ፊልጵስዩስ 1 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ፊልጵስዩስ 1:1-30

1የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፤

ከቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳትና1፥1 ወይም ተመልካች ጠባቂዎች ከዲያቆናት ጋር በፊልጵስዩስ ላሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፤

2ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ምስጋናና ጸሎት

3እናንተን ባስታወስሁ ቍጥር አምላኬን አመሰግናለሁ። 4ዘወትር ስለ ሁላችሁ ስጸልይ፣ በደስታ እጸልያለሁ፤ 5ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እስካሁን ድረስ በወንጌል አገልግሎት ተካፋይ ሆናችኋልና። 6በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው ርግጠኛ ነኝ።

7በልቤ ስላላችሁ፣ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰቤ ተገቢ ነው፤ በእስራቴም ሆነ ለወንጌል ስመክትና ሳጸናው ሁላችሁም ከእኔ ጋር የእግዚአብሔር ጸጋ ተካፋዮች ናችሁና። 8በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁንም ምን ያህል እንደምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።

9ፍቅራችሁ በጥልቅ ዕውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ። 10ይኸውም ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ፣ እስከ ክርስቶስም ቀን ድረስ ንጹሓንና ነቀፋ የሌለባችሁ እንድትሆኑ፣ 11ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ እንድትሞሉ ነው።

በጳውሎስ እስራት ወንጌል መስፋፋቱ

12አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ በእኔ ላይ የደረሰው ነገር ወንጌል በይበልጥ እንዲስፋፋ መርዳቱን ታውቁ ዘንድ እወድዳለሁ። 13ከዚህ የተነሣ እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንደ ሆነ፣ በቤተ መንግሥት ዘበኞችና1፥13 ወይም በቤተ መንግሥት ሁሉ በሌሎችም ሁሉ ዘንድ ታውቋል። 14በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ካሉት ወንድሞች ብዙዎቹ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሀት፣ በድፍረት ለመናገር ብርታት አግኝተዋል።

15አንዳንዶች ከቅናትና ከፉክክር የተነሣ፣ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብካሉ። 16እነዚህ፣ እኔ ለወንጌል ለመሟገት እዚህ እንዳለሁ ስለሚያውቁ፣ በፍቅር ይህን ያደርጋሉ፤ 17እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ ሳለሁ መከራ ሊያጸኑብኝ ዐስበው፣ በቅንነት ሳይሆን ለግል ምኞታቸው ሲሉ ክርስቶስን ይሰብካሉ1፥16-17 አንዳንድ ጥንታዊ ያልሆኑ ቅጆች የ16 እና 17 ቅደም ተከተል ለዋውጠውታል።18ታዲያ ችግሩ ከምኑ ላይ ነው? ቁም ነገሩ በቅንነትም ይሁን በማስመሰል በማንኛውም መንገድ ክርስቶስ መሰበኩ ነው። በዚህም ደስ ይለኛል።

አዎን፤ ደስ ይለኛል፤ 19በእኔ ላይ የደረሰው ነገር፣ በጸሎታችሁ አማካይነትና ከኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በተሰጠ ረድኤት ለመዳኔ1፥19 ወይም ለትድግናዬ እንደሚሆን ዐውቃለሁና። 20በምንም ዐይነት መንገድ ዐፍሬ እንዳልገኝ ጽኑ ናፍቆትና ተስፋ አለ፤ ነገር ግን እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በሕይወትም ሆነ በሞት ክርስቶስ በሥጋዬ እንዲከበር ሙሉ ድፍረት ይኖረኛል። 21ለእኔ፣ መኖር ክርስቶስ ነው፤ ሞትም ማትረፍ ነው። 22በሥጋ ከቈየሁ፣ ፍሬያማ ተግባር ይኖረኛል፤ ነገር ግን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም። 23በእነዚህ በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ፣ ከክርስቶስም ጋር ልሆን እናፍቃለሁ፤ ይህ እጅግ የተሻለ ነውና። 24ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ለእናንተ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። 25ይህን በማስተዋል፣ በእምነት እንድታድጉና ደስ እንዲላችሁ፣ በሁላችሁ ዘንድ እንደምቈይና እንደምኖር ተረድቻለሁ። 26እንደ ገና መጥቼ በእናንተ ዘንድ በምሆንበት ጊዜ፣ በእኔ ምክንያት በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁ ደስታ ይበዛላችኋል።

