New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 8:1-66

ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ

8፥1-21 ተጓ ምብ – 2ዜና 5፥2–6፥11

1ከዚያም ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ለማምጣት፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የእስራኤልን ነገድ አለቆችና የእስራኤልን ጐሣዎች ሹማምት ሁሉ እርሱ ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ጠራቸው። 2በዓሉ በሚከበርበት ኤታኒም በተባለው በሰባተኛው ወር፣ የእስራኤል ወንዶች ሁሉ ንጉሥ ሰሎሞን ወዳለበት ተሰበሰቡ።

3የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በመጡ ጊዜም ካህናቱ ታቦቱን አነሡ፤ 4የእግዚአብሔርን ታቦት፣ የመገናኛውን ድንኳንና በውስጡ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አመጡ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ይህን ሁሉ ተሸከሙ። 5ንጉሥ ሰሎሞንና አብሮት በዚያ የተሰበሰበው መላው የእስራኤል ጉባኤም በታቦቱ ፊት በመሆን ስፍር ቊጥር የሌለው በግና በሬ ሠዋ።

6ከዚያም ካህናቱ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አምጥተው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወዳለው ማደሪያው፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በማስገባት ከኪሩቤል ክንፍ በታች አኖሩት። 7ኪሩቤልም ታቦቱ ባለበት ቦታ ላይ ክንፋቸውን ዘርግተው፣ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን ጋረዱ። 8መሎጊያዎቹ ከመርዘማቸው የተነሣ ጫፎቻቸው ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ካለው ከመቅደሱ ሆኖ ይታዩ ነበር፤ ከመቅደሱ ወዲያ ላለ ሰው ግን አይታዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያው ይገኛሉ። 9የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ኪዳን በገባበት በኮሬብ፣ ሙሴ በታቦቱ ውስጥ ካስቀመጣቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም።

10ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ በወጡ ጊዜ፣ ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሞላው። 11የእግዚአብሔር ክብር ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ስለ ነበር፣ ካህናቱ በደመናው ምክንያት አገልግሎታቸውን ማከናወን አልቻሉም ነበር።

12ከዚያም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ጥቅጥቅ ባለ ደመና ውስጥ እንደሚኖር ተናግሮአል፤ 13እነሆ፣ እኔም ለዘላለም የምትኖርበትን ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርቼልሃለሁ።”

14መላው የእስራኤል ጉባኤ በዚያ ቆሞ ሳለ፣ ንጉሡ ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ ጉባኤውን ባረከ። 15ከዚያም እንዲህ አለ፤

“ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ ተናግሮ የሰጠውን ተስፋ፣ እርሱ ራሱ በእጁ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበርና፤ 16‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ዕለት አንሥቶ፣ ስሜ በዚያ እንዲጠራና ቤተ መቅደስ እንዲሠ ራበት ከመላው የእስራኤል ነገድ አንድም ከተማ አልመረጥሁም፤ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲመራ ግን ዳዊትን መረጥሁት።’

17“አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ለመሥራት በልቡ አስቦ ነበር፤ 18እግዚአብሔር ግን አባቴን ዳዊትን እንዲህ አለው፤ ‘ለስሜ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አስበሃልና፣ ይህን በልብህ ማሰብህ መልካም ነው፤ 19ይሁን እንጂ ቤተ መቅደሱን የምትሠራው አንተ ሳትሆን፣ ከአንተ የሚወለደው ልጅህ ነው፤ አዎን ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው።’

20እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ፈጽሞአል፤ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቻለሁ፤ በእስራኤል ዙፋን ተቀምጫለሁ፤ እንዲሁም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ሠርቻለሁ። 21ከግብፅ ባወጣቸው ጊዜ ከአባቶቻችን ጋር የገባው የእግዚአብሔር ኪዳን በውስጡ ላለበት ታቦት መኖሪያ ስፍራ በዚያ አዘጋጅቻለሁ።”

ሰሎሞን በምረቃው ላይ ያቀረበው ጸሎት

8፥22-53 ተጓ ምብ – 2ዜና 6፥12-40

22ከዚያም ሰሎሞን መላው የእስራኤል ጉባኤ ባለበት በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ፣ 23እንዲህ አለ፤

“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በፊትህ በፍጹም ልባቸው ጸንተው ለሚኖሩ አገልጋዮችህ ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ጽኑ ፍቅርህን የምትገልጥ አንተ ነህ፤ በላይ በሰማይ፣ በታችም በምድር እንዳንተ ያለ አምላክ ከቶ የለም፤ 24ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ ጠብቀሃል፤ በአፍህ ተናገርህ፤ ይህንኑም በዛሬው ዕለት በእጅህ ፈጸምኸው።

