ዘፍጥረት 16 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 16:1-16

አጋርና እስማኤል

1የአብራም ሚስት ሦራ፣ ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤ እርሷም አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። 2አብራምንም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋር ተኛ” አለችው።

አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ። 3አብራም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ሚስቱ ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን አጋርን ሚስት እንድትሆነው ለባሏ ሰጠችው። 4አብራምም ከአጋር ጋር ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች። አጋርም ነፍሰ ጡር መሆኗን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን መናቅ ጀመረች። 5ሦራም አብራምን፣ “ለደረሰብኝ በደል ተጠያቂው አንተ ነህ፤ አገልጋዬ ዕቅፍህ ውስጥ እንድትገባ እኔው ሰጠሁህ፤ አሁን ግን ይኸው ማርገዟን ስታውቅ ትንቀኝ ጀመር፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በአንተና በእኔ መካከል ይፍረድ” አለችው።

6አብራምም፣ “አገልጋይሽ እንደ ሆነች በእጅሽ ውስጥ ናት፤ የፈለግሽውን አድርጊባት” አላት። ከዚያም ሦራ ስላሠቃየቻት አጋር ጥላት ኰበለለች።

7የእግዚአብሔር (ያህዌ) መልአክ አጋርን በአንድ የውሃ ምንጭ አጠገብ በምድረ በዳ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ዳር ነበር። 8መልአኩም፣ “የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፤ ከየት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” አላት፤

እርሷም፣ “ከእመቤቴ ከሦራ ኰብልዬ መምጣቴ ነው” ብላ መለሰች።

9የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ፣ “ወደ እመቤትሽ ተመለሽ፤ ለእርሷም ተገዥላት” አላት። 10ደግሞም መልአኩ፣ “ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር አይችልም” አላት።

11የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤

“እነሆ፤ ፀንሰሻል፤

ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ፤

እግዚአብሔር (ያህዌ) ችግርሽን ተመልክቷል፤

ስሙን እስማኤል16፥11 እስማኤል ማለት እግዚአብሔር ይሰማል ማለት ነው። ትዪዋለሽ።

12እርሱም እንደ ዱር አህያ ይሆናል፤

እጁንም ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ ያነሣል፤

ያገኘውም ሁሉ እጁን ያነሣበታል፤

ከወንድሞቹ ሁሉ ጋር እንደ ተጣላ ይኖራል።”16፥12 ወይም በስተ ምሥራቅ ይኖራል

13እርሷም ያናገራትን እግዚአብሔርን (ያህዌ)፣ “ኤልሮኢ” ብላ ጠራችው፤ ምክንያቱም “የሚያየኝን አሁን አየሁት”16፥13 ወይም ኋላውን አየሁት ብላ ነበርና። 14ከዚህ የተነሣ የዚያ ምንጭ ስም፣ “ብኤርለሃይሮኢ”16፥14 ብኤርለሃይሮኢ ማለት የሚያየኝ የሕያው ምንጭ ማለት ነው። ተብሎ ተጠራ፤ እስካሁንም በቃዴስና በባሬድ መካከል ይገኛል።

15አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አብራምም ስሙን እስማኤል ብሎ ጠራው። 16አብራም፣ አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ ዕድሜው 86 ዓመት ነበር።

New International Version

Genesis 16:1-16

Hagar and Ishmael

1Now Sarai, Abram’s wife, had borne him no children. But she had an Egyptian slave named Hagar; 2so she said to Abram, “The Lord has kept me from having children. Go, sleep with my slave; perhaps I can build a family through her.”

Abram agreed to what Sarai said. 3So after Abram had been living in Canaan ten years, Sarai his wife took her Egyptian slave Hagar and gave her to her husband to be his wife. 4He slept with Hagar, and she conceived.

When she knew she was pregnant, she began to despise her mistress. 5Then Sarai said to Abram, “You are responsible for the wrong I am suffering. I put my slave in your arms, and now that she knows she is pregnant, she despises me. May the Lord judge between you and me.”

6“Your slave is in your hands,” Abram said. “Do with her whatever you think best.” Then Sarai mistreated Hagar; so she fled from her.

7The angel of the Lord found Hagar near a spring in the desert; it was the spring that is beside the road to Shur. 8And he said, “Hagar, slave of Sarai, where have you come from, and where are you going?”

“I’m running away from my mistress Sarai,” she answered.

9Then the angel of the Lord told her, “Go back to your mistress and submit to her.” 10The angel added, “I will increase your descendants so much that they will be too numerous to count.”

11The angel of the Lord also said to her:

“You are now pregnant

and you will give birth to a son.

You shall name him Ishmael,16:11 Ishmael means God hears.

for the Lord has heard of your misery.

12He will be a wild donkey of a man;

his hand will be against everyone

and everyone’s hand against him,

and he will live in hostility

toward16:12 Or live to the east / of all his brothers.”

13She gave this name to the Lord who spoke to her: “You are the God who sees me,” for she said, “I have now seen16:13 Or seen the back of the One who sees me.” 14That is why the well was called Beer Lahai Roi16:14 Beer Lahai Roi means well of the Living One who sees me.; it is still there, between Kadesh and Bered.

15So Hagar bore Abram a son, and Abram gave the name Ishmael to the son she had borne. 16Abram was eighty-six years old when Hagar bore him Ishmael.