1 ቆሮንቶስ 16 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

1 ቆሮንቶስ 16:1-24

ለቅዱሳን የተደረገ የገንዘብ መዋጮ

1አሁን ደግሞ ለቅዱሳን ስለሚደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ፤ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት በሰጠሁት ትእዛዝ መሠረት አድርጉ። 2ገንዘብ ማሰባሰብ የሚደረገው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን፣ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደ ገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ። 3በምመጣበት ጊዜ እናንተ ለመረጣችኋቸው ሰዎች የመሸኛ ደብዳቤ ሰጥቼ ስጦታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያደርሱ እልካቸዋለሁ። 4የእኔ መሄድ የሚያስፈልግ ከሆነ አብረውኝ ይሄዳሉ።

የሐዋርያው ዕቅድ

5በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር፣ መቄዶንያ ከደረስሁ በኋላ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 6ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጕዞዬ እንድትረዱኝ፣ እናንተ ዘንድ እቈይ ይሆናል፤ ምናልባትም ክረምቱን ከእናንተ ጋር እሰነብት ይሆናል። 7አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጐበኛችሁ አልፈልግም፤ ጌታ ቢፈቅድ ረዘም ላለ ጊዜ እናንተ ዘንድ ለመሰንበት ተስፋ አደርጋለሁ። 8ነገር ግን እስከ በዓለ አምሳ በኤፌሶን እቈያለሁ፤ 9ምክንያቱም ታላቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤ ብዙ ተቃዋሚዎችም አሉብኝ።

10ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፣ አብሯችሁ ያለ ፍርሀት እንዲቀመጥ አድርጉ፤ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና። 11ስለዚህ ማንም አይናቀው፤ በሰላም ወደ እኔ እንዲመለስ ርዱት፤ መመለሱንም ከወንድሞች ጋር እየጠበቅን ነው።

12ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፣ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።

13ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤ 14የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።

15የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች በአካይያ የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እለምናችኋለሁ፤ 16እንደ እነርሱ ላሉትና ከእነርሱም ጋር በአገልግሎት ለሚደክሙ ሁሉ ታዘዙ።

17እስጢፋኖስ፣ ፈርዶናጥስና አካይቆስ በመምጣታቸው ደስ ብሎኛል፤ ምክንያቱም እናንተ እዚህ ባለመኖራችሁ የጐደለኝን አሟልተዋል፤ 18የእኔንም የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋልና። ስለዚህ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች መታወቅ ይገባቸዋል።

የመሰናበቻ ቃል

19በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

አቂላና ጵርስቅላ16፥19 በግሪኩ ጵርስቃየጵርስቅላ ሌላው አጠራር ነው።፣ በቤታቸውም ያለችው ቤተ ክርስቲያን የከበረ ሰላምታ በጌታ ያቀርቡላችኋል።

20ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።

21ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁላችሁ እኔ ጳውሎስ ነኝ።

22ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታ ሆይ፤ ና!16፥22 በአራማይክ ጌታ ሆይ፤ ና ማለት ማራናታ ማለት ነው።

23የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

24ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ነው፤ አሜን።16፥24 አንዳንድ ቅጆች አሜን የሚለው የላቸውም።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

哥林多前书 16:1-24

捐助圣徒

1至于捐款帮助圣徒这件事,你们可以照我吩咐加拉太各教会的方法办理。 2每逢周日,各人应按照自己的收入抽出一部分留起来,免得我到的时候才现凑。 3我到了以后,会差遣你们委托的人带着推荐信把你们的捐款送到耶路撒冷4如果我也需要去的话,他们可以跟我一起去。

保罗的计划

5我正打算从马其顿经过,过了马其顿,我就去探望你们。 6我也许会和你们住一段时期,甚至在你们那里过冬。之后,我无论去什么地方,你们都可以给我送行。 7我不想只是现在顺道探望你们,主若许可,我盼望能够和你们同住一段时期。 8我会在以弗所停留到五旬节, 9因为大门为我敞开了,工作很有成效,不过反对我的人也很多。

10提摩太到了以后,你们要好好接待他,让他在你们那里安心,因为他和我一样,都是在为主做工。 11所以谁也不许轻视他。你们要帮助他平安地回到我这里,我正在等候他和弟兄们同来。 12至于亚波罗弟兄,我虽然再三劝他和弟兄们去你们那里,但他目前还不愿启行。不过他有机会就会去。

劝勉与问候

13你们要警醒,在信仰上坚定不移,做勇敢刚强的人。 14无论做什么事,都要有爱心。

15弟兄姊妹,你们都知道司提法纳一家在亚该亚是最早信主的16:15 最早信主的”希腊文是“最早的果子”。,也知道他们怎样尽心竭力地服侍圣徒。 16你们要顺服这样的人,也要顺服所有同心努力服侍的人。 17我很高兴司提法纳福徒拿都亚该古来我这里,因为你们帮不到我的地方,他们都补足了。 18他们使我和你们心里都感到十分欣慰,你们要敬重这样的人。

19亚细亚的各教会问候你们。亚居拉百基拉夫妇和常在他们家里聚会的信徒,奉主的名衷心地向你们问安。 20全体弟兄姊妹都问候你们。你们要以圣洁的吻彼此问候。

21保罗亲笔问候你们。

22如果有人不爱主,这人可咒可诅!主啊,我愿你来!

23愿主耶稣基督的恩典与你们同在! 24我在基督耶稣里爱你们所有的人。阿们!