1 ነገሥት 1 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 1:1-53

አዶንያስ ለመንገሥ እንደ ፈለገ

1ንጉሥ ዳዊት እየሸመገለና ዕድሜው በጣም እየገፋ ሲሄድ፣ ልብስ ቢደራርቡለትም እንኳ ሊሞቀው አልቻለም። 2ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ “ንጉሡን የምትንከባከብና የምታገለግል ወጣት ድንግል እንፈልግ፤ እርሷም ጌታችን ንጉሡ እንዲሞቀው በጐኑ ትተኛለች” አሉት።

3ከዚያም በመላው እስራኤል ቈንጆ ልጃገረድ ፈልገው ሱነማዊቷን አቢሳን አገኙ፤ ለንጉሡም አመጡለት። 4ልጃገረዲቱ እጅግ ቈንጆ ነበረች፤ ንጉሡንም ትንከባከበውና ታገለግለው ነበር፤ ንጉሡ ግን ከእርሷ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።

5በዚህ ጊዜ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ “እነግሣለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ስለዚህ ሠረገሎችንና1፥5 ወይም ሠረገለኞች ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። ፈረሶችን እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሄዱ አምሳ ሰዎችን አዘጋጀ። 6አባቱም፣ “ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ ገሥጾት አያውቅም ነበር፤ አዶንያስም እጅግ መልከ መልካምና የአቤሴሎም ታናሽ ወንድም ነበር።

7አዶንያስ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም ድጋፋቸውን ሰጡት። 8ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ነቢዩ ናታን፣ ሳሚ፣ ሬሲና1፥8 ወይም እና ጓደኞቹ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። የዳዊት የክብር ዘበኞች ከአዶንያስ ጋር አልተባበሩም።

9ከዚያም አዶንያስ በዓይንሮጌል አቅራቢያ ባለው የዞሔልት ድንጋይ አጠገብ በጎችን፣ በሬዎችንና የሠቡ ጥጆችን ሠዋ፤ ወንድሞቹን ሁሉ፣ የንጉሡን ልጆች እንዲሁም የቤተ መንግሥቱ ሹማምት የነበሩትን የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ 10ይሁን እንጂ ነቢዩ ናታንንም ሆነ በናያስን፣ የክብር ዘበኞቹንም ሆነ ወንድሙን ሰሎሞንን አልጠራም።

11ከዚያም ናታን የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ አላት፤ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ መንገሡን አልሰማሽምን? 12አሁንም የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት እንዴት ማዳን እንደምትችዪ ልምከርሽ፤ 13ወደ ንጉሥ ዳዊት ሂጂና፣ ‘ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ “ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል” ብለህ ለእኔ ለአገልጋይህ አልማልህልኝም ነበር? ታዲያ አዶንያስ የነገሠው ስለ ምንድን ነው?’ በዪው፤ 14አንቺ እዚያው ሆነሽ ይህን በምትነግሪው ጊዜ እኔ እገባና ያልሽው ትክክል መሆኑን አረጋግጣለሁ።”

15ስለዚህ ቤርሳቤህ፣ ሱነማዊቷ አቢሳ በምታገለግልበት ክፍል እርጅና የተጫጫነውን ንጉሥ ለማነጋገር ሄደች። 16ቤርሳቤህም ለጥ ብላ እጅ ከነሣች በኋላ እፊቱ በጕልበቷ ተንበረከከች።

ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።

17እርሷም እንዲህ አለችው፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ አንተው ራስህ ለአገልጋይህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ምለህልኝ ነበር። 18እነሆ፤ አሁንም አዶንያስ ነግሧል፤ ንጉሥ ጌታዬ አንተ ግን ስለዚህ ነገር አታውቅም። 19እርሱ በሬዎችን፣ ኮርማዎችንና በጎችን በብዛት ሠውቷል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ ካህኑን አብያታርንና የሰራዊቱን አዛዥ ኢዮአብን ጠርቷል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጠራውም። 20ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ከአንተ ቀጥሎ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ ማን መቀመጥ እንዳለበት እንድታሳውቀው የእስራኤል ዐይን ሁሉ አንተን ይመለከታል። 21አለበለዚያ ግን ንጉሥ ጌታዬ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎሞን እንደ ወንጀለኞች እንቈጠራለን።”

