ዮሐንስ 15 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዮሐንስ 15:1-27

የወይን ግንድና ቅርንጫፎቹ

1“እውነተኛው የወይን ተክል እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው። 2እርሱም በእኔ ያለውን፣ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን የበለጠ እንዲያፈራ ይገርዘዋል።15፥2 ይገርዘዋል የሚለው የግሪኩ ቃል ያጠራዋል የሚል ትርጕም አለው። 3ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ አሁን ንጹሓን ናችሁ። 4በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ካልሆነ በቀር ብቻውን ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም።

5“እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በእርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና። 6በእኔ የማይኖር ተጥሎ እንደሚደርቅ ቅርንጫፍ ነው፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተለቅመው ወደ እሳት ይጣላሉ፤ ይቃጠላሉም። 7በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም። 8ብዙ ፍሬ በማፍራት ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብትገልጡ፣ በዚህ አባቴ ይከብራል።

9“አብ እንደ ወደደኝ ሁሉ እኔም ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ። 10እኔ የአባቴን ትእዛዝ ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር፣ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። 11ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ። 12ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። 13ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም፤ 14የማዝዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ። 15ከእንግዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ አገልጋይ ጌታው የሚሠራውን አያውቅምና፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጽሁላችሁ ወዳጆች ብያችኋለሁ። 16እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። 17እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ፣ ትእዛዜ ይህች ናት።

ዓለም ደቀ መዛሙርትን መጥላቱ

18“ዓለም ቢጠላችሁ፣ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ። 19ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ፣ ዓለም የራሱ እንደ ሆኑት አድርጎ በወደዳችሁ ነበር፤ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኋችሁ የዓለም አይደላችሁም፤ ዓለም የሚጠላችሁም ስለዚሁ ነው። 20‘አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም’ ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን አሳድደውኝ ከሆነ፣ እናንተንም ያሳድዷችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነም ቃላችሁን ይጠብቃሉ። 21የላከኝን ስለማያውቁ፣ በስሜ ምክንያት ይህን ያደርጉባችኋል። 22መጥቼ ባልነግራቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን ለኀጢአታቸው የሚሰጡት ምክንያት የላቸውም። 23እኔን የሚጠላ፣ አባቴንም ይጠላል። 24ሌላ ሰው ያላደረገውን በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ፣ ኀጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እነዚህን ታምራት አይተዋል፤ ሆኖም እኔንም አባቴንም ጠልተዋል። 25ይህም፣ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።

26“እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ፣ ከአብ የሚወጣው አጽናኙ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል። 27እናንተም ደግሞ፣ ከመጀመሪያው ከእኔ ጋር ስለ ነበራችሁ፣ ትመሰክራላችሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约翰福音 15:1-27

真葡萄树

1耶稣说:“我是真葡萄树,我父是栽培的人。 2属于我的枝子如果不结果子,祂就把它剪掉;如果结果子,祂便修剪它,让它结更多的果子。 3我对你们所讲的道已经使你们洁净了。 4你们要常在我里面,我就常在你们里面。枝子若离开葡萄树,就不能结果子。同样,你们若不常在我里面,也不能结果子。

5“我是葡萄树,你们是枝子。常在我里面的,我也常在他里面,他就会多结果子,因为你们离开了我什么都不能做。 6不常在我里面的人就像丢在外面枯干的枝子,最后只有被人拾起来丢在火里烧掉。 7如果你们常在我里面,我的话也常在你们里面,无论你们求什么,都会得到应允。 8你们多结果子,证明自己是我的门徒,就会给我父带来荣耀。 9父怎样爱我,我也怎样爱你们。你们要常在我的爱中。 10你们若遵守我的命令,就必常在我的爱中,正如我遵守了父的命令,常在父的爱中一样。

11“我把这些事告诉你们,是要叫你们心里有我的喜乐,让你们的喜乐满溢。 12你们要彼此相爱,像我爱你们一样,这就是我的命令。 13为朋友舍命可以说是人间最伟大的爱了。 14你们如果照我的吩咐去做,就是我的朋友。 15我不再称你们为奴仆,因为奴仆不知道主人的事。我称你们为朋友,因为我把从父那里听见的一切都告诉了你们。 16不是你们拣选了我,而是我拣选了你们,并且派你们出去结永存的果子。这样,你们奉我的名无论向父求什么,祂都会赐给你们。 17我把这些事吩咐你们,是要叫你们彼此相爱。

被世人憎恶

18“如果世人恨你们,要知道,他们恨你们以前已经恨我了。 19如果你们属于这个世界,世人一定会爱你们。可是你们不属于这世界,我已经把你们拣选出来,因此世人恨你们。 20你们要记住我说的话,‘奴仆不能大过主人。’他们若迫害我,也必迫害你们;他们若遵行我的话,也必遵行你们的话。 21世人将因为我的名而这样对待你们,因为他们不认识差我来的那位。 22我如果没有来教导他们,他们就没有罪了,但现在他们的罪无可推诿。 23恨我的,也恨我的父。 24我如果没有在他们当中行过空前的神迹,他们就没有罪了。然而,他们亲眼看见了,竟然还恨我和我的父。 25这是要应验他们律法书上的话,‘他们无故地恨我。’

26“我要从父那里为你们差护慰者来,祂就是从父而来的真理之灵。祂来了要为我做见证。 27你们也要为我做见证,因为你们从开始就与我在一起。