሐሰባይ ልጅ ኤሌፋላት፣

የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊአም፣

35ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፤

አርባዊው ፈዓራይ፣

36የሱባ ሰው የሆነው የናታን ልጅ ይግዓል፣

37አሞናዊው ጻሌቅ፣

የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጦር መሣሪያ ያዥ የነበረው ብኤሮታዊው ነሃራይ፣

38ይትራዊው ዒራስ፣

ይትራዊው ጋሬብ፣

39እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ፤

በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ።

Nova Versão Internacional

2 Samuel 23:1-39

As Últimas Palavras de Davi

1Estas são as últimas palavras de Davi:

“Palavras de Davi, filho de Jessé;

palavras do homem que foi exaltado,

do ungido pelo Deus de Jacó,

do cantor dos cânticos de Israel23.1 Ou o amado cantor de Israel:

2“O Espírito do Senhor falou por meu intermédio;

sua palavra esteve em minha língua.

3O Deus de Israel falou,

a Rocha de Israel me disse:

‘Quem governa o povo com justiça,

quem o governa com o temor de Deus,

4é como a luz da manhã ao nascer do sol,

numa manhã sem nuvens.

É como a claridade depois da chuva,

que faz crescer as plantas da terra’.

5“A minha dinastia está de bem com Deus.

Ele fez uma aliança eterna comigo,

firmada e garantida em todos os aspectos.

Certamente me fará prosperar em tudo

e me concederá tudo quanto eu desejo.

6Mas os perversos serão lançados fora como espinhos,

que não se ajuntam com as mãos;

7quem quer tocá-los usa uma ferramenta

ou o cabo de madeira da lança.

Os espinhos serão totalmente queimados onde estiverem”.

Os Principais Guerreiros de Davi

8Estes são os nomes dos principais guerreiros de Davi:

Jabesão23.8 Alguns manuscritos da Septuaginta sugerem Is-Bosete, isto é, Esbaal ou Josebe-Bassebete. Veja 1Cr 11.11., um tacmonita23.8 Provavelmente variante de hacmonita. Veja 1Cr 11.11., chefe dos três guerreiros principais; numa ocasião, com uma lança, enfrentou23.8 Conforme alguns manuscritos da Septuaginta. O Texto Massorético e outros manuscritos da Septuaginta dizem três; foi o esnita Adino que matou oitocentos homens. Veja 1Cr 11.11. oitocentos homens numa mesma batalha e os matou.

9Depois dele, Eleazar, filho do aoíta Dodô. Ele era um dos três principais guerreiros e esteve com Davi quando os filisteus se reuniram em Pas-Damim para a batalha. Os israelitas recuaram, 10mas ele manteve a sua posição e feriu os filisteus até a sua mão ficar dormente e grudar na espada. O Senhor concedeu uma grande vitória a Israel naquele dia, e o exército voltou para onde Eleazar estava, mas somente para saquear os mortos.

11Depois dele, Samá, filho de Agé, de Harar. Os filisteus reuniram-se em Leí, onde havia uma plantação de lentilha. O exército de Israel fugiu dos filisteus, 12mas Samá tomou posição no meio da plantação, defendeu-a e derrotou os filisteus. O Senhor concedeu-lhe uma grande vitória.

13Durante a colheita, três chefes do batalhão dos Trinta foram encontrar Davi na caverna de Adulão, enquanto um grupo de filisteus acampava no vale de Refaim. 14Estando Davi nessa fortaleza e o destacamento filisteu em Belém, 15Davi expressou este forte desejo: “Quem me dera me trouxessem água da cisterna da porta de Belém!” 16Então aqueles três atravessaram o acampamento filisteu, tiraram água da cisterna e a trouxeram a Davi. Mas ele se recusou a beber; em vez disso, derramou-a como oferta ao Senhor e disse: 17“O Senhor me livre de beber desta água! Seria como beber o sangue dos que arriscaram a vida para trazê-la!” E Davi não bebeu daquela água.

Foram esses os feitos dos três principais guerreiros.

18Abisai, irmão de Joabe e filho de Zeruia, era o chefe do batalhão dos Trinta23.18 Conforme a maioria dos manuscritos do Texto Massorético. Dois manuscritos do Texto Massorético e a Versão Siríaca dizem chefe dos três. Veja 1Cr 11.20.. Certa ocasião, com sua lança matou trezentos homens, tornando-se tão famoso quanto os três. 19Foi mais honrado que o batalhão dos Trinta e tornou-se o chefe deles. Mas nunca igualou-se aos três principais guerreiros.

20Benaia, filho de Joiada, era um corajoso soldado de Cabzeel, que realizou grandes feitos. Matou dois dos melhores guerreiros de Moabe e, num dia de neve, desceu num buraco e matou um leão. 21Também matou um egípcio de grande estatura. O egípcio tinha na mão uma lança, e Benaia o enfrentou com um cajado. Arrancou a lança da mão do egípcio e com ela o matou. 22Esses foram os grandes feitos de Benaia, filho de Joiada, que também teve fama como os três principais guerreiros de Davi. 23Foi mais honrado do que qualquer dos Trinta, mas nunca igualou-se aos três. E Davi lhe deu o comando da sua guarda pessoal.

24Entre os Trinta estavam:

Asael, irmão de Joabe;

Elanã, filho de Dodô, de Belém;

25Samá e Elica, de Harode;

26Helez, de Pelete;

Ira, filho de Iques, de Tecoa;

27Abiezer, de Anatote;

Mebunai23.27 Alguns manuscritos da Septuaginta dizem Sibecai. Veja 1Cr 11.29., de Husate;

28Zalmom, de Aoí;

Maarai, de Netofate;

29Helede23.29 Muitos manuscritos dizem Helebe. Veja 1Cr 11.30., filho de Baaná, de Netofate;

Itai, filho de Ribai, de Gibeá de Benjamim;

30Benaia, de Piratom;

Hidai23.30 Alguns manuscritos da Septuaginta dizem Hurai. Veja 1Cr 11.32., dos riachos de Gaás;

31Abi-Albom, de Arbate;

Azmavete, de Baurim;

32Eliaba, de Saalbom;

os filhos de Jasém;

Jônatas, 33filho de23.33 Conforme alguns manuscritos da Septuaginta. O Texto Massorético não diz filho de. Veja 1Cr 11.34. Samá, de Harar;

Aião, filho de Sarar23.33 Alguns manuscritos dizem Sacar. Veja 1Cr 11.35., de Harar;

34Elifelete, filho de Aasbai, de Maaca;

Eliã, filho de Aitofel, de Gilo;

35Hezrai, de Carmelo;

Paarai, de Arabe;

36Igal, filho de Natã, de Zobá;

o filho de Hagri23.36 Vários manuscritos dizem Hagadi. Veja 1Cr 11.38.;

37Zeleque, de Amom;

Naarai, de Beerote, escudeiro de Joabe, filho de Zeruia;

38Ira e Garebe, de Jatir;

39e o hitita Urias.

Foram ao todo trinta e sete.