1 ዜና መዋዕል 8 – NASV & HTB

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 8:1-40

የብንያማዊው የሳኦል ትውልድ ሐረግ

8፥28-38 ተጓ ምብ – 1ዜና 9፥34-44

1ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣

ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣

2አራተኛ ልጁን ኖሐን፣ አምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ።

3የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤

አዳር፣ ጌራ፣ አቢሁድ፣8፥3 ወይም፣ የሁድ አባት ጌራ 4አቢሱ፣ ናዕማን፣ አሖዋ፣ 5ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።

6በጌባ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤

7ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።

8ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ። 9ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣ 10ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው። 11ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።

12የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤

ዔቤር፣ ሚሻም እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞችን ከነመንደሮቻቸው የቈረቈረ ሻሜድ፣ 13በኤሎን ይኖሩ ለነበሩ ቤተ ሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።

14አሒዮ፣ ሻሻቅ፣ ይሬምት፣ 15ዝባድያ፣ ዓራድ፣ ዔድር፣ 16ሚካኤል፣ ይሽጳና ዮሐ የበሪዓ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

17ዝባድያ፣ ሜሱላም፣ ሕዝቂ፣ ሔቤር፣ 18ይሽምራይ፣ ይዝሊያና ዮባብ የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።

19ያቂም፣ ዝክሪ፣ ዘብዲ፣ 20ኤሊዔናይ፣ ጺልታይ፣ ኤሊኤል፣ 21ዓዳያ፣ ብራያና ሺምራት የሰሜኢ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

22ይሽጳን፣ ዔቤር፣ ኤሊኤል፣ 23ዓብዶን፣ ዝክሪ፣ ሐናን፣ 24ሐናንያ፣ ኤላም፣ ዓንቶትያ 25ይፍዴያና ፋኑኤል የሶሴቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

26ሽምሽራይ፣ ሽሃሪያ፣ ጎቶልያ፣ 27ያሬሽያ፣ ኤልያስና፣ ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።

28እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

29የገባዖን አባት8፥29 አባት ማለት፣ የማኅበረ ሰብ መሪ ወይም የጦር መሪ ማለት ነው። ይዒኤል8፥29 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (1ዜና 9፥35 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ይዒኤል የሚለውን አይጨምርም በገባዖን ኖረ፤ ሚስቱ መዓካ ትባል ነበር።

30የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ ባኣል፣ ኔር፣8፥30 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም 1ዜና 9፥36 ይመ) ከዚህ ጋር ይሰማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ “ኔር” የሚለውን ስም አይጨምርም ናዳብ፣ 31ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩርና 32የሺምዓ አባት ሚቅሎት ነበሩ። እነዚህም ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ከተማ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።

33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን8፥33 ሜፊቦሼት በመባልም ይታወቃል ወለደ።

34የዮናታን ወንድ ልጅ

መሪበኣል8፥34 ሜፈቦሼት በመባልም ይታወቃል፤ እርሱም ሚካን ወለደ።

35የሚካ ወንዶች ልጆች፤

ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።

36አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ። 37ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ፤ ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።

38ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦

ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሽዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ይባላል፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።

39የወንድሙ የኤሴቅ ወንዶች ልጆች፤

የበኵር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛ ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛ ልጁ ኤሊፋላት። 40የኡላም ልጆች በቀስት መንደፍ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ እነርሱም በአጠቃላይ ቍጥራቸው አንድ መቶ ሃምሳ ወንዶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ትውልዶች ነበሩ።

Het Boek

1 Kronieken 8:1-40

1Benjamin verwekte Béla, zijn eerstgeborene, Asj-bel als tweede, Achrach als derde. 2Nocha als vierde, Rafa als vijfde. 3Béla had de volgende kinderen: Addar, Gera, Abihoed, 4Abisjóea, Naäman en Achóach. 5Gera, Sjefoefam en Choeram 6waren zonen van Echoed; ze waren familiehoofden van de bewoners van Géba, en werden verbannen naar Manáchat. 7Het was Gera met Naäman en Achi-ja, die ze verbande. Gera verwekte Oezza en Achihoed. 8Sjacharáim verwekte in de velden van Moab, nadat hij zijn vrouwen Choesjim en Baraä had weggezonden, 9bij zijn vrouw Chódesj: Jobab, Sibja, Mesja, Malkam, 10Jeoes, Sakeja en Mirma; dit waren zijn zonen, allen familiehoofden. 11Van Choesjim had hij Abitoeb en Elpáal gekregen. 12De zonen van Elpáal waren: Éber, Misjam en Sjemed; dezen bouwden Ono en Loed met bijbehorende plaatsen. 13Beria en Sjéma waren de familiehoofden van de bewoners van Ajjalon. Zij joegen de bewoners van Gat op de vlucht; 14hun broeders heetten Elpáal, Sjasjak en Jerimot. 15Zebadja, Arad, Eder, 16Mikaël, Jisjpa en Jocha waren zonen van Beria. 17Zebadja, Mesjoellam, Chizki, Cheber, 18Jisjmerai, Jizlia en Jobab waren zonen van Elpáal. 19Jakim, Zikri, Zabdi, 20Eliënai, Silletai, Eliël, 21Adaja, Beraja en Sjimrat waren zonen van Sjimi. 22Jisjpan, Éber, Eliël, 23Abdon, Zikri, Chanan, 24Chananja, Elam, Antoti-ja, 25Jifdeja en Penoeël waren zonen van Sjasjak. 26Sjamsjerai, Sjecharja, Atalja, 27Jaäresjja, Eli-ja en Zikri waren zonen van Jerocham. 28Dit waren de familiehoofden naar hun geslachten, die in Jerusalem woonden. 29In Gibon woonde de stamvader van Gibon; zijn vrouw heette Maäka. 30Zijn oudste zoon was Abdon; verder Soer, Kisj, Báal, Ner, Nadab, 31Gedor, Achjo, Zéker en Miklot. 32Miklot verwekte Sjima; ook dezen woonden bij hun stamgenoten in Jerusalem, in hun nabijheid. 33Ner verwekte Kisj; Kisj verwekte Saul; Saul verwekte Jonatan, Malkisjóea, Abinadab en Esjbáal. 34De zoon van Jonatan was Merib-Báal; Merib-Báal verwekte Mika. 35De zonen van Mika waren: Piton, Mélek, Taréa en Achaz. 36Achaz verwekte Jehoadda; Jehoadda verwekte Alémet, Azmáwet en Zimri; Zimri verwekte Mosa; 37Mosa verwekte Bina. Diens zoon was Rafa; die van Rafa was Elasa; die van Elasa was Asel. 38Asel had zes kinderen, die aldus heetten: Azrikam, Bokeroe, Jisjmaël, Sjearja, Obadja en Chanan; allen zonen van Asel. 39De zonen van zijn broer Ésjek waren Oelam de oudste, Jeöesj de tweede en Elifélet de derde. 40De zonen van Oelam waren dappere mannen, die de boog konden spannen en veel kinderen en kleinkinderen hadden, wel honderd vijftig. Dit waren allemaal afstammelingen van Benjamin.