1 ሳሙኤል 13 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

1 ሳሙኤል 13:1-23

ሳሙኤል ሳኦልን መገሠጹ

1ሳኦል በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ13፥1 ጥንታዊ ያልሆኑ ጥቂት የሰብዓ ሊቃናት ቅጆች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ሠላሳ የሚለውን አይጨምርም ዓመት ነበረ፤ እስራኤልንም አርባ13፥1 የዐሥር ብዜት የሆኑት ቍጥሮች በተመለከተ ሐሥ 13፥21 ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን አርባ የሚለውን አይጨምርም። ሁለት ዓመት ገዛ።

2ሳኦል13፥2 ወይም እርሱ በእስራኤል ላይ ለሁለት ዓመት ከነገሠ በኋላ ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደየቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።

3ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፣ “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሪቱ ሁሉ መለከት አስነፋ። 4ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ፣ “ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር ሰፈር መታ፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ ርኩስ ተቈጥራ ተጠላች” የሚለውን ወሬ ሰሙ፤ ሕዝቡም ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ።

5ፍልስጥኤማውያን ሦስት13፥5 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን ሠላሳ ሺሕ ይላል። ሺሕ ሠረገሎች፣ ስድስት ሺሕ ፈረሰኞች ቍጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሰራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤት አዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ። 6እስራኤላውያን፣ ያሉበት ሁኔታ እጅግ የሚያሠጋ መሆኑንና ሰራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፣ በየዋሻውና በየቍጥቋጦው፣ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጕድጓዱ ሁሉ ተደበቁ። 7ከዕብራውያንም አንዳንዶቹ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ።

ሳኦል ግን በጌልገላ ቈየ፣ አብሮት የነበረውም ሰራዊት ሁሉ በፍርሀት ይንቀጠቀጥ ነበር። 8እርሱም ሳሙኤል በሰጠው ቀጠሮ መሠረት ሰባት ቀን ጠበቀው። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም፤ የሳኦልም ሰራዊት መበታተን ጀመረ። 9በዚህ ጊዜ ሳኦል፣ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን13፥9 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል። አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ። 10ልክ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ፣ ወዲያውኑ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም ሊቀበለው ወጣ።

11ሳሙኤልም፣ “ያደረግኸው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሰራዊቱ መበታተኑን፣ አንተም በቀጠርኸው ጊዜ አለመምጣትህን፣ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን አየሁ፤ 12‘ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም’ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።”

13ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “የማይገባህን አደረግህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፤ ጠብቀኸው ቢሆን ኖሮ፣ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር፤ 14አሁን ግን መንግሥትህ አይጸናም፤ እነሆ፣ እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው አግኝቷል፤ አንተ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመጠበቅህም፣ እርሱን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መርጦታል።”

15ከዚያ በኋላ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ13፥15 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን፣ ከጌልገላ ተነሥተው ወደ መንገድ ሄዱ፤ ከጦሩ ጋር ለመገናኘት የተቀረው ሕዝብ ሳኦልን ተከተለ፤ ከጌልገላም ወጥቶ ሄደ ይላል። በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች ቈጠራቸው፤ ብዛታቸውም ስድስት መቶ ያህል ነበረ።

እስራኤል ያለ ጦር መሣሪያ

16ፍልስጥኤማውያን በማክማስ ሰፍረው በነበረበት ጊዜ ሳኦል፣ ልጁ ዮናታንና አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች በብንያም ግዛት በምትገኘው በጊብዓ ነበሩ። 17በሦስት ምድብ የተከፈሉ ወራሪዎች ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጡ፤ አንዱ ምድብ በሦጋል ግዛት ወደሚገኘው ወደ ዖፍራ አቀና፤ 18ሌላው ወደ ቤትሖሮን፣ ሦስተኛው ደግሞ በምድረ በዳው ትይዩ ካለው ከስቦይም ሸለቆ ቍልቍል ወደሚያሳየው ድንበር ዞረ።

19ፍልስጥኤማውያን፣ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር፣ በመላው የእስራኤል ምድር ብረት ቀጥቃጭ አልተገኘም። 20ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ፣ ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፣ ጠገራቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር። 21ማረሻና ዶማ ለማሾል የሚከፈለው ዋጋ ሁለት ሦስተኛ ሰቅል13፥21 በዕብራይስጡ፣ ፒም ይባላል፤ 8 ግራም ያህል ነው ሲሆን፣ መንሽና ጠገራ እንዲሁም የበሬ መንጃ ለማሾል ደግሞ አንድ ሦስተኛ ሰቅል13፥21 4 ግራም ያህል ነው። ነበር።