22እርሷ ከንጉሡ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለች ነቢዩ ናታን ገባ። 23ለንጉሡም፣ “ነቢዩ ናታን መጥቷል” ብለው ነገሩት፤ እርሱም ንጉሡ ፊት ቀርቦ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።

24ናታንም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ለመሆኑ አዶንያስ ከአንተ ቀጥሎ እንደሚነግሥ፣ በዙፋንህም እንደሚቀመጥ አስታውቀሃልን? 25በዛሬው ቀን ታች ወርዶ ብዙ በሬዎች፣ ኮርማዎችና በጎች ሠውቷል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ የሰራዊቱን አዛዦችና ካህኑን አብያታርንም ጠርቷል። እነሆ፤ አሁን፣ ‘አዶንያስ ለዘላለም ይኑር’ እያሉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው። 26ነገር ግን እኔን አገልጋይህን፣ ካህኑን ሳዶቅን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስንና አገልጋይህን ሰሎሞንን አልጠራም፤ 27ታዲያ ከእርሱ ቀጥሎ በንጉሥ ጌታዬ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን አገልጋዮቹን ሳያሳውቅ ይህ እንዲሆን ንጉሡ ፈቅዷልን?”

ዳዊት ሰሎሞን እንዲነግሥ አደረገ

1፥28-53 ተጓ ምብ – 1ዜና 29፥21-25

28ከዚያም ንጉሥ ዳዊት፣ “ቤርሳቤህን ጥሩልኝ” አለ፤ እርሷም ንጉሡ ወዳለበት ገብታ በፊቱ ቆመች።

29ከዚያም ንጉሡ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳናት ሕያው እግዚአብሔርን! 30‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በእኔም ምትክ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር የማልሁልሽን ዛሬ በእውነት እፈጽማለሁ።”

31ቤርሳቤህም ለጥ ብላ እጅ ከነሣች በኋላ፣ በንጉሡ ፊት ተንበርክካ፣ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ይኑር!” አለች።

32ንጉሥ ዳዊትም፣ “ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንንና የዮዳሄን ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። እነርሱም ንጉሡ ፊት በቀረቡ ጊዜ፣ 33እንዲህ አላቸው፤ “የጌታችሁን አገልጋዮች ይዛችሁ በመሄድ ልጄን ሰሎሞንን በራሴ በቅሎ ላይ አስቀምጡት፤ ወደ ግዮንም ይዛችሁት ውረዱ። 34በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡት፤ ቀንደ መለከት ነፍታችሁም፣ ‘ንጉሥ ሰሎሞን ለዘላለም ይኑር!’ ብላችሁ ጩኹ። 35አጅባችሁት ወደ ላይ ውጡ፤ ከዚያም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ፤ በእኔም ምትክ ይግዛ፤ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ ሾሜዋለሁ።”

36የዮዳሄ ልጅ በናያስም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አሜን! የጌታዬ የንጉሡ አምላክ እግዚአብሔር ይህንኑ ያጽናው። 37እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር እንደ ነበረ ሁሉ፣ ከሰሎሞንም ጋር ይሁን፤ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው።”

38ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ወርደው ሰሎሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ አስቀምጠው በማጀብ ወደ ግዮን አመጡት። 39ካህኑ ሳዶቅም የዘይቱን ቀንድ ከመገናኛው ድንኳን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው፤ ከዚያም ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ሕዝቡም በሙሉ፣ “ንጉሥ ሰሎሞን ለዘላለም ይኑር!” በማለት ዳር እስከ ዳር አስተጋቡ። 40ሕዝቡ ሁሉ እንቢልታ እየነፋና እጅግ እየተደሰተ አጀበው፤ ከድምፁ የተነሣም ምድሪቱ ተናወጠች።

41አዶንያስና የተጠሩት እንግዶች ሁሉ ግብዣውን በማገባደድ ላይ ሳሉ፣ ይህንኑ ሰሙ፤ ኢዮአብም የመለከቱን ድምፅ ሲሰማ፣ “ይህ በከተማዪቱ ውስጥ የሚሰማው ድምፅ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ።

