New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 15:1-34

የይሁዳ ንጉሥ አብያ

15፥1-2፡7-8 ተጓ ምብ – 2ዜና 13፥1-2፡22–14፥1

1የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ15፥1 በዚህ ስፍራና በቍ 7 እና 8 ላይ እንዳንድ የዕብራይስጥና የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ትርጒሞች ግን፤ አቢጃም ይላሉ በይሁዳ ነገሠ፤ 2በኢየሩሳሌም ሆኖ ሦስት ዓመት ገዛ፤ እናቱ መዓካ የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች።

3እርሱም አባቱ ከእርሱ በፊት የሠራውን ኀጢአት ሁሉ ሠራ፤ እንደ አባቱ እንደ ዳዊትም በፍጹም ልቡ በታማኝነት ለእግዚአብሔር አልተገዛም። 4ነገር ግን ከእርሱ ቀጥሎ እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምን እንዲያጸናት፣ አምላክ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል በኢየሩሳሌም መብራት ሰጠው። 5ዳዊት በኬጢያዊው በኦርዮ ላይ ካደረሰው በደል በቀር፣ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ፈቀቅ ያለበት ጊዜ አልነበረም።

6አብያም15፥6 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ከዚህ ጋር ይስማማሉ አንዳንድ የዕብራይስጥና የሱርስት ትርጒሞች ግን፣ አቢጃም ይላሉ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበር። 7ሌላው አብያ በዘመኑ የፈጸመውና ያደረገው ሁሉ፣ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? በአብያና በኢዮርብዓም መካከልም ጦርነት ነበር። 8አብያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ። ልጁም አሳ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

የይሁዳ ንጉሥ አሳ

15፥9-22 ተጓ ምብ – 2ዜና 14፥2-3፤ 15፥16–16፥6

15፥23-24 ተጓ ምብ – 2ዜና 16፥11–17፥1

9የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በሃያኛው ዓመት፣ አሳ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤ 10በኢየሩሳሌምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ አያቱ መዓካ ትባላለች፤ እርሷም የአቤሴሎም ልጅ ነበረች።

11አሳ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር አደረገ። 12የቤተ ጣዖት ወንደቃዎችን ከምድሪቱ አባረረ፤ አባቶቹ የሠሯቸውን ጣዖታት ሁሉ አስወገደ። 13አስጸያፊውን የአሼራ ምስል ዐምድ በማቆሟ፣ አያቱን መዓካን ከእቴጌነቷ ሻራት፤ ጣዖቷንም ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው። 14አሳ የማምለኪያ ኰረብታዎችን ፈጽሞ ባያስወግድም እንኳ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ፣ ልቡ ለእግዚአብሔር የተገዛ ነበር። 15አባቱና እርሱ ለእግዚአብሔር የቀደሱትን ብርና ወርቅ እንዲሁም ዕቃዎችን አምጥቶ ወደ እግዚአብሔር ቤት አስገባ።

16አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ዘመነ መንግሥታቸውን ያሳለፉት፣ እርስ በርስ በመዋጋት ነበር። 17የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ይሁዳን ለመውጋት ወጣ፤ ከዚያም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ ግዛት ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ ለመቈጣጠር ራማን ምሽግ አድርጎ ሠራት።

18አሳም በእግዚአብሔር ቤትና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት የቀረውን ብርና ወርቅ በሙሉ ወሰደ፤ ከዚያም በታማኝ ሹማምቱ እጅ በደማስቆ ይገዛ ለነበረው፣ ለጠብሪሞን ልጅ፣ የአዚን የልጅ ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ለቤን ሀዳድ ላከው። 19እንዲህም አለ፤ “በአባቴና በአባትህ መካከል የስምምነት ውል እንደ ነበረ ሁሉ፣ አሁንም በእኔና በአንተ መካከል ይኑር፤ እነሆ፣ የብርና የወርቅ ገጸ በረከት ልኬልሃለሁ። አሁንም የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ወደ መጣበት እንዲመለስ፣ ሄደህ ከእርሱ ጋር ያደረግኸውን የስምምነት ውል አፍርስ።”

20ቤንሀዳድም የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ፣ የጦር አዛዦቹን በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ፤ ዒዮንን፣ ዳንን፣ አቤልቤት ማዕካን እንዲሁም ንፍታሌምን ጨምሮ ጌንሳሬጥን በሙሉ ድል አደረገ። 21ባኦስም ይህን ሲሰማ፣ በራማ የጀመረውን የምሽግ ሥራ አቁሞ ወደ ቴርሳ ተመለሰ። 22ንጉሥ አሳ አንድም ሰው እንዳይቀር በይሁዳ ሁሉ ዐዋጅ አስነገረ፤ ከዚያም ሕዝቡ ባኦስ በራማ አስቀምጦት የነበረውን ድንጋይና ዕንጨት አጋዘ፤ ንጉሡም በዚሁ ምጽጳንና በብንያም ውስጥ ጌባን ሠራ።

23በአሳ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር በሙሉ፣ ያደረገውም ሁሉና የሠራቸውም ከተሞች በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፈው የሚገኙ አይደሉምን? ንጉሥ አሳ በሸመገለ ጊዜ ግን እግሮቹ ታመሙ። 24አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ ኢዮሣፍጥም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

የእስራኤል ንጉሥ ናዳብ

25በይሁዳ ንጉሥ በአሳ ዘመነ መንግሥት በሁለተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ናዳብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ሁለት ዓመትም ገዛ። 26እርሱም በአባቱ መንገድ በመሄድ፣ አባቱ የሠራውንና እስራኤልም እንዲሠሩ ያደረገውን ኀጢአት በመሥራት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ።