25“አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ለአባቴ ለባሪያህ ለዳዊት፣ ‘አንተ እንዳደረግኸው ሁሉ፣ ልጆችህ በፊቴ ለመመላለስ በሚያደርጉት ሁሉ ይጠንቀቁ ብቻ እንጂ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚቀመጥ ሰው አታጣም’ ስትል የሰጠኸውን ተስፋ ፈጽምለት። 26አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም።

27“ነገር ግን አምላክ በእርግጥ በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፤ ሰማይ፣ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ እንኳ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምኑ ሊበቃ! 28አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህም ሆኖ የባሪያህን ጸሎትና ልመና ስማ፤ በዛሬው ዕለት ባሪያህ በፊትህ የሚያቀርበውን ጩኸትና ልመና አድምጥ። 29ባሪያህ ወደዚህ ቦታ የሚያቀርበውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’ ወዳልኸው በዚህ ስፍራ ወዳለው ቤተ መቅደስ ዐይኖችህ ሌትና ቀን የተከፈቱ ይሁኑ። 30ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ ጸሎት በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ልመናቸውን ተቀበል፤ መኖሪያህ በሆነው በሰማይ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል።

31“አንድ ሰው ባልንጀራውን በድሎ መማል ኖሮበት ቢመጣና በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ በመሠዊያህ ፊት ቢምል፣ 32ይህን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፤ ለበደለኛው ስለ አድራጎቱ የእጁን ክፈል፤ ከበደል ነጻ ለሆነውም ንጽሕናውን ይፋ በማድረግ ይህንኑ አረጋግጥለት።

33ሕዝብህ እስራኤል አንተን ከመበደላቸው የተነሣ፣ በጠላቶቻቸው ድል በሚሆኑበት ጊዜ፣ ወደ አንተም ተመልሰው ስምህን ቢጠሩ፣ በዚህም ቤተ መቅደስ ወደ አንተ ቢጸልዩና ልመናቸውን ቢያቀርቡ፣ 34በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የሕዝብህ የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸውም ምድር መልሰህ አግባቸው።

35“ሕዝቡም አንተን ከመበደላቸው የተነሣ፣ ሰማዩ ተዘግቶ ዝናብ ሳይዘንብ ቢቀር፣ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩና ስምህን ቢጠሩ፣ ስላስጨነቅሃቸውም ከበደላቸው ቢመለሱ፣ 36በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የባሪያዎችህን የሕዝብህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ የሚሄዱበትን ቀናውን መንገድ አስተምራቸው፤ ርስት አድርገህ ለሕዝብህ ለሰጠሃትም ምድር ዝናብ አውርድ።

37“በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት፣ ዋግ ወይም አረማሞ በሚከሠትበት፣ አንበጣ ወይም ኵብኵባ በሚወርድበት ወይም በምድራቸው ውስጥ ባሉት ከተሞቻቸው ጠላት ቢከባቸው እንዲሁም ማንኛውም ዐይነት ጥፋት ወይም በሽታ በሚመጣባቸው ጊዜ፣ 38ከሕዝብህ ከእስራኤል ማንኛውም ሰው የልቡን ጭንቀት ዐውቆ እጆቹን ወደዚህ ቤት በመዘርጋት ጸሎትና ልመና በሚያቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ 39በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ይቅር በል፤ አድርግም። አንተ ብቻ የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቅ ስለ ሆንህ ልቡን ለምታውቀው ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ሁሉ ክፈለው፤ 40ይህም እነርሱ ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ፣ አንተን እንዲፈሩ ነው።

41“ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ፣ ግን ከስምህ ታላቅነት የተነሣ ከሩቅ የመጣ የባዕድ አገር ሰው ቢኖር፣ 42ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፣ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፣ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፣ 43አንተ በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የጠየቀህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ይኸውም የምድር ሕዝቦች ሁሉ ስምህን ዐውቀው፣ ሕዝብህ እስራኤል አንተን እንደሚፈሩት ሁሉ እንዲፈሩህ፣ እኔ የሠራሁትም ይህ ቤት በስምህ መጠራቱን እንዲያውቁ ነው።

