New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 6:1-38

ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመረ

6፥1-29 ተጓ ምብ – 2ዜና 3፥1-14

1እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በአራት መቶ ሰማንያ6፥1 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒም አራት መቶ አርባ ይላሉ ዓመት፣ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ዚፍ በተባለው በሁለተኛው ወር ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።

2ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር የሠራው ቤተ መቅደስ ርዝመቱ ሥልሳ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ6፥2 ርዝመቱ 27 ሜትር፣ ወርዱ 9 ሜትር እንዲሁም ቁመቱ 13.5 ሜትር ያህል ነው ነበር። 3በቤተ መቅደሱ ዋነኛ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ወርዱ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ሁሉ ሃያ ክንድ6፥3 16.9 ሜትር ያህል ነው ሲሆን፣ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ6፥3 4.5 ሜትር ያህል ነው ወደ ውጭ የወጣ ነበር። 4ለቤተ መቅደሱም ባለ ዐይነ ርግብ መስኮቶች አበጀ። 5በዋናው ቤተ መቅደስና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግድግዳ ዙሪያ ልዩ ክፍሎች ያሉት ተቀጥላ ግንብ ሠራ። 6የምድር ቤቱ ወርድ አምስት ክንድ፣6፥6 በዚህ እንዲሁም በቍ 10 እና 24 ላይ 2.3 ሜትር ያህል ነው የመካከለኛው ፎቅ ስድስት ክንድ፣6፥6 2.7 ሜትር ያህል ነው የሦስተኛው ፎቅ ሰባት ክንድ6፥6 3.1 ሜትር ያህል ነው ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ዘልቆ እንዳይገባም፣ ከቤተ መቅደሱ ግንብ ውጭ ዙሪያውን እርከኖች አደረገ።

7ቤተ መቅደሱ የተሠራው እዚያው ድንጋዩ ተቈፍሮ ከወጣበት ቦታ በተዘጋጀ ድንጋይ በመሆኑ የመራጃ፣ የመሮ ወይም የሌላ ብረት ነክ መሣሪያ ድምፅ በቤተ መቅደሱ አካባቢ አልተሰማም ነበር።

8የምድር ቤቱ6፥8 የሰብዓ ሊቃናት ትርጒም ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን የመካከለኛው ደርብ ይላሉ መግቢያ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የቤተ መቅደሱ ጐን ሲሆን ወደ መካከለኛውና ከዚያም ወደ መጨረሻው ፎቅ የሚያስወጣ ደረጃ ነበረው። 9ቤተ መቅደሱንም በዚሁ ሁኔታ ሠርቶ ጨረሰ፤ ለጣራው ተሸካሚ አደረገለት፤ በዝግባ ሳንቃም ከደነው። 10በቤተ መቅደሱም ዙሪያ በሙሉ፣ ቁመታቸው አምስት አምስት ክንድ የሆነ ክፍሎች ሠራ፤ እነዚህንም ከቤተ መቅደሱ ጋር በዝግባ አግዳሚ ዕንጨቶች አያያዛቸው።

11የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሰሎሞን መጣ፤ 12“ስለምትሠራው ስለዚህ ቤተ መቅደስ ሥርዐቴን ብትከተል፣ ፍርዴን በተግባር ብትገልጸው፣ ትእዛዛቴን ብትጠብቅና ብትመላለስባቸው ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን ተስፋ በአንተ እፈጽመዋለሁ፤ 13በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ ሕዝቤን እስራኤልንም አልተወውም።”

14ስለዚህ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ፈጸመ፤ 15የውስጡን ግድግዳ ከቤተ መቅደሱ ወለል እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃ ለበጠ፤ የቤተ መቅደሱንም ወለል የጥድ ሳንቃ አለበሰው። 16በቤተ መቅደሱም ውስጥ በስተ ኋላ በኩል፣ ሃያውን ክንድ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲሆን፣ ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃዎች ጋረደው፤ 17በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ያለው ዋና አዳራሽ ርዝመቱ አርባ ክንድ6፥17 18 ሜትር ያህል ነው ነበር። 18የቤተ መቅደሱም፣ ውስጡ በሙሉ በዝግባ የተለበጠ ሲሆን፣ ይህም በእንቡጥ አበቦችና በፈኩ አበቦች ቅርጽ የተጌጠ ነበር፤ በሙሉ ዝግባ እንጂ የሚታይ ድንጋይ አልነበረም።

19በቤተ መቅደሱም ውስጠኛ ክፍል የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚቀመጥበትን ቅድስተ ቅዱሳን ሠራ። 20ቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱም ሃያ ክንድ6፥20 ርዝመቱ፣ ወርዱና ቁመቱ 9 ሜትር ያህል ነው ነበር፤ ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ ከዝግባ የተሠራውንም መሠዊያ በወርቅ ለበጠው። 21ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በወርቅ በተለበጠው ቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊትም የወርቅ ሰንሰለቶች ዘረጋ። 22ስለዚህ ውስጡን በሙሉ በወርቅ ለበጠው፤ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ያለውን መሠዊያም እንደዚሁ በወርቅ ለበጠው። 23በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ6፥23 4.5 ሜትር ያህል ነው የሆነ ሁለት የኪሩቤል ቅርጽ ከወይራ ዕንጨት ሠራ፤ 24የአንደኛው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሲሆን፣ ሌላውም ክንፉ እንደዚሁ አምስት ክንድ ነበር፤ ይህም ከአንዱ ክንፍ ጫፍ እስከ ሌላው ክንፍ ጫፍ ዐሥር ክንድ ማለት ነው። 25የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ እንደዚሁ ዐሥር ክንድ ሆነ፣ ሁለቱ ኪሩቤል በመጠንና በቅርጽ አንድ ዐይነት ነበሩና። 26የእያንዳንዱም ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበር። 27ክንፎቻቸው እንደ ተዘረጋ፣ ኪሩቤልን ወስዶ በቅድስተ ቅዱሳኑ አኖራቸው፤ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ አንዱን ግድግዳ ሲነካ፣ የሌላው ኪሩብ ክንፍ ደግሞ ሌላውን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌሎቹ ክንፎቻቸውም በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። 28ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው።

29በመቅደሱ ግድግዳ ዙሪያ ላይ ሁሉ በውስጥም በውጭም ኪሩቤልን፣ ከዘንባባ ዛፎችና ከፈነዱ አበቦች ጋር ቀረጸ። 30እንዲሁም የቅድስተ ቅዱሳኑንና የመቅደሱን ወለል በሙሉ በወርቅ ለበጠ።

31ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ የወይራ ዕንጨት ደጃፎች ሠራ፤ መቃኖቻቸውንና መድረኮቻቸውን ባለ አምስት ማእዘን አደረገ። 32በሁለቱ የወይራ ዕንጨት መዝጊያዎችም ላይ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈነዱ አበቦችን ቀረጸ፤ በወርቅም ለበጣቸው። 33እንዲሁም ለዋናው አዳራሽ መግቢያ ባለ አራት ማእዘን የወይራ ዕንጨት መቃን ሠራ፤ 34እያንዳንዳቸው በማጠፊያ የተያያዙ ሁለት ሁለት ሳንቃዎች ያሏቸው ሁለት መዝጊያዎች አበጀ። 35ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችንም ቀረጸባቸው፤ ቅርጹን ሠራ፤ ጥሩ አድርጎም በወርቅ ለበጠው።

36የውስጠኛውን አደባባይ በሦስት ረድፍ ጥርብ ድንጋይና በአንድ ረድፍ የዝግባ ሳንቃ ሠራው።

37የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም በአራተኛው ዓመት ዚፍ በተባለው ወር መሠረቱ ተጣለ፤ 38በዐሥራ አንደኛው ዓመት ቡል በተባለውም በስምንተኛው ወር ቤተ መቅደሱ በዝርዝር ጥናቱ መሠረት እንደ ታቀደው ተፈጸመ፤ ሠርቶ የጨረሰውም በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

列王紀上 6:1-38

建造聖殿

1所羅門在做以色列王的第四年二月,即西弗月,開始為耶和華建殿。那時正是以色列人離開埃及後第四百八十年。 2所羅門王為耶和華建造的殿長二十七米,寬九米,高十三米半。 3殿前的門廊和殿一樣寬九米,深四米半。 4殿有精緻的窗戶。 5靠殿牆、圍著外殿和內殿又造了三層廂房, 6底層寬二點二五米,中層寬二點七米,上層寬三點一米。廂房的橫樑都搭在殿牆突出的地方,免得插入殿牆。 7建殿的石頭都在採石場鑿好了,建殿的時候聽不到錘子、斧頭或其他鐵器的響聲。

8底層廂房的進口在殿的南面,沿著一道螺旋樓梯可以通到第二層和第三層。 9殿建成後,殿頂裝上香柏木的梁木和木板。 10靠著殿牆所造的廂房每一層高二點二五米,用香柏木的梁木與殿牆接連起來。

耶和華的約

11耶和華對所羅門說: 12「關於你所建的這殿,若你遵行我的律例,順從我的典章,謹守我的一切誡命,我必實現我對你父親大衛的應許。 13我必住在以色列人當中,不拋棄我的以色列子民。」

14所羅門建造的殿落成了。 15殿裡的牆壁和天花板都鋪上了香柏木,地面都鋪上了松木板。 16在殿的後部,從地面至天花板用香柏木板隔出長九米的內殿,就是至聖所。 17在至聖所外面是外殿,長十八米。 18殿內全部鋪上香柏木,不露一點石頭,香柏木上刻著野瓜和花朵的圖案。 19殿的至聖所用來安放耶和華的約櫃。 20至聖所長、寬和高都是九米,裡面全貼上純金,香柏木造的祭壇也包上純金。 21殿內全部貼上純金,至聖所前面有金鏈攔著。 22殿內都貼上純金,至聖所內的祭壇也都包上純金。

23至聖所裡面放著兩個橄欖木造的基路伯天使,各高四米半, 24各有兩個二點二五米長的翅膀,雙翅展開,兩翅尖相距四點五米。 25兩個基路伯的大小和形狀一模一樣, 26高度都是四點五米。 27他將兩個基路伯安在至聖所內,兩個基路伯展開翅膀,各有一個翅膀在至聖所的中央相接,另一個翅膀的尖端觸到牆壁。 28這兩個基路伯天使也包上金。

29內殿和外殿的牆壁都刻上基路伯天使、棕樹和花朵的圖案, 30地板是鋪金的。 31至聖所的門、門楣和門柱都是橄欖木造的,門柱呈五角形。 32兩扇用橄欖木造的門上都刻著基路伯天使、棕樹和花朵的圖案,並包上金。 33外殿的四角形門柱也是用橄欖木造的, 34兩扇門是松木造的,每一扇門都分為可折疊的兩片, 35上面刻著基路伯天使、棕樹和花朵的圖案,並包上金。 36內院的牆是由三層鑿好的石頭和一層香柏木建的。

37耶和華的殿在所羅門執政第四年的西弗月奠基, 38在他執政的第十一年的布勒月,即八月全部按規格建成,歷經七年。