New Amharic Standard Version

1 ተሰሎንቄ 2:1-20

የጳውሎስ አገልግሎት በተሰሎንቄ

1ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ የመጣነው ለከንቱ እንዳልሆነ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 2እንደምታውቁት ከዚህ ቀደም በፊልጵስዩስ መከራ ተቀብለን ተንገላታን፤ ነገር ግን ብርቱ ተቃውሞ ቢደር ስብንም እንኳ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንደምናበሥር በአምላካችን ድፍረት አገኘን። 3የምናቀርበው ልመና ከስሕተት ወይም ከክፉ ዐላማ ወይም እናንተን ለማታለል ከመፈለግ የመነጨ አይደለም። 4ነገር ግን ወንጌልን በዐደራ ለመቀበል እግዚአብሔር ብቁ አድርጎ እንደ ቈጠራቸው ሰዎች ሆነን እንናገራለን። ይህንም የምናደርገው ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን እንጂ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት ብለን አይደለም። 5የሽንገላ ቃል ከቶ እንዳልተናገርን ወይም ሥሥትን ለመሸፈን ብለን አስመሳዮች እንዳልሆንን ታውቃላችሁ፤ ለዚህም እግዚአብሔር ምስክራችን ነው። 6ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ከማንም፣ ከሰው የሚገኝ ክብር አልፈለግንም። የክርስቶስ ሐዋርያት እንደ መሆናችን መጠን ሸክም በሆንባችሁ ነበር፤ 7ነገር ግን እናት ልጅዋን እንደምትንከባከብ እኛም በመካከላችሁ በየዋህነት ተመላለስን።

8የእግዚአብሔርን ወንጌል ብቻ ሳይሆን ሕይወታችንን ጭምር ልናካፍላችሁ ደስ እስከሚለን ድረስ ወደድናችሁ፤ ምክንያቱም እናንተ በእኛ ዘንድ ተወዳጆች ነበራችሁ። 9ወንድሞች ሆይ፤ ጥረታችንንና ድካማችንን ታስታውሳላችሁ፤ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እየሠራን ወንጌል ሰበክንላችሁ።

10በእናንተ በምታምኑት መካከል ሳለን እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅ እንዲሁም ያለ ነቀፋ ሆነን እንደኖርን እናንተም እግዚአብሔርም ምስክሮች ናችሁ። 11አባት ለገዛ ልጆቹ እንደሚሆን እኛም ለእያንዳንዳችሁ የቱን ያህል እንደሆንን ታውቃላችሁና፤ 12ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትኖሩ ዘንድ አበረታታናችሁ፤ አጽናናችሁ፤ አጥብቀንም ለመንናችሁ።

13ከእኛ የሰማችሁትን የእግዚአብሔርን ቃል በተቀበላችሁ ጊዜ፣ በእናንተ በምታምኑት ዘንድ በርግጥ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት እግዚአብሔርን ያለ ማቋረጥ እናመሰግናለን። 14ወንድሞች ሆይ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን በይሁዳ የሚገኙትን የእግዚአብሔርን አብያተ ክርስቲያናት መስላችኋል፤ እነዚያ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፣ እናንተም ከገዛ ወገኖቻችሁ መከራን ተቀብላችኋል። 15እነርሱ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፤ እኛንም አሳደዱን፤ እግዚአብሔርንም ደስ አላሰኙትም፤ የሰውም ሁሉ ፀር ሆኑ፤ 16ይኸውም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ለመከልከል ነው፤ በዚህ ሁኔታ ኀጢአታቸውን ሁል ጊዜ በራሳቸው ላይ እስከ መጨረሻው እያከማቹ ይሄዳሉ። ቊጣውም በእነርሱ ላይ ያለ ልክ መጥቶአል2፥16 ወይም በሙላት መጥቶአል

ጳውሎስ የተሰሎንቄን ሰዎች ለማየት የነበረው ናፍቆት

17ነገር ግን ወንድሞች ሆይ፤ እኛ በልባችን ሳይሆን በአካል ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ብንለይም፣ ለእናንተ ካለን ታላቅ ናፍቆት የተነሣ ፊታችሁን ለማየት ብርቱ ጥረት አደረግን። 18ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፤ በተለይም እኔ ጳውሎስ ብዙ ጊዜ ሞክሬ ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን አዘገየኝ። 19ጌታችን ኢየሱስ ሲመጣ በእርሱ ፊት ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም አክሊላችን ማን ነው? እናንተ አይደላችሁምን? 20በርግጥ ክብራችንም ደስታችንም ናችሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

帖撒罗尼迦前书 2:1-20

保罗在帖撒罗尼迦的工作

1弟兄姊妹,你们自己知道,我们那次探望你们并没有白费。 2你们也知道,我们之前在腓立比遭受了迫害和凌辱,遇到强烈的反对,但仍然靠着我们的上帝放胆向你们传扬祂的福音。 3我们的劝勉并非出于谬误、不良动机或诡诈。 4我们得到了上帝的认可,受委派传福音。我们不是要取悦人,而是要取悦鉴察我们内心的上帝。

5你们知道,我们没有花言巧语奉承人,也没有心存贪念,上帝可以为我们作证。 6我们不求得到你们或其他任何人的赞扬。 7身为基督的使徒,我们理当受到你们的尊重,然而我们像母亲抚育婴儿一样温柔地对待你们。 8我们深爱你们,对你们有深厚的感情,不仅乐意把上帝的福音传给你们,甚至把生命给你们也在所不惜。

9弟兄姊妹,你们一定记得我们的劳苦和艰难。我们一面向你们传福音,一面昼夜辛勤工作,免得成为你们任何人的负担。 10我们怎样以圣洁、公义、纯全的方式对待你们众信徒,你们自己可以作证,上帝也可以作证。 11你们也知道,我们对待你们就像父亲对待自己的孩子一样。 12我们安慰你们,劝勉你们,督促你们,好叫你们行事为人对得起上帝,祂呼召你们进入祂的国、享受祂的荣耀。

13我们不住地感谢上帝,因为你们从我们这里听了上帝的道后就接受了,确信这不是人的道理,而是上帝的道。这道正在你们信的人心里发挥作用。

14弟兄姊妹,你们的遭遇和犹太地区基督耶稣的众教会的遭遇一样。你们受到了自己同胞的迫害,他们也受到了犹太人的迫害。 15这些犹太人杀死了主耶稣和众先知,又迫害我们。他们不但冒犯上帝,还与所有的人为敌, 16阻止我们传福音给外族人,唯恐他们得救。这些人恶贯满盈,上帝的烈怒终于临到了他们头上。

保罗渴望去帖撒罗尼迦

17弟兄姊妹,我们暂时与你们分离,心灵却与你们在一起。我们非常渴望见到你们。 18我们想去你们那里,我保罗也一次又一次地想去,只是遭到撒旦的拦阻。 19我们主耶稣再来的时候,我们在祂面前的盼望、喜乐和可夸耀的冠冕是什么呢?不就是你们吗? 20因为你们是我们的荣耀和喜乐。