New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 19:1-21

ኤልያስ ወደ ኮሬብ ኰበለለ

1አክዓብ በዚህ ጊዜ፣ ኤልያስ ያደረገውን በሙሉ፣ ነቢያቱንም ሁሉ እንዴት በሰይፍ እንዳስገደላቸው ለኤልዛቤል ነገራት። 2ስለዚህም እርሷ፣ “ነገ በዚህ ሰዓት ያንተንም ነፍስ ከእነዚያ እንደ አንዱ ነፍስ ሳላደርጋት ብቀር አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ” ስትል ወደ ኤልያስ መልእክተኛ ላከች።

3ኤልያስም ፈርቶ19፥3 ወይም ኤልያስ አይቶ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል ስለ ነበር፣ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ሸሸ። በይሁዳ ምድር ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ እንደ መጣም አገልጋዩን በዚያ ተወው፤ 4በምድረ በዳም ውስጥ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዘ፤ ወደ አንድ ክትክታ ዛፍ እንደ መጣም፣ ከሥሩ ተቀምጦ፣ ይሞት ዘንድ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅቶኛል፤ እኔ ከቀደሙት አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት” ብሎ ጸለየ። 5ከዚያም ከዛፍ ሥር ተጋደመ፤ እንቅልፍም ወሰደው።

በድንገትም አንድ መልአክ ነካ አደረገውና፣ “ተነሥና ብላ” አለው። 6ዘወር ብሎ ሲመለከትም፣ እነሆ፣ በፍም የተጋገረ እንጎቻና አንድ ገንቦ ውሃ ከራስጌው አገኘ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ ተኛ።

7የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና መጥቶ ነካ አደረገውና፣ “ሩቅ መንገድ ስለምትሄድ ተነሥና ብላ” አለው። 8ስለዚህም ተነሥቶ በላ፤ ጠጣም፤ በምግቡም ብርታት አግኝቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ እስኪደርስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተጓዘ፤ 9በዚያም ወደ አንዲት ዋሻ ገብቶ ዐደረ።

እግዚአብሔር ለኤልያስ ተገለጠለት

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እርሱ መጣ፤ “ኤልያስ ሆይ፤ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” አለው።

10እርሱም፣ “እኔ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ እስራኤላውያን ኪዳንህን ትተዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና። የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አሁንም እኔን ለመግደል ይፈልጋሉ” አለ።

11እግዚአብሔርም፣እግዚአብሔር በዚያ ያልፋልና ወደ ተራራው ወጥተህ በእግዚአብሔር ፊት ቁም” አለው።

ከዚያም ታላቅና ኀይለኛ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም በእግዚአብሔር ፊት ብትንትናቸውን አወጣ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ከነፋሱም ቀጥሎ የምድር መነዋወጥ ሆነ፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መነዋወጡ ውስጥ አልነበረም። 12ከምድር መነዋወጡም ቀጥሎ እሳት መጣ፤ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም ቀጥሎ ለስ ለስ ያለ ድምፅ ተሰማ። 13ኤልያስም ይህን ሲሰማ፣ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፍኖ ወጣና በዋሻው ደጃፍ ቆመ።

ከዚያም፣ “ኤልያስ ሆይ፤ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ።

14እርሱም፣ “እኔ ሁሉን ለሚችል ጌታ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ እስራኤላውያን ኪዳንህን ትተዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና። የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አሁንም እኔን ለመግደል ይፈልጋሉ” አለ።

15እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “በመጣህበት መንገድ ተመልሰህ ወደ ደማስቆ ምድረ በዳ ሂድ፤ እዚያ ስትደርስም አዛሄልን በሶርያ ላይ እንዲነግሥ ቅባው። 16እንዲሁም የናሜሲን ልጅ ኢዩን በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ቅባው፤ ደግሞም ነቢይ ሆኖ በእግርህ እንዲተካ የአቤል ምሖላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው። 17ከአዛሄል ሰይፍ ያመለጠውን ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ ሰይፍ ያመለጠውን ደግሞ ኤልሳዕ ይገድለዋል። 18እኔም ጒልበታቸው ለበኣል ያልተንበረከከውንና አፋቸው ምስሉን ያልሳመውን ሰባት ሺህ ሰዎች በእስራኤል አስቀራለሁ።”

