1 ነገሥት 8 – NASV & PCB

New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 8:1-66

ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ

8፥1-21 ተጓ ምብ – 2ዜና 5፥2–6፥11

1ከዚያም ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ለማምጣት፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የእስራኤልን ነገድ አለቆችና የእስራኤልን ጐሣዎች ሹማምት ሁሉ እርሱ ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ጠራቸው። 2በዓሉ በሚከበርበት ኤታኒም በተባለው በሰባተኛው ወር፣ የእስራኤል ወንዶች ሁሉ ንጉሥ ሰሎሞን ወዳለበት ተሰበሰቡ።

3የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በመጡ ጊዜም ካህናቱ ታቦቱን አነሡ፤ 4የእግዚአብሔርን ታቦት፣ የመገናኛውን ድንኳንና በውስጡ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አመጡ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ይህን ሁሉ ተሸከሙ። 5ንጉሥ ሰሎሞንና አብሮት በዚያ የተሰበሰበው መላው የእስራኤል ጉባኤም በታቦቱ ፊት በመሆን ስፍር ቍጥር የሌለው በግና በሬ ሠዋ።

6ከዚያም ካህናቱ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አምጥተው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወዳለው ማደሪያው፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በማስገባት ከኪሩቤል ክንፍ በታች አኖሩት። 7ኪሩቤልም ታቦቱ ባለበት ቦታ ላይ ክንፋቸውን ዘርግተው፣ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን ጋረዱ። 8መሎጊያዎቹ ከመርዘማቸው የተነሣ ጫፎቻቸው ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ካለው ከመቅደሱ ሆኖ ይታዩ ነበር፤ ከመቅደሱ ወዲያ ላለ ሰው ግን አይታዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያው ይገኛሉ። 9የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ኪዳን በገባበት በኮሬብ፣ ሙሴ በታቦቱ ውስጥ ካስቀመጣቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም።

10ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ በወጡ ጊዜ፣ ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሞላው። 11የእግዚአብሔር ክብር ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ስለ ነበር፣ ካህናቱ በደመናው ምክንያት አገልግሎታቸውን ማከናወን አልቻሉም ነበር።

12ከዚያም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ጥቅጥቅ ባለ ደመና ውስጥ እንደሚኖር ተናግሯል፤ 13እነሆ፣ እኔም ለዘላለም የምትኖርበትን ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርቼልሃለሁ።”

14መላው የእስራኤል ጉባኤ በዚያ ቆሞ ሳለ፣ ንጉሡ ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ ጉባኤውን ባረከ። 15ከዚያም እንዲህ አለ፤

“ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ ተናግሮ የሰጠውን ተስፋ፣ እርሱ ራሱ በእጁ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበርና፤ 16‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ዕለት አንሥቶ፣ ስሜ በዚያ እንዲጠራና ቤተ መቅደስ እንዲሠራበት ከመላው የእስራኤል ነገድ አንድም ከተማ አልመረጥሁም፤ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲመራ ግን ዳዊትን መረጥሁት።’

17“አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ለመሥራት በልቡ ዐስቦ ነበር፤ 18እግዚአብሔር ግን አባቴን ዳዊትን እንዲህ አለው፤ ‘ለስሜ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አስበሃልና፣ ይህን በልብህ ማሰብህ መልካም ነው፤ 19ይሁን እንጂ ቤተ መቅደሱን የምትሠራው አንተ ሳትሆን፣ ከአንተ የሚወለደው ልጅህ ነው፤ አዎን ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው።’

20እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ፈጽሟል፤ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት፣ በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቻለሁ፤ በእስራኤል ዙፋን ተቀምጫለሁ፤ እንዲሁም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ሠርቻለሁ። 21ከግብፅ ባወጣቸው ጊዜ ከአባቶቻችን ጋር የገባው የእግዚአብሔር ኪዳን በውስጡ ላለበት ታቦት መኖሪያ ስፍራ በዚያ አዘጋጅቻለሁ።”