42ኢዮአብ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ደረሰ፤ አዶንያስም፣ “እንደ አንተ ያለ ታማኝ ሰው መልካም ዜና ሳይይዝ አይመጣምና ግባ” አለው።

43ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ነገሩ ከቶ እንዲህ አይደለም! ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አንግሦታል። 44ንጉሡ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን አብረውት እንዲሄዱ አድርጓል፤ እነርሱም በንጉሡ በቅሎ አስቀመጡት። 45ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ቀብተው አንግሠውታል። ከዚያም ደስ ብሏቸው ወጥተዋል፤ ከተማዪቱም ይህንኑ አስተጋብታለች፤ እንግዲህ የሰማችሁት ድምፅ ይኸው ነው። 46ከዚህም ሌላ ሰሎሞን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ ተቀምጧል። 47የመንግሥቱ ሹማምትም ወደ ጌታችን ወደ ንጉሥ ዳዊት መጥተው፣ ‘አምላክህ የሰሎሞንን ስም ከአንተ ስም የላቀ፣ ዙፋኑንም ከአንተ ዙፋን የበለጠ ያድርገው’ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸውለታል። ንጉሡም ዐልጋው ላይ ሆኖ በመስገድ፣ 48‘ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውን ወራሽ ዐይኔ እንዲያይ የፈቀደ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ ምስጋና ይድረሰው’ አለ።”

49በዚህም አዶንያስና የጠራቸው እንግዶች በሙሉ ደንግጠው ተነሡ፤ በየአቅጣጫውም ተበታተኑ። 50አዶንያስ ግን ሰሎሞንን በመፍራት ሄዶ፣ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ። 51ከዚያም፣ ለሰሎሞን፣ “አዶንያስ እነሆ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በመፍራት የመሠዊያውን ቀንድ ይዞ ተማጥኗል፤ እርሱም፣ ‘ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለው ንጉሡ ሰሎሞን ዛሬውኑ ይማልልኝ’ ብሏል” ብለው ነገሩት።

52ሰሎሞንም፣ “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ ጥፋት ከተገኘበት ግን ይሞታል” ሲል መለሰ። 53ከዚያም ንጉሥ ሰሎሞን ሰዎች ልኮ ከመሠዊያው ላይ አወረዱት። አዶንያስም መጥቶ ለንጉሥ ሰሎሞን አጐንብሶ እጅ ነሣ፤ ሰሎሞንም፣ “በል ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

列王纪上 1:1-53

王位之争

1大卫王年纪老迈,虽然盖了几层被子,仍然觉得冷。 2他的臣仆建议:“不如选一位少女进宫伺候、照顾我主我王,让她睡在王怀中给王取暖。”

3于是,他们在以色列全国寻找美貌女子,找到了一位名叫雅比莎书念少女,把她带到王那里。 4这女子长得花容月貌,她照顾、伺候王,但王没有与她同房。

5那时,哈姬的儿子亚多尼雅妄自尊大,说:“我必做王。”他为自己制备了车辆和骑兵,派五十人在前面开路。 6他父亲从不干涉、责问他:“你这是做什么?”他是押沙龙的弟弟,长得英俊非凡。

7亚多尼雅洗鲁雅的儿子约押及祭司亚比亚他商议,二人都答应支持他。 8不过,撒督祭司、耶何耶大的儿子比拿雅拿单先知、示每利以大卫的勇士却没有跟随他。

9一天,亚多尼雅隐·罗结附近的琐希列磐石那里宰了牛羊和肥牛犊献祭,并邀请了众王子和犹大的群臣。 10可是他没有邀请拿单先知、比拿雅大卫的勇士和他的兄弟所罗门

11拿单所罗门的母亲拔示芭说:“你没有听说吗?哈姬的儿子亚多尼雅做王了,我们的主大卫还不知道。 12事到如今,我有一个主意,可以保住你和你儿子所罗门的性命。 13你去见大卫王,对他说,‘我主我王啊,你不是起誓说让臣妾的儿子所罗门继承王位吗?怎么现在亚多尼雅做了王呢?’ 14你跟王说话的时候,我会进去证实你的话。”