27ናዳብና መላው እስራኤል በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከበው ሳሉ፣ ከይሳኮር ነገድ የተወለደው የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐምፆ በመነሣት ናዳብን በገባቶን ገደለው። 28ባኦስ ናዳብን የገደለውና በእግሩ ተተክቶ የነገሠው፣ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነው።

29ወዲያውኑ እንደ ነገሠም የኢዮርብዓምን ቤተ ሰብ በሙሉ ፈጀ። እግዚአብሔር በሴሎናዊው ባሪያው በአኪያ በኩል እንደ ተናገረው፣ ከኢዮርብዓም ቤተ ሰብ አንድም ሰው በሕይወት ሳያስቀር፣ ሁሉንም አጠፋቸው፤ 30ይህም የሆነው ኢዮርብዓም በሠራው ኀጢአትና እስራኤልም እንዲሠሩ በማድረጉ ምክንያት፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን ለቊጣ በማነሣሣቱ ነው።

31ሌላው በናዳብ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው፣ እርሱም ያደረገው ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 32አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ዘመነ መንግሥታቸውን ያሳለፉት እርስ በርስ በመዋጋት ነበር።

የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ

33የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በቴርሳ ከተማ፣ በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ሃያ አራት ዓመትም ገዛ። 34በኢዮርብዓም መንገድ በመሄድና እስራኤልም እንዲሠሩ ያደረገውን ኀጢአት በመፈጸም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠራ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

列王紀上 15:1-34

亞比央做猶大王

1尼八的兒子耶羅波安王執政第十八年,亞比央登基做猶大王, 2他在耶路撒冷執政三年,母親是押沙龍的女兒瑪迦

3亞比央和他父親一樣作惡多端,沒有像他祖先大衛一樣忠於他的上帝耶和華。 4但他的上帝耶和華因為大衛的緣故,仍然讓他兒子在耶路撒冷繼位,使耶路撒冷堅立。 5除了烏利亞事件以外,大衛一生都做耶和華視為正的事,沒有違背耶和華的任何命令。

6羅波安耶羅波安之間常有戰事,一直延續到亞比央王朝。 7亞比央耶羅波安之間也常有戰事。亞比央其他的事及其一切所作所為都記在猶大的列王史上。 8亞比央與祖先同眠後葬在大衛城,他兒子亞撒繼位。

亞撒做猶大王

9耶羅波安以色列王第二十年,亞撒登基做猶大王, 10他在耶路撒冷執政四十一年。他祖母是押沙龍的女兒瑪迦11亞撒效法他祖先大衛,做耶和華視為正的事。 12他從國中驅逐了男廟妓,清除了他祖先製造的一切神像。 13亞撒還廢除了他祖母瑪迦的太后之位,因為她造了可憎的亞舍拉神像。亞撒把她的神像砍倒,放在汲淪溪燒掉。 14雖然他沒有拆毀邱壇,但他一生忠於耶和華。 15他又把他父親和他自己所獻上的金銀和器皿都帶到耶和華的殿裡。

16亞撒以色列巴沙之間常有爭戰。 17以色列巴沙上來攻打猶大,他修築拉瑪城,企圖隔斷猶大亞撒與外界的聯繫。 18於是,亞撒把耶和華殿裡和王宮庫房裡剩餘的金銀交給臣僕,派他們送給大馬士革亞蘭王,即他伯利們的兒子、希旬的孫子便·哈達,說: 19「我們之間應立盟約,像我們的父親之間立約一樣,現在奉上金銀為禮,請你取消與以色列巴沙立的盟約。這樣,他就會從我境內退兵。」 20便·哈達接受了亞撒王的提議,派將領攻打以色列的城邑,攻佔了以雲亞伯·伯·瑪迦基尼烈全境和拿弗他利全境。 21巴沙聞訊,就停止修築拉瑪,退回得撒去了。 22亞撒王令全國的猶大人出動,將巴沙修築拉瑪城的石頭和木材搬走,用來修建便雅憫迦巴米斯巴23亞撒其他的事蹟、功業和他興建的城邑都記在猶大的列王史上。亞撒年老的時候,患了腳疾。 24他與祖先同眠後,葬在大衛城他的祖墳裡。他兒子約沙法繼位。

拿答做以色列王

25亞撒猶大王第二年,耶羅波安的兒子拿答登基做以色列王,執政兩年。 26拿答像他父親一樣作惡多端,行耶和華視為惡的事,使以色列人陷入罪中。 27-28亞撒猶大王第三年,拿答以色列軍圍攻非利士基比頓城時,以薩迦支派亞希雅的兒子巴沙叛變,殺了拿答,篡位稱王。 29巴沙一做王,立刻誅殺耶羅波安全家,無一倖免,應驗了耶和華藉祂僕人——示羅亞希雅所說的話。 30這是因為耶羅波安犯罪,並使以色列人陷入罪中,惹以色列的上帝耶和華發怒。 31拿答其他的事及其一切所作所為都記在以色列的列王史上。 32亞撒以色列巴沙執政期間,雙方常常爭戰。

巴沙做以色列王

33猶大亞撒執政第三年,亞希雅的兒子巴沙得撒登基做以色列王,執政二十四年。 34他步耶羅波安的後塵,做耶和華視為惡的事,使以色列人陷入罪中。