44“ሕዝብህ ጠላታቸውን ለመውጋት አንተ ወደምትልካቸው ወደ የትኛውም ቦታ ለጦርነት በሚወጡበት ጊዜ፣ አንተ ወደ መረጥሃት ከተማና እኔ ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ለእግዚአብሔር ቢጸልዩ፣ 45ጸሎትና ልመናቸውን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ርዳቸውም።

46“መቼም ኀጢአት የማይሠራ የለምና ሕዝብህ በአንተ ላይ ኀጢአት ቢሠሩ አንተም ተቈጥተህ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነው ምድሩ ማርኮ ለሚወስደው ጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ 47ተማርከው በሚኖሩበት አገር ሳሉ ልባቸው ቢመለስ፣ በተማረኩበትም ምድር ሆነው ንስሓ ቢገቡና ‘ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’ ብለው ቢለምኑህ፣ 48እንዲሁም ማርከው በወሰዷቸው ጠላቶቹ ምድር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፣ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃት ወደዚህች ምድር ወደ መረጥሃትም ወደዚህች ከተማና እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፣ 49ከማደሪያህ ከሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ ልመናቸውንም ተቀበል፤ ርዳቸውም። 50በአንተ ላይ ስለሠሩት ኀጢአት፣ አንተንም ስለ በደሉህ በደል ሁሉ ሕዝብህን ይቅር በል፤ የማረኳቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ። 51ከዚያች እንደ ብረት ማቅለጫ እቶን እሳት ከሆነችው፣ ከግብፅ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህም ርስትህም ናቸውና።

52“አሁንም ዐይኖችህ ለባሪያህና ለሕዝብህ ለእስራኤል ልመና የተከፈቱ ይሁኑ፤ ወደ አንተ በሚጮኹበትም ጊዜ ሁሉ ስማቸው፤ 53አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፤ አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ፣ በባሪያህ በሙሴ አማካኝነት እንደ ተናገርኸው ሁሉ፣ ርስትህ ይሆኑ ዘንድ ከምድር ሕዝቦች ሁሉ ለይተሃቸዋልና።”

54ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ጸሎትና ልመና ለእግዚአብሔር አቅርቦ ከፈጸመ በኋላ፣ እጆቹን ወደ ሰማይ በመዘርጋት፣ በጒልበቱ ተንበርክኮ ከነበረበት ከእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ተነሣ። 55ከዚያም ቆሞ መላውን የእስራኤልን ጉባኤ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ ሲል መረቀ፤

56“በሰጠው ተስፋ መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን ለሰጠ እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው፤ በባሪያው በሙሴ አማካይነት ከተሰጠው መልካም ተስፋ ሁሉ አንድም ቃል አልቀረምና። 57አምላካችን እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ጋር እንደ ነበረ ሁሉ፣ ከእኛም ጋር ይሁን፤ አይተወን፤ አይጣለንም። 58በመንገዱም ሁሉ እንድንሄድ፣ ለአባቶቻችን የሰጣቸውን ትእዛዞች፣ ሥርዐቶችና ደንቦች እንድንጠብቅ ልባችንን ወደ እርሱ ይመልስ። 59በየዕለቱም ባሪያውንና ሕዝቡን እስራኤልን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ እንዲረዳቸው፣ ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያቀረብኋት የራሴ ልመና በቀንና በሌሊት ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ፊት ትቅረብ። 60ይኸውም የምድር ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ እንደሆነና ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ነው። 61ስለዚህ እንደ ዛሬው ዕለት ሁሉ፣ በሥርዐቱ እንድትኖሩና ትእዛዙን እንድትጠብቁ ልባችሁ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የተገዛ ይሁን።”

የቤተ መቅደሱ መመረቅ

8፥62-66 ተጓ ምብ – 2ዜና 7፥1-10

62ከዚያም ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት እስራኤል ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት አቀረቡ። 63ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺህ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺህ በግና ፍየል የኅብረት መሥዋዕት8፥63 በዚህና በቍ 64 ላይ በትውፊት፣ የሰላም መሥዋዕት ይባላል። አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ንጉሡና እስራኤላውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።

64በዚያኑ ዕለትም ንጉሡ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ያለውን የአደባባዩን መካከለኛ ክፍል ቀደሰ፤ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህል ቊርባንና የኅብረት መሥዋዕቱን ስብ አቀረበ፤ ይህን ያደረገውም በእግዚአብሔር ፊት የነበረው የናስ መሠዊያ ከትንሽነቱ የተነሣ የሚቃጠለውን መሥዋዕት የእህሉን ቊርባንና የኅብረት መሥዋዕቱን ስብ መያዝ ባለመቻሉ ነበር።