27ብቻ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ፤ ይህ ከሆነ መጥቼ ባያችሁ ወይም በርቀት ሆኜ ስለ እናንተ ብሰማ፣ ለወንጌል እምነት እንደ አንድ ሰው ሆናችሁ በመጋደል በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ እንደምትቆሙ ዐውቃለሁ። 28በማንኛውም መንገድ በተቃዋሚዎቻችሁ አትሸበሩ፤ ይህ እነርሱ እንደሚጠፉ፣ እናንተ ግን እንደምትድኑ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ምልክት ነው። 29በክርስቶስ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን ስለ እርሱ መከራ እንድትቀበሉም ይህ ጸጋ ተሰጥቷችኋልና፤ 30ቀድሞ እንዳያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ በምትሰሙት በዚያው ዐይነት ተጋድሎ እናንተም እያለፋችሁ ነውና።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

腓立比書 1:1-30

1保羅提摩太是基督耶穌的奴僕,寫信給腓立比屬於基督耶穌的眾聖徒、諸位監督和執事。

2願我們的父上帝和主耶穌基督賜給你們恩典和平安!

感恩和禱告

3我每逢想起你們,就感謝我的上帝。 4每次為你們眾人禱告的時候,我心裡都很喜樂。 5因為你們從開始直到現在,一直和我同心合意地傳揚福音。 6我深信,上帝既然在你們心裡開始了這美好的工作,祂必在耶穌基督再來的時候完成這工作。 7我對你們眾人有這樣的感受是很自然的,因為我常把你們放在心上1·7 我常把你們放在心上」或譯「你們常把我放在心上」。。不論我是身在獄中,還是為福音辯護和作證的時候,你們都與我同蒙恩典。 8上帝可以作證,我是怎樣以基督耶穌的慈愛之心想念你們。

9我所祈求的就是:你們的愛心隨著屬靈知識的增加和辨別力的提高而日益增長, 10使你們知道怎樣擇善而從,做誠實無過的人,一直到基督再來的日子, 11並靠著耶穌基督結滿仁義的果子,使上帝得到榮耀與頌讚。

為基督而活

12弟兄姊妹,我希望你們知道,我的遭遇反而會使福音傳得更廣, 13連所有的皇家衛兵和其他眾人都知道我是為了基督的緣故而受囚禁。 14大多數主內的弟兄姊妹看見我為主被囚,信心受到鼓舞,更加放膽無懼地傳揚上帝的道。 15當然,有些人宣講基督是出於嫉妒和爭強好勝,也有些人是出於善意。 16後者是出於愛心,知道我是上帝派來維護福音的。 17前者傳講基督是出於個人野心,動機不純,以為可以增加我在獄中的痛苦。 18那又怎樣呢?無論他們傳福音是真心還是假意,基督的福音畢竟傳開了,因此我很歡喜,而且歡喜不已。 19因為我知道,藉著你們的禱告和耶穌基督之靈的幫助,我終會得到釋放。

20我殷切地期待和盼望:我不會感到任何羞愧,而是放膽無懼,不管是生是死,都要一如既往地使基督在我身上得到尊崇。 21因為對我來說,活著是為了基督,死了也有益處。 22如果活在世上,我可以做工,多結果子。我真不知道該怎麼選擇! 23我處在兩難之間。我情願離開世界,與基督在一起,那實在是再好不過了。 24可是為了你們,我應該活在世上。 25我既然對此深信不疑,就知道自己仍要活下去,繼續跟你們在一起,好使你們在信仰上又長進又充滿喜樂。 26這樣,我再到你們那裡的時候,你們可以因為我的緣故更加以基督耶穌為榮。

27最要緊的是:你們行事為人要與基督的福音相稱。這樣,不管是去看你們,還是只聽到你們的消息,我都能知道你們同心合意,堅定不移地一起為福音奮鬥, 28毫不懼怕敵人的恐嚇。這清楚表明他們必滅亡,你們必得救,這是出於上帝。 29因為上帝為了基督的緣故,賜恩使你們不但信基督,而且為祂受苦, 30經歷你們從前在我身上見過,現在又從我這裡聽到的同樣爭戰。