22ስለዚህ ጦርነቱ በተደረገበት ዕለት ከሳኦልና ከልጁ ከዮናታን በስተቀር፣ አብረዋቸው ከነበሩት ወታደሮች መካከል ሰይፍ ወይም ጦር የያዘ አንድም ሰው አልነበረም።

ዮናታን በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ መጣሉ

23በዚያ ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጥቶ ነበር።

New International Version – UK

1 Samuel 13:1-23

Samuel rebukes Saul

1Saul was thirty13:1 A few late manuscripts of the Septuagint; Hebrew does not have thirty. years old when he became king, and he reigned over Israel for forty-13:1 Probable reading of the original Hebrew text (see Acts 13:21); Masoretic Text does not have forty-. two years.

2Saul chose three thousand men from Israel; two thousand were with him at Michmash and in the hill country of Bethel, and a thousand were with Jonathan at Gibeah in Benjamin. The rest of the men he sent back to their homes.

3Jonathan attacked the Philistine outpost at Geba, and the Philistines heard about it. Then Saul had the trumpet blown throughout the land and said, ‘Let the Hebrews hear!’ 4So all Israel heard the news: ‘Saul has attacked the Philistine outpost, and now Israel has become obnoxious to the Philistines.’ And the people were summoned to join Saul at Gilgal.

5The Philistines assembled to fight Israel, with three thousand13:5 Some Septuagint manuscripts and Syriac; Hebrew thirty thousand chariots, six thousand charioteers, and soldiers as numerous as the sand on the seashore. They went up and camped at Michmash, east of Beth Aven. 6When the Israelites saw that their situation was critical and that their army was hard pressed, they hid in caves and thickets, among the rocks, and in pits and cisterns. 7Some Hebrews even crossed the Jordan to the land of Gad and Gilead.

Saul remained at Gilgal, and all the troops with him were quaking with fear. 8He waited for seven days, the time set by Samuel; but Samuel did not come to Gilgal, and Saul’s men began to scatter. 9So he said, ‘Bring me the burnt offering and the fellowship offerings.’ And Saul offered up the burnt offering. 10Just as he finished making the offering, Samuel arrived, and Saul went out to greet him.

11‘What have you done?’ asked Samuel.

Saul replied, ‘When I saw that the men were scattering, and that you did not come at the set time, and that the Philistines were assembling at Michmash, 12I thought, “Now the Philistines will come down against me at Gilgal, and I have not sought the Lord’s favour.” So I felt compelled to offer the burnt offering.’

13‘You have done a foolish thing,’ Samuel said. ‘You have not kept the command the Lord your God gave you; if you had, he would have established your kingdom over Israel for all time. 14But now your kingdom will not endure; the Lord has sought out a man after his own heart and appointed him ruler of his people, because you have not kept the Lord’s command.’

15Then Samuel left Gilgal13:15 Hebrew; Septuagint Gilgal and went his way; the rest of the people went after Saul to meet the army, and they went out of Gilgal and went up to Gibeah in Benjamin, and Saul counted the men who were with him. They numbered about six hundred.

Israel without weapons

16Saul and his son Jonathan and the men with them were staying in Gibeah13:16 Two Hebrew manuscripts; most Hebrew manuscripts Geba, a variant of Gibeah of Benjamin, while the Philistines camped at Michmash. 17Raiding parties went out from the Philistine camp in three detachments. One turned towards Ophrah in the vicinity of Shual, 18another towards Beth Horon, and the third towards the borderland overlooking the Valley of Zeboyim facing the wilderness.

19Not a blacksmith could be found in the whole land of Israel, because the Philistines had said, ‘Otherwise the Hebrews will make swords or spears!’ 20So all Israel went down to the Philistines to have their ploughshares, mattocks, axes and sickles13:20 Septuagint; Hebrew ploughshares sharpened. 21The price was two-thirds of a shekel13:21 That is, about 8 grams for sharpening ploughshares and mattocks, and a third of a shekel13:21 That is, about 4 grams for sharpening forks and axes and for repointing goads.

22So on the day of the battle not a soldier with Saul and Jonathan had a sword or spear in his hand; only Saul and his son Jonathan had them.

Jonathan attacks the Philistines

23Now a detachment of Philistines had gone out to the pass at Michmash.