65በዚያን ጊዜም ሰሎሞን አብረውት ካሉት የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋር፣ ማለትም ከሐማት መተላለፊያ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ8፥65 ወይም ከመግቢያው ጀምሮ ተብሎ መተርጐም ይችላል። ካለው ምድር ከተሰበሰበው ታላቅ ጉባኤ ጋር በዓሉን አከበረ። እነርሱም ሰባት ቀን፣ በተጨማሪም ሌላ ሰባት ቀን በድምሩ ዐሥራ አራት ቀን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በዓሉን አከበሩ። 66በሚቀጥለው ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ ሕዝቡም ንጉሡን መረቁ፤ እግዚአብሔር ለባሪያው ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ባደረገው በጎ ነገር ሁሉ ከልብ ተደስተው ሐሤት በማድረግ ወደየቤታቸው ተመለሱ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

列王紀上 8:1-66

運約櫃入聖殿

1所羅門以色列的長老、各支派的首領和族長召集到耶路撒冷,準備把耶和華的約櫃從大衛錫安運上來。

2以他念月,即七月住棚節的時候,以色列人都聚集到所羅門王那裡。 3以色列的長老到齊後,祭司便抬起約櫃, 4祭司和利未人將約櫃、會幕和會幕裡的一切聖器運上來。 5所羅門王和聚集到他那裡的以色列全體會眾在約櫃前獻祭,獻上的牛羊多得不可勝數。 6祭司把耶和華的約櫃抬進內殿,即至聖所,放在兩個基路伯天使的翅膀下面。 7基路伯天使展開翅膀,遮蓋約櫃和抬約櫃的橫杠。 8橫杠相當長,在至聖所前面的聖所中可以看見橫杠的末端,在聖所外面看不見。橫杠至今仍在那裡。 9約櫃裡除了兩塊石版,沒有別的東西。石版是以色列人離開埃及後,耶和華在何烈山跟他們立約時,摩西放進去的。 10祭司從聖所出來的時候,就有雲彩充滿了耶和華的殿, 11以致祭司不能留在殿裡供職,因為那裡充滿了耶和華的榮光。 12那時,所羅門說:

「耶和華啊,

你曾說你要住在密雲中,

13現在,我為你建造了殿宇,

作你永遠的居所。」

14然後,王轉身為站立在那裡的以色列民眾祝福, 15說:「以色列的上帝耶和華當受稱頌!祂親口給我父大衛的應許,現在祂親手成就了! 16祂曾說,『自從我把我的以色列子民帶出埃及以來,我並沒有在以色列各支派中選出一座城來建造殿宇,作為我名下的居所。我只是揀選了大衛來治理我的以色列子民。』」 17所羅門又說:「我父大衛曾想為以色列的上帝耶和華建殿, 18但是耶和華對我父大衛說,『你想為我建殿,這番心意是好的, 19但你不要建,要由你的親生兒子為我建殿。』

20「耶和華已經實現祂的應許,祂讓我繼承我父大衛的王位統治以色列。現在,我為以色列的上帝耶和華的名建了殿, 21並在殿裡預備了放約櫃的地方。約櫃裡有耶和華的約,是祂把我們的祖先帶出埃及時跟他們立的。」

所羅門的禱告

22所羅門當著以色列會眾的面,站在耶和華的壇前,向天伸出雙手, 23禱告說:「以色列的上帝耶和華啊,天上地下沒有神明可以與你相比!你向盡心遵行你旨意的僕人守約,施慈愛。 24你持守向你僕人——我父大衛的應許,你曾親口應許,你今天親手成就了。

25以色列的上帝耶和華啊,你曾對你僕人——我父大衛說,『你的子孫若像你一樣謹慎行事、遵行我的旨意,你的王朝就不會中斷。』求你信守這應許。 26以色列的上帝耶和華啊,求你實現你向你僕人——我父大衛的應許。

27「然而,上帝啊,你真的會住在人間嗎?看啊,諸天尚且不夠你居住,更何況我建造的這殿呢? 28可是,我的上帝耶和華啊,求你垂顧你僕人的禱告和祈求,垂聽你僕人今天在你面前的呼求和祈禱。 29願你晝夜看顧這殿——你應許立你名的地方!你僕人向著這地方禱告的時候,求你垂聽。 30你僕人和你的以色列子民向這地方祈禱的時候,求你從你天上的居所垂聽,赦免我們的罪。

