አምልኮን በሚመለከት የተሰጠ መመሪያ
1እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ 2ይህም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው። 3ይህ በእግዚአብሔር በአዳኛችን ፊት ደስ የሚያሰኝ ነው፤ 4እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል። 5አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 6ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። 7እኔም ለዚህ ነገር የምሥራች አብሣሪና ሐዋርያ እንዲሁም ለአሕዛብ የእውነተኛ እምነት አስተማሪ ሆኜ ተሾምሁ፤ እውነቱን እናገራለሁ፤ አልዋሽም።
8እንግዲህ ወንዶች በሁሉም ቦታ ያለ ቍጣና ያለ ክርክር የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ። 9እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራስን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልብስ ይልበሱ እንጂ በሹሩባ ወይም በዕንወይም ዋጋቸው ውድ በሆኑ ልብሶች አይሽቀርቀሩ፤ 10ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ።
11ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር። 12ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤ 13ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች። 14ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት። 15ይሁን እንጂ ሴት2፥15 ግሪኩ እርሷ ይላል። በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም ራሷን እየገዛች ብትጸና ልጅ በመውለድ ትድናለች2፥15 ወይም ትታደሳለች።
要為他人禱告
1我勸你首先要為所有的人懇求、禱告、代求和感謝上帝。 2也要為所有的君王和掌權者禱告,使我們可以懷著虔誠、端正的心過和平安寧的生活。 3這樣做很美好,是蒙我們的救主上帝悅納的。 4因為祂願世人都得救,明白真理。 5上帝只有一位,在上帝和世人之間只有一位中保,就是降世為人的基督耶穌。 6祂捨命作所有人的贖價,這在所定的時候已顯明出來。 7為此,我被指派做傳道人和使徒,教導外族人認識信仰和真理。我說的是實話,並非謊言。
信徒的操守
8我願男人舉起聖潔的手隨處禱告,不發怒,不爭辯2·8 「爭辯」或譯「疑惑」。。 9我願女人衣著得體,樸素端莊,不靠髮型、珠寶金飾或名貴衣服來妝飾自己, 10要有善行,這樣才配稱為敬畏上帝的女人。 11女人應當安安靜靜地學習,完全順服。
12我不准女人教導或管轄男人,她們應當保持安靜。 13因為先造的是亞當,後造的是夏娃, 14並非亞當受騙,而是夏娃受騙陷入罪中。 15不過,女人如果持守信心和愛心,聖潔自律,就必在生育的事上得救。