ዘፀአት 6 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 6:1-30

1ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ፤ ከኀያሉ እጄ የተነሣ እንዲሄዱ ይለቅቃቸዋል፤ ከኀያሉም እጄ የተነሣ ከአገሩ ያስወጣቸዋል” አለው።

2እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ። 3ሁሉን የሚችል አምላክ6፥3 ዕብራይስጡ ኤልሻዳይ ይለዋል። (