31「如果有人得罪鄰舍,被叫到這殿中,在你的壇前起誓, 32求你從天上垂聽,在你眾僕人當中施行審判,按他們的行為罰惡賞善。

33「當你的以色列子民因得罪你而敗在敵人手中時,如果他們回心轉意歸向你,承認你的名,在這殿裡祈禱, 34求你從天上垂聽,赦免他們的罪,帶領他們回到你賜給他們祖先的土地上。

35「當你的子民得罪你,你懲罰他們,叫天不降雨時,如果他們向著這殿禱告,承認你的名,並離開罪惡, 36求你在天上垂聽,赦免你僕人——你以色列子民的罪,教導他們走正道,降下甘霖滋潤你賜給你子民作產業的土地。

37「如果國中有饑荒、瘟疫、旱災、黴病、蝗災、蟲災,或是城邑被敵人圍困,無論遭遇什麼災禍疾病, 38只要你的以色列子民,或個人或全體,自知心中痛苦並向著這殿伸手禱告,無論祈求什麼, 39求你從天上的居所垂聽,赦免他們。唯獨你能洞察人心,你必按各人的行為施行賞罰, 40使你的子民在你賜給我們祖先的土地上終生敬畏你。

41-42「如果有遠方的外族人聽說你的大能大力,慕名而來,向著這殿禱告, 43求你從天上的居所垂聽,應允他們的祈求,好叫天下萬民都像你的以色列子民一樣認識你的名,敬畏你,並知道我建造的這殿屬於你的名下。

44「你的子民奉你的命令上陣與敵人作戰,無論他們在哪裡,如果他們向著你選擇的這城和我為你建造的這殿禱告, 45求你從天上垂聽,使他們得勝。

46「世上沒有不犯罪的人,如果你的子民得罪你,以致你向他們發怒,讓敵人把他們擄走,不論遠近, 47若他們在那裡回心轉意,向你懇求,承認自己犯罪作惡了; 48若他們全心全意地歸向你,朝著你賜給他們祖先的這片土地、你選擇的這城和我為你建的這殿向你禱告, 49求你從天上的居所垂聽他們的祈求,為他們伸張正義, 50赦免得罪你的子民,赦免他們的一切過犯,使擄掠他們的人善待他們。 51因為他們是你的子民、你的產業,是你從埃及那熊熊的火爐裡拯救出來的。

52「願你垂顧僕人和你的以色列子民的祈求。無論他們什麼時候向你祈求,都求你垂聽。 53主耶和華啊,因為你把我們祖先帶出埃及的時候,曾經藉著你的僕人摩西應許將以色列人從萬民中分別出來,作你自己的產業。」

所羅門為民祝福

54所羅門跪在耶和華的壇前,舉著手向耶和華禱告完畢, 55便站起來高聲為以色列全體會眾祝福: 56「耶和華當受稱頌!祂照著應許賜平安給祂的以色列子民。祂從前藉著僕人摩西賜下的美好應許一句也沒有落空。 57願我們的上帝耶和華與我們同在,就像與我們的祖先同在一樣。願祂永遠都不撇下我們,不丟棄我們, 58使我們的心歸向祂,遵行祂的旨意,謹守祂吩咐我們祖先的誡命、律例和典章。 59願我們的上帝耶和華晝夜顧念我在祂面前的這些祈求,天天護佑祂的僕人和祂的以色列子民, 60叫地上萬民都知道,耶和華是獨一無二的上帝。 61願你們像今天一樣專心事奉我們的上帝耶和華,遵行祂的律法,謹守祂的誡命。」

聖殿奉獻禮

62王和以色列眾民一同向耶和華獻祭。 63所羅門向耶和華獻上兩萬二千頭牛、十二萬隻羊作平安祭,王和以色列眾民為耶和華的殿舉行奉獻典禮。

64那天,因為耶和華殿前的銅壇太小,容不下燔祭、素祭和平安祭祭牲的脂肪,所羅門王就把殿前院子中間分別出來作聖潔之地,在那裡獻上燔祭、素祭和平安祭祭牲的脂肪。 65所羅門和從哈馬口直至埃及小河而來的全體以色列人聚成一大群會眾,在我們的上帝耶和華面前守節期兩週,共十四天。 66之後,所羅門王讓眾民各回本鄉。他們看見耶和華向祂的僕人大衛以色列子民所施的一切恩惠,都為王祝福,並滿心歡喜地回家去了。