15拔示芭就进内室去见年迈的王,书念的少女雅比莎正在伺候他。 16拔示芭向王屈身下拜。王问道:“你有什么事吗?” 17拔示芭回答说:“我主啊,你曾经凭你的上帝耶和华起誓说让臣妾的儿子所罗门继承你的王位,坐你的宝座。 18但现在亚多尼雅已经称王了,我主我王还不知道。 19他宰了许多牛羊和肥牛犊献祭,邀请众王子、亚比亚他祭司和约押元帅,却没有邀请你的仆人所罗门20我主我王啊!以色列举国拭目以待,等着王来指定谁继承王位。 21不然,到我主我王与祖先同眠之后,我和我儿所罗门必被定为罪人。”

22她与王正说话间,拿单先知进宫来了。 23有人奏告王,说:“拿单先知来了。”拿单来到王面前,俯伏在地, 24说:“我主我王啊,你已经宣布让亚多尼雅继承你的王位,坐你的宝座吗? 25他今天宰了许多牛羊和肥犊献祭,宴请众王子、将领和亚比亚他祭司,他们正在他那里一边吃喝一边说,‘亚多尼雅王万岁!’ 26但他没有邀请臣仆我、撒督祭司、耶何耶大的儿子比拿雅和你的仆人所罗门27这是我主我王的旨意吗?王还没有对臣仆们说过谁继承王位。”

28于是,大卫王召见拔示芭拔示芭立刻晋见,侍立在王面前。 29王起誓说:“我凭救我脱离一切苦难的永活的耶和华起誓, 30我今天必实现我凭以色列的上帝耶和华向你起的誓。你的儿子所罗门必继承王位,坐在我的宝座上。”

31拔示芭就向王俯伏下拜说:“我主我王万岁!”

32大卫王又召见撒督祭司、拿单先知和耶何耶大的儿子比拿雅。他们都来到王面前。 33王嘱咐道:“你们要率领我的随从,让我儿所罗门骑上我的骡子,护送他下到基训34撒督祭司和拿单先知要在那里膏立他为以色列王。你们要吹响号角,高喊,‘所罗门王万岁!’ 35然后,你们要随他回来,他要登基,继承我的王位。我已立他做以色列犹大的君王了。”

36耶何耶大的儿子比拿雅说:“遵命,愿我主我王的上帝耶和华成全这事。 37耶和华怎样与我主我王同在,愿祂也照样与所罗门同在,使他的国比我主大卫王的国更强大。” 38于是,撒督祭司、拿单先知、耶何耶大的儿子比拿雅,以及基利提人和比利提人请所罗门骑上大卫王的骡子,护送他前往基训39撒督祭司从圣幕里拿来盛膏油的角,膏立所罗门为王。他们吹响号角,民众高声欢呼:“所罗门王万岁!” 40众人浩浩荡荡地随着所罗门回京,一路上吹笛欢呼,声音震动大地。 41亚多尼雅和他的众宾客刚刚饮宴完毕,听见了这声音。约押听见号角声,便问:“城里为什么如此喧闹?” 42就在这时候,亚比亚他祭司的儿子约拿单来了,亚多尼雅说:“进来!你是个忠勇的人,一定带来了好消息。”

43约拿单说:“我们的主大卫王已经立所罗门为王了。 44王派撒督祭司、拿单先知、耶何耶大的儿子比拿雅,以及基利提人和比利提人护送所罗门骑上王的骡子。 45撒督祭司和拿单先知在基训膏立他为王,他们一路上欢呼着回来了,全城轰动。你们听到的就是他们的声音。 46所罗门已经登基掌权, 47王的臣仆也来向我们的主大卫王道喜说,‘愿王的上帝使所罗门比王更声名显赫,使他的国比王的国更强大。’王在床上俯伏敬拜, 48说,‘以色列的上帝耶和华当受称颂,因为祂让我亲眼看见我的继承人今天登基。’”

49亚多尼雅的众宾客听后,吓得四散而去。 50亚多尼雅惧怕所罗门,就去抓住祭坛的角。 51有人告诉所罗门:“亚多尼雅惧怕王,现在正抓住祭坛的角,要王今天起誓不要杀他。”

52所罗门说:“如果他是个忠义的人,必毫发无损;如果他作恶,必死无疑。” 53于是,所罗门王便派人去把亚多尼雅从祭坛上带下来。亚多尼雅前来向所罗门王俯伏下拜,所罗门对他说:“你回家去吧。”