ሰሎሞን በምረቃው ላይ ያቀረበው ጸሎት

8፥22-53 ተጓ ምብ – 2ዜና 6፥12-40

22ከዚያም ሰሎሞን መላው የእስራኤል ጉባኤ ባለበት በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ፣ 23እንዲህ አለ፤

“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በፊትህ በፍጹም ልባቸው ጸንተው ለሚኖሩ አገልጋዮችህ ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ጽኑ ፍቅርህን የምትገልጥ አንተ ነህ፤ በላይ በሰማይ፣ በታችም በምድር እንደ አንተ ያለ አምላክ ከቶ የለም፤ 24ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ ጠብቀሃል፤ በአፍህ ተናገርህ፤ ይህንኑም በዛሬው ዕለት በእጅህ ፈጸምኸው።

25“አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ለአባቴ ለባሪያህ ለዳዊት፣ ‘አንተ እንደ አደረግኸው ሁሉ፣ ልጆችህ በፊቴ ለመመላለስ በሚያደርጉት ሁሉ ይጠንቀቁ ብቻ እንጂ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚቀመጥ ሰው አታጣም’ ስትል የሰጠኸውን ተስፋ ፈጽምለት። 26አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም።

27“ነገር ግን አምላክ በርግጥ በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፤ ሰማይ፣ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ እንኳ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምኑ ሊበቃ! 28አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህም ሆኖ የባሪያህን ጸሎትና ልመና ስማ፤ በዛሬው ዕለት ባሪያህ በፊትህ የሚያቀርበውን ጩኸትና ልመና አድምጥ። 29ባሪያህ ወደዚህ ቦታ የሚያቀርበውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’ ወደ አልኸው በዚህ ስፍራ ወዳለው ቤተ መቅደስ ዐይኖችህ ሌትና ቀን የተከፈቱ ይሁኑ። 30ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ ጸሎት በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ልመናቸውን ተቀበል፤ መኖሪያህ በሆነው በሰማይ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል።

31“አንድ ሰው ባልንጀራውን በድሎ መማል ኖሮበት ቢመጣና በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ በመሠዊያህ ፊት ቢምል፣ 32ይህን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፤ ለበደለኛው ስለ አድራጎቱ የእጁን ክፈል፤ ከበደል ነጻ ለሆነውም ንጽሕናውን ይፋ በማድረግ ይህንኑ አረጋግጥለት።

33“ሕዝብህ እስራኤል አንተን ከመበደላቸው የተነሣ፣ በጠላቶቻቸው ድል በሚሆኑበት ጊዜ፣ ወደ አንተም ተመልሰው ስምህን ቢጠሩ፣ በዚህም ቤተ መቅደስ ወደ አንተ ቢጸልዩና ልመናቸውን ቢያቀርቡ፣ 34በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የሕዝብህ የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸውም ምድር መልሰህ አግባቸው።

35“ሕዝቡም አንተን ከመበደላቸው የተነሣ፣ ሰማዩ ተዘግቶ ዝናብ ሳይዘንብ ቢቀር፣ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩና ስምህን ቢጠሩ፣ ስላስጨነቅሃቸውም ከበደላቸው ቢመለሱ፣ 36በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የባሪያዎችህን የሕዝብህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ የሚሄዱበትን ቀናውን መንገድ አስተምራቸው፤ ርስት አድርገህ ለሕዝብህ ለሰጠሃትም ምድር ዝናብ አውርድ።

37“በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት፣ ዋግ ወይም አረማሞ በሚከሠትበት፣ አንበጣ ወይም ኵብኵባ በሚወርድበት ወይም በምድራቸው ውስጥ ባሉት ከተሞቻቸው ጠላት ቢከብባቸው፣ እንዲሁም ማንኛውም ዐይነት ጥፋት ወይም በሽታ በሚመጣባቸው ጊዜ፣ 38ከሕዝብህ ከእስራኤል ማንኛውም ሰው የልቡን ጭንቀት ዐውቆ እጆቹን ወደዚህ ቤት በመዘርጋት ጸሎትና ልመና በሚያቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ 39በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ይቅር በል፤ አድርግም። አንተ ብቻ የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቅ ስለ ሆንህ ልቡን ለምታውቀው ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ሁሉ ክፈለው፤ 40ይህም እነርሱ ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ፣ አንተን እንዲፈሩ ነው።

41“ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ፣ ግን ከስምህ ታላቅነት የተነሣ ከሩቅ የመጣ የባዕድ አገር ሰው ቢኖር፣ 42ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፣ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፣ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፣ 43አንተ በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የጠየቀህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ይኸውም የምድር ሕዝቦች ሁሉ ስምህን ዐውቀው፣ ሕዝብህ እስራኤል አንተን እንደሚፈሩት ሁሉ እንዲፈሩህ፣ እኔ የሠራሁትም ይህ ቤት በስምህ መጠራቱን እንዲያውቁ ነው።

44“ሕዝብህ ጠላታቸውን ለመውጋት አንተ ወደምትልካቸው ወደ የትኛውም ቦታ ለጦርነት በሚወጡበት ጊዜ፣ አንተ ወደ መረጥሃት ከተማና እኔ ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ለእግዚአብሔር ቢጸልዩ፣ 45ጸሎትና ልመናቸውን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ርዳቸውም።

46“መቼም ኀጢአት የማይሠራ የለምና ሕዝብህ በአንተ ላይ ኀጢአት ቢሠሩ፣ አንተም ተቈጥተህ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነው ምድሩ ማርኮ ለሚወስደው ጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ 47ተማርከው በሚኖሩበት አገር ሳሉ ልባቸው ቢመለስ፣ በተማረኩበትም ምድር ሆነው ንስሓ ቢገቡና ‘ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’ ብለው ቢለምኑህ፣ 48እንዲሁም ማርከው በወሰዷቸው ጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፣ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃት ወደዚህች ምድር፣ ወደ መረጥሃትም ወደዚህች ከተማና እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፣ 49ከማደሪያህ ከሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ ልመናቸውንም ተቀበል፤ ርዳቸውም። 50በአንተ ላይ ስለ ሠሩት ኀጢአት፣ አንተንም ስለ በደሉህ በደል ሁሉ ሕዝብህን ይቅር በል፤ የማረኳቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ። 51ከዚያች እንደ ብረት ማቅለጫ እቶን እሳት ከሆነችው፣ ከግብፅ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህም ርስትህም ናቸውና።

52“አሁንም ዐይኖችህ ለባሪያህና ለሕዝብህ ለእስራኤል ልመና የተከፈቱ ይሁኑ፤ ወደ አንተ በሚጮኹበትም ጊዜ ሁሉ ስማቸው፤ 53አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፤ አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ፣ በባሪያህ በሙሴ አማካይነት እንደ ተናገርኸው ሁሉ፣ ርስትህ ይሆኑ ዘንድ ከምድር ሕዝቦች ሁሉ ለይተሃቸዋልና።”

54ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ጸሎትና ልመና ለእግዚአብሔር አቅርቦ ከፈጸመ በኋላ፣ እጆቹን ወደ ሰማይ በመዘርጋት፣ በጕልበቱ ተንበርክኮ ከነበረበት ከእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ተነሣ። 55ከዚያም ቆሞ መላውን የእስራኤልን ጉባኤ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ ሲል መረቀ፤

56“በሰጠው ተስፋ መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን ለሰጠ እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው፤ በባሪያው በሙሴ አማካይነት ከተሰጠው መልካም ተስፋ ሁሉ አንድም ቃል አልቀረምና። 57አምላካችን እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ጋር እንደ ነበረ ሁሉ ከእኛም ጋር ይሁን፤ አይተወን፤ አይጣለንም። 58በመንገዱም ሁሉ እንድንሄድ፣ ለአባቶቻችን የሰጣቸውን ትእዛዞች፣ ሥርዐቶችና ደንቦች እንድንጠብቅ ልባችንን ወደ እርሱ ይመልስ። 59በየዕለቱም ባሪያውንና ሕዝቡን እስራኤልን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ እንዲረዳቸው፣ ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያቀረብኋት የራሴ ልመና በቀንና በሌሊት ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ፊት ትቅረብ። 60ይኸውም የምድር ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ እንደ ሆነና ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ነው። 61ስለዚህ እንደ ዛሬው ዕለት ሁሉ፣ በሥርዐቱ እንድትኖሩና ትእዛዙን እንድትጠብቁ ልባችሁ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የተገዛ ይሁን።”

የቤተ መቅደሱ መመረቅ

8፥62-66 ተጓ ምብ – 2ዜና 7፥1-10

62ከዚያም ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት እስራኤል ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት አቀረቡ። 63ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል የኅብረት መሥዋዕት8፥63 በዚህና በ64 ላይ በትውፊት፣ የሰላም መሥዋዕት ይባላል። አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ንጉሡና እስራኤላውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።

64በዚያኑ ዕለትም ንጉሡ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ያለውን የአደባባዩን መካከለኛ ክፍል ቀደሰ፤ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የኅብረት መሥዋዕቱን ሥብ አቀረበ፤ ይህን ያደረገውም በእግዚአብሔር ፊት የነበረው የናስ መሠዊያ ከትንሽነቱ የተነሣ የሚቃጠለውን መሥዋዕት የእህሉን ቍርባንና የኅብረት መሥዋዕቱን ስብ መያዝ ባለመቻሉ ነበር።

65በዚያን ጊዜም ሰሎሞን አብረውት ካሉት የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋር፣ ማለትም ከሐማት መተላለፊያ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ8፥65 ወይም ከመግቢያው ጀምሮ ተብሎ መተርጐም ይችላል። ካለው ምድር ከተሰበሰበው ታላቅ ጉባኤ ጋር በዓሉን አከበረ። እነርሱም ሰባት ቀን፣ በተጨማሪም ሌላ ሰባት ቀን በድምሩ ዐሥራ አራት ቀን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በዓሉን አከበሩ። 66በሚቀጥለው ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ ሕዝቡም ንጉሡን መረቁ፤ እግዚአብሔር ለባሪያው ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ባደረገው በጎ ነገር ሁሉ ከልብ ተደስተው ሐሤት በማድረግ ወደየቤታቸው ተመለሱ።

Persian Contemporary Bible

اول پادشاهان 8:1-66

صندوق عهد به خانهٔ خدا منتقل می‌شود

(دوم تواريخ 5‏:2 تا 6‏:2)

1آنگاه سليمان پادشاه تمام سران قبايل و طوايف قوم اسرائيل را به اورشليم دعوت كرد تا صندوق عهد خداوند را كه در صهيون، شهر داوود بود به خانه خدا بياورند. 2همهٔ آنها در روزهای عيد خيمه‌ها در ماه ايتانيم كه ماه هفتم است در اورشليم جمع شدند. 3‏-4آنگاه كاهنان و لاويان صندوق عهد و خيمه عبادت را با تمام ظروف مقدسی كه در آن بود، به خانه خدا آوردند. 5سپس سليمان پادشاه و تمام بنی‌اسرائيل در برابر صندوق عهد خداوند جمع شدند و در آن روز تعداد زيادی گاو و گوسفند قربانی كردند. تعداد گاو و گوسفند قربانی شده آنقدر زياد بود كه نمی‌شد شمرد.

6سپس كاهنان، صندوق عهد را به درون قدس‌الاقداس خانهٔ خداوند بردند و آن را زير بالهای آن دو مجسمهٔ فرشته قرار دادند. 7مجسمهٔ فرشته‌ها طوری ساخته شده بود كه بالهايشان روی صندوق عهد خداوند و روی چوبهای حامل صندوق گسترده می‌شد و آن را می‌پوشاند. 8اين چوبها آنقدر دراز بود كه از داخل اتاق دوم يعنی قدس ديده می‌شدند اما از حياط ديده نمی‌شدند. (اين چوبها هنوز هم در آنجا هستند.) 9در صندوق عهد چيزی جز دو لوح سنگی نبود. وقتی خداوند با قوم خود، پس از بيرون آمدنشان از مصر، در كوه حوريب عهد و پيمان بست، موسی آن دو لوح را در صندوق عهد گذاشت.

10وقتی كاهنان از قدس بيرون می‌آمدند ناگهان ابری خانهٔ خداوند را پر ساخت 11و حضور پرجلال خداوند آن مكان را فرا گرفت به طوری كه كاهنان نتوانستند به خدمت خود ادامه دهند.

12‏-13آنگاه سليمان پادشاه اينطور دعا كرد:

«خداوندا، تو فرموده‌ای كه در ابر غليظ و تاريک ساكن می‌شوی؛ ولی من برای تو خانه‌ای ساخته‌ام تا هميشه در آن منزل گزينی!»

سليمان برای قوم سخنرانی می‌كند

(دوم تواريخ 6‏:3‏-11)

14‏-15سپس پادشاه رو به جماعتی كه ايستاده بودند كرد و ايشان را بركت داده، گفت: «سپاس بر خداوند، خدای اسرائيل كه آنچه را به پدرم داوود وعده داده بود، امروز با قدرت خود بجا آورده است. 16او به پدرم فرمود: از زمانی كه قوم خود را از مصر بيرون آوردم تاكنون در هيچ جای سرزمين اسرائيل هرگز شهری را انتخاب نكرده‌ام تا در آنجا خانه‌ای برای حرمت نام من بنا شود ولی داوود را انتخاب كرده‌ام تا بر قوم من حكومت كند.

17«پدرم داوود می‌خواست خانه‌ای برای خداوند، خدای اسرائيل بنا كند، 18اما خداوند به او فرمود: قصد و نيت تو خوب است، 19اما كسی كه بايد خانه خدا را بسازد تو نيستی؛ پسر تو خانهٔ مرا بنا خواهد كرد. 20حال، خداوند به وعدهٔ خود وفا كرده است. زيرا من به جای پدرم بر تخت سلطنت اسرائيل نشسته‌ام و اين خانه را برای عبادت خداوند، خدای اسرائيل ساخته‌ام، 21و در آنجا مكانی برای صندوق عهد آماده كرده‌ام عهدی كه خداوند هنگامی كه اجداد ما را از مصر بيرون آورد، با ايشان بست.»

دعای سليمان

(دوم تواريخ 6‏:12‏-42)

22‏-23آنگاه سليمان در حضور جماعت اسرائيل، روبروی قربانگاه خداوند ايستاده، دستهای خود را به طرف آسمان بلند كرد و گفت: «ای خداوند، خدای اسرائيل، در تمام زمين و آسمان خدايی همانند تو وجود ندارد. تو خدايی هستی كه عهد پر از رحمت خود را با كسانی كه با تمام دل احكام تو را اطاعت می‌كنند نگاه می‌داری. 24تو به وعده‌ای كه به بندهٔ خود، پدرم داوود دادی، امروز وفا كرده‌ای. 25پس ای خداوند، خدای اسرائيل، اينک به اين وعده‌ای هم كه به پدرم دادی وفا كن كه فرمودی: اگر فرزندان تو مانند خودت مطيع دستورات من باشند هميشه کسی از نسل تو بر اسرائيل پادشاهی خواهد كرد. 26اكنون ای خدای اسرائيل، از تو خواستارم كه اين وعده‌ای را كه به پدرم دادی، به انجام برسانی.

27«ولی آيا ممكن است كه خدا واقعاً روی زمين ساكن شود؟ ای خداوند، حتی آسمانها گنجايش تو را ندارند، چه رسد به اين خانه‌ای كه من ساخته‌ام. 28با وجود اين، ای خداوند، خدای من، تو دعای مرا بشنو و آن را مستجاب فرما. 29چشمان تو شبانه روز بر اين خانه باشد كه برای خود انتخاب كرده‌ای. هر وقت در اين مكان دعا می‌كنم، دعای مرا بشنو و اجابت فرما. 30نه تنها من، بلكه هر وقت قوم تو اسرائيل نيز در اينجا دعا می‌كنند، تو دعای آنها را اجابت فرما و از آسمان كه محل سكونت تو است، استغاثهٔ ايشان را بشنو و گناهانشان را ببخش.

31«هرگاه كسی متهم به جرمی شده باشد و از او بخواهند كنار اين قربانگاه سوگند ياد كند كه بی‌گناه است، 32آنگاه از آسمان بشنو و داوری كن. اگر به دروغ سوگند ياد نموده و مقصر باشد وی را به سزای عملش برسان، در غير اين صورت بی‌گناهی او را ثابت و اعلام كن.

33‏-34«وقتی قوم تو اسرائيل گناه ورزند و مغلوب دشمن شوند، ولی بعد به سوی تو روی آورند و اعتراف نمايند و در اين خانه به درگاه تو دعا كنند، آنگاه از آسمان ايشان را اجابت فرما و گناه قوم خود را بيامرز و بار ديگر آنان را به اين سرزمين كه به اجداد ايشان بخشيده‌ای، بازگردان.

35«اگر قوم تو گناه كنند و دريچهٔ آسمان به سبب گناهشان بسته شود و ديگر باران نبارد، آنگاه كه آنها از گناهشان بازگشت نموده، اعتراف نمايند و در اين خانه به درگاه تو دعا كنند، 36تو از آسمان دعای ايشان را اجابت فرما و گناه بندگان خود را بيامرز و راه راست را به ايشان نشان بده و بر زمينی كه به قوم خود به ملكيت داده‌ای باران بفرست.

37«هرگاه اين سرزمين دچار قحطی يا طاعون شود، يا محصول آن بر اثر بادهای سوزان و هجوم ملخ از بين برود، يا دشمن قوم تو را در شهر محاصره كند و يا هر بلا و مرض ديگری پيش آيد 38و قوم تو، هر يک دستهای خود را به سوی اين خانه دراز كرده، دعا كنند، آنگاه تو ناله‌های ايشان را 39از آسمان كه محل سكونت تو است، بشنو و گناهشان را ببخش. ای خدا تو كه از دل مردم آگاهی، هر كس را برحسب كارهايش جزا بده 40تا قوم تو در اين سرزمينی كه به اجدادشان بخشيده‌ای همواره از تو اطاعت كنند.

41‏-42«وقتی بيگانگان از عظمت نام تو و معجزات شگفت‌انگيزت باخبر شوند و از سرزمينهای دور برای پرستش تو به اينجا بيايند و در اين خانه دعا كنند 43آنگاه از آسمان كه محل سكونت توست، دعای آنها را بشنو و هر چه می‌خواهند به آنها ببخش تا تمام اقوام روی زمين تو را بشناسند و مانند قومت اسرائيل تو را احترام كرده، بدانند كه حضور تو در اين خانه‌ای است كه من ساخته‌ام.

44«اگر قومت به فرمان تو به جنگ دشمن بروند و از ميدان جنگ به سوی اين شهر برگزيدهٔ تو و اين خانه‌ای كه به اسم تو ساخته‌ام نزد تو دعا كنند، 45آنگاه از آسمان دعای ايشان را اجابت فرما و آنها را در جنگ پيروز گردان.

46«اگر قوم تو نسبت به تو گناه كنند و كيست كه گناه نكند؟ و تو بر آنها خشمگين شوی و اجازه دهی دشمن آنها را به كشور خود، خواه دور و خواه نزديک، به اسارت ببرد، 47سپس در آن كشور بيگانه به خود آيند و توبه كرده، به تو پناه آورند و دعا نموده، بگويند: خداوندا، ما به راه خطا رفته‌ايم و مرتكب گناه شده‌ايم! 48و از گناهان خود دست بكشند و به طرف اين سرزمين كه به اجداد ايشان بخشيدی و اين شهر برگزيده‌ات و اين خانه‌ای كه به اسم تو ساخته‌ام دعا كنند، 49آنگاه از آسمان كه محل سكونت توست، دعاها و ناله‌های ايشان را بشنو و به داد آنان برس. 50قوم خود را كه نسبت به تو گناه كرده‌اند بيامرز و تقصيراتشان را ببخش و در دل دشمن نسبت به آنها ترحم ايجاد كن؛ 51زيرا آنها قوم تو و از آن تو هستند و تو ايشان را از اسارت و بندگی مصریان آزاد كردی!

52«ای خداوند، همواره بر بنده‌ات و قومت نظر لطف بفرما و دعاها و ناله‌هايشان را بشنو. 53زيرا وقتی اجداد ما را از سرزمين مصر بيرون آوردی، به بنده خود موسی فرمودی: من قوم اسرائيل را از ميان تمام قومهای جهان انتخاب كرده‌ام تا قوم خاص من باشد!»

دعای بركت سليمان

54‏-55سليمان همانطور كه زانو زده و دستهای خود را به سوی آسمان بلند كرده بود، دعای خود را به پايان رسانيد. سپس از برابر قربانگاه خداوند برخاست و با صدای بلند برای تمام بنی‌اسرائيل بركت طلبيد و گفت:

56«سپاس بر خداوند كه همهٔ وعده‌های خود را در حق ما به انجام رسانيد و به قوم خود آرامش و آسايش بخشيد. خدا به تمام وعده‌های خوبی كه توسط بندهٔ خويش موسی به ما داده بود، وفا نموده است. 57همانگونه كه خداوند، خدای ما، با اجداد ما بود، با ما نيز باشد و هرگز ما را ترک نگويد و وانگذارد. 58او قلبهای ما را به سوی خود مايل گرداند تا ما از او پيروی كنيم و از تمامی احكام و دستوراتی كه به اجداد ما داده؛ اطاعت نماييم. 59خداوند، خدای ما تمام كلمات اين دعا را شب و روز در نظر داشته باشد و برحسب نياز روزانه، مرا و قوم بنی‌اسرائيل را ياری دهد، 60تا همهٔ قومهای جهان بدانند كه فقط خداوند، خداست و غير از او خدای ديگری وجود ندارد. 61ای قوم من، با تمام دل از خداوند، خدايمان پيروی كنيد و مانند امروز، از احكام و دستورات او اطاعت نماييد.»

تقديس خانه خدا

(دوم تواريخ 7‏:4‏-10)

62‏-63سپس پادشاه و تمام مردم قربانیهای سلامتی به خداوند تقديم كردند. جمعاً بيست و دو هزار گاو و صد و بيست هزار گوسفند ذبح شد. به اين ترتيب، خانهٔ خداوند را تبرک نمودند. 64چون قربانگاه مفرغی خانهٔ خداوند گنجايش آن همه قربانیهای سوختنی و هدايای آردی و پيه قربانیهای سلامتی را نداشت پس پادشاه وسط حياط خانه خدا را به عنوان قربانگاه تقديس كرد8‏:64 تقديس يعنی جدا کردن، اختصاص دادن و مقدس ساختن.‏ تا از آنجا نيز استفاده كنند. 65اين جشن چهارده روز طول كشيد و گروه بی‌شماری از سراسر اسرائيل، از گذرگاه حمات گرفته، تا سرحد مصر، در آن شركت كردند. 66روز بعد سليمان مردم را مرخص كرد و آنها به خاطر تمام بركاتی كه خداوند به خدمتگزار خود داوود و قوم خويش اسرائيل عطا كرده بود با خوشحالی به شهرهای خود بازگشتند و برای سلامتی پادشاه دعا كردند.