የኤልሳዕ መጠራት

19ስለዚህ ኤልያስ ከዚያ ተነሥቶ ሲሄድ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬ አውጥቶ ራሱ በዐሥራ ሁለተኛው ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ መጥቶ መጐናጸፊያውን በላዩ ጣለበት። 20ከዚያም ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ኤልያስን ተከትሎ እየሮጠ፣ “አባቴንና እናቴን ስሜ እንድሰናበታቸው ፍቀድልኝ፤ ከዚያም እከተልሃለሁ” አለው።

ኤልያስም መልሶ፣ “እኔ ምን ያደረግሁህ ነገር አለ? ልትመለስ ትችላለህ” አለው።

21ስለዚህም ኤልሳዕ ትቶት ተመለሰ። ሁለቱን በሬዎቹን ወስዶ ዐረደ፤ የዕርሻ ዕቃውን አንድዶ ሥጋቸውን በመቀቀል ለሕዝቡ ሰጠ፤ እነርሱም በሉ። ከዚያም ኤልያስን ለመከተል ሄደ፤ ረዳቱም ሆነ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

列王紀上 19:1-21

以利亞逃亡

1亞哈以利亞做的一切事以及他怎樣殺掉所有巴力先知的經過,都告訴了耶洗別2耶洗別就派人去告訴以利亞,說:「明天這個時候,我若不使你像那些人一樣喪命,願神明重重地懲罰我。」

3以利亞很害怕,連忙逃命,來到猶大別示巴。他讓僕人留在那裡, 4自己在曠野走了一天的路程,來到一棵羅騰樹下,坐下來禱告求死,說:「耶和華啊,我受夠了,求你取走我的性命吧,我不比我的祖先強。」 5他躺在樹下睡著了。有一位天使拍醒他,說:「起來吃東西吧。」 6他睜開眼睛,見頭邊有用炭火烤好的餅和一瓶水。他吃喝完畢,又躺下來。 7耶和華的天使第二次來拍醒他,說:「起來吃東西吧,你還要走很遠的路。」 8以利亞起來吃喝,就有了力氣,走了四十晝夜,來到上帝的山——何烈山。

9他進了一個山洞,在裡面過夜。耶和華就問他:「以利亞,你在這裡做什麽?」 10以利亞回答說:「我一向熱心事奉萬軍之上帝耶和華。但以色列人背棄你的約,拆毀你的祭壇,殘殺你的先知。現在只剩下我一個人,他們還要殺我。」 11耶和華說:「你出來站在山上,站在我面前。」耶和華從那裡經過時,疾風大作,劈山碎石,但耶和華不在風中。疾風過後又有地震,但耶和華不在其中。 12地震之後又有火,但耶和華也不在火中。之後,傳來微小的聲音。 13以利亞聽見後,就用外袍蒙著臉出去站在洞口。那聲音問他:「以利亞,你在這裡做什麽?」 14以利亞回答說:「我一向熱心事奉萬軍之上帝耶和華。但以色列人背棄你的約,拆毀你的祭壇,殘殺你的先知。現在只剩下我一個人,他們還要殺我。」 15耶和華吩咐他說:「你原路返回,前往大馬士革附近的曠野,到了之後要膏立哈薛亞蘭王。 16然後,再膏立寧示的孫子耶戶以色列王,還要膏立亞伯·米何拉沙法的兒子以利沙做先知來接替你。 17將來從哈薛刀下逃生的,必被耶戶殺死;從耶戶刀下逃生的,必被以利沙殺死。 18此外,我在以色列留下七千人,他們未曾跪拜巴力,也未曾親吻巴力。」

呼召以利沙

19於是,以利亞離開那裡,找到沙法的兒子以利沙,他正在耕田。他前面有十二對牛,他正趕著第十二對。以利亞走過以利沙身邊時,將自己的外袍搭在他身上。 20以利沙就撇下牛,追上以利亞說:「請你讓我先回去與父母親吻道別,再跟你走吧。」以利亞說:「你回去吧,別忘了我剛才對你做的事。」 21以利沙就回去了。他宰了兩頭耕牛,用耕具作柴煮肉分給眾人,然後去跟隨以利亞,服侍他。