እግዚአብሔር ለዳዊት የሰጠው ተስፋ
17፥1-15 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 7፥1-17
1ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፣ ነቢዩ ናታንን “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።
2ናታንም ለዳዊት፣ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለሆነ፣ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት።
3በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጥቶ እንዲህ አለው፤
4“ሂድና ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም። 5እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱ ማደሪያ ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣ በቤት ውስጥ አልኖርሁም። 6ከእስራኤላውያን ጋር በሄድሁባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ ሕዝቤን እንዲጠብቁ ላዘዝኋቸው መሪዎቻቸው17፥6 በዚህና በቍጥር 10 ላይ በትውፊት፣ መሳፍንት ይባላል ከቶ፣ “ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሠራችሁልኝም” ያልሁበት ጊዜ አለን?’
7“እንግዲህ አሁንም ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘የሕዝቤ የእስራኤል ገዥ እንድትሆን በጎችን ከመጠበቅና ከመከተል አንሥቼ ወሰድሁህ። 8በሄድህበት ሁሉ ከአንተ አልተለየሁም፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁልህ፤ አሁንም ስምህን እንደ ምድር ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ። 9ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው፣ ከእንግዲህም በኋላ እንዳይናወጡ አደርጋቸዋለሁ። ክፉ ሰዎች በመጀመሪያ እንዳደረጉት ሁሉ፣ ከእንግዲህ አይጨቍኗቸውም፤ 10ከዚህ ቀደም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪዎች በሾምሁ ጊዜ ጨቋኞቹ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉትም፤ ጠላቶቻችሁን ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ።
“ ‘እግዚአብሔር ቤት እንደሚሠራልህ በግልጽ እነግርሃለሁ፤ 11ዘመንህን ጨርሰህ ወደ አባቶችህ በምትሄድበት ጊዜ፣ ከአብራክህ ከተከፈሉት ልጆችህ አንዱ በእግርህ እንዲተካ አደርጋለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለታለሁ፤ 12ቤት የሚሠራልኝም እርሱ ነው፤ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ። 13አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደ ወሰድሁ፣ ከእርሱ ላይ ከቶ አልወስድም። 14በቤቴና በመንግሥቴ ላይ ለዘላለም አኖረዋለሁ፤ ዙፋኑም ለዘላለም ይጸናል።’ ”
15ናታንም የዚህን ሁሉ ራእይ ቃል ለዳዊት ነገረው።
የዳዊት ጸሎት
17፥16-27 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 7፥18-29
16ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦም እንዲህ አለ፤
“እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ለመሆኑ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤተ ሰቤስ ምንድን ነው? 17አምላክ ሆይ፤ ይህ በፊትህ በቂ እንዳልሆነ ቈጥረህ ስለ ወደ ፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገርህ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ እኔንም ከሰዎች ሁሉ እጅግ የከበረ ሰው አድርገህ ተመለከትኸኝ።
18“ባሪያህን ስላከበርኸው፣ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ማለት ይችላል? ባሪያህን እኮ ታውቀዋለህ፤ 19እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ባሪያህ ብለህና እንደ ፈቃድህም መሠረት ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ እነዚህም ታላላቅ ተስፋዎች ሁሉ እንዲታወቁ አደረግህ።
20“አቤቱ፤ እንደ አንተ ያለ የለም፤ በጆሯችን እንደ ሰማነው ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም። 21ከግብፅ ተቤዥተህ እንዳወጣኸው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ማን አለ? እነርሱ እግዚአብሔር ለራሱ ሊቤዣቸው ከምድር ሕዝቦች መካከል የመረጣቸው ናቸው፤ በሕዝብህም ፊት ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ መንግሥታትን በፊታቸው አሳደድህ። 22ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም የራስህ ሕዝብ አደረግኸው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተም አምላክ ሆንህለት።
23“እግዚአብሔር ሆይ፤ አሁንም ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የሰጠኸው ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤ የሰጠኸውንም ተስፋ ፈጽም፤ 24ይህም ስምህ ጸንቶ እንዲኖርና ለዘላለምም ታላቅ እንዲሆን ነው። ከዚያም ሰዎች ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው!’ ይላሉ፤ የባሪያህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።
25“አምላኬ ሆይ፤ ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ። 26እግዚአብሔር ሆይ፤ በእውነት አንተ አምላክ ነህ፤ ይህንም መልካም ተስፋ ለባሪያህ ሰጥተሃል። 27በፊትህ ለዘላለም እንዲኖር አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወድደሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የባረክኸው አንተ ስለ ሆንህ፣ ለዘላለም የተባረከ ይሆናል።”
وعدهٔ خداوند به داوود
(دوم سموئيل 7:1-17)
1پس از آنكه داوود در كاخ سلطنتی خود ساكن شد، روزی به ناتان نبی گفت: «من در اين كاخ زيبا كه با چوب سرو ساخته شده است زندگی میكنم، در حالی كه صندوق عهد خداوند در يک خيمه نگهداری میشود!»
2ناتان در جواب داوود گفت: «آنچه را كه در نظر داری انجام بده زيرا خدا با توست.»
3ولی همان شب خدا به ناتان فرمود 4كه برود و به خدمتگزار او داوود چنين بگويد: «تو آن كسی نيستی كه بايد برای من خانهای بسازد. 5زيرا من هرگز در ساختمانی ساكن نبودهام. از آن زمان كه بنیاسرائيل را از مصر بيرون آوردم تا به امروز خانهٔ من يک خيمه بوده است و از جايی به جای ديگر در حركت بودهام. 6در طول اين مدت هرگز به هيچكدام از رهبران اسرائيل كه آنها را برای شبانی قوم خود تعيين نموده بودم، نگفتم كه چرا برايم خانهای از چوب سرو نساختهايد؟
7«و حال خداوند قادر متعال میفرمايد كه وقتی چوپان سادهای بيش نبودی و در چراگاهها از گوسفندان نگهداری میكردی، تو را به رهبری قوم اسرائيل برگزيدم. 8هر جايی كه رفتهای با تو بودهام و دشمنانت را نابود كردهام. تو را از اين هم بزرگتر میكنم تا يكی از معروفترين مردان دنيا شوی! 9-10برای قوم خود سرزمينی انتخاب كردم تا در آن سروسامان بگيرند. اين وطن آنها خواهد بود و قومهای بتپرست ديگر مثل سابق كه قوم من تازه وارد اين سرزمين شده بود، بر آنها ظلم نخواهند كرد. تو را از شر تمام دشمنانت حفظ خواهم كرد. اين منم كه خانهٔ تو را میسازم. 11وقتی تو بميری و به اجدادت ملحق شوی، من يكی از پسرانت را وارث تاج و تخت تو میسازم و حكومت او را تثبيت میكنم. 12او همان كسی است كه خانهای برای من میسازد. من سلطنت او را تا به ابد پايدار میكنم. 13من پدر او و او پسر من خواهد بود و محبت من از او دور نخواهد شد، آن طور كه از شائول دور شد. 14تا به ابد او را بر قوم خود و سرزمين اسرائيل خواهم گماشت و فرزندانش هميشه پادشاه خواهند بود.»
15پس ناتان نزد داوود بازگشت و آنچه را كه خداوند فرموده بود به او بازگفت.
دعای داوود
(دوم سموئيل 7:18-29)
16آنگاه داوود به خيمهٔ عبادت رفت و در آنجا نشسته، در حضور خداوند چنين دعا كرد: «ای خداوند، من كيستم و خاندان من چيست كه مرا به اين مقام رساندهای؟ 17به اين هم اكتفا نكردی بلكه به نسل آيندهٔ من نيز وعدهها دادی. ای خداوند، تو مرا از همهٔ مردم سرافرازتر كردهای. 18ديگر چه بگويم كه تو میدانی من نالايق هستم ولی با وجود اين سرافرازم كردهای. 19اين خواست تو بود كه به خاطر خدمتگزارت داوود اين كارهای بزرگ را انجام دهی و وعدههای عظيم را نصيب خدمتگزارت گردانی. 20هرگز نشنيدهايم كه خدايی مثل تو وجود داشته باشد! تو خدای بینظيری هستی! 21در سراسر دنيا، كدام قوم است كه مثل قوم تو، بنیاسرائيل، چنين بركاتی يافته باشد؟ تو بنیاسرائيل را رهانيدی تا از آنها برای خود قومی بسازی و نامت را جلال دهی. با معجزات عظيم، مصر را نابود كردی. 22بنیاسرائيل را تا به ابد قوم خود ساختی و تو ای خداوند، خدای ايشان شدی.
23«ای خداوند باشد آنچه كه دربارهٔ من و خاندانم وعده فرمودهای، به انجام رسد. 24اسم تو تا به ابد ستوده شود و پايدار بماند و مردم بگويند: خداوند قادر متعال، خدای اسرائيل است. تو خاندان مرا تا به ابد حفظ خواهی كرد. 25ای خداوند من، تو به من وعده دادی كه خاندانم تا به ابد بر قوم تو سلطنت كند. به همين سبب است كه جرأت كردهام چنين دعايی در حضورت بنمايم. 26ای خداوند تو واقعاً خدا هستی و تو اين چيزهای خوب را به من وعده فرمودهای. 27ای خداوند، بگذار اين بركت هميشه از آن فرزندان من باشد زيرا وقتی تو بركت میدهی، بركت تو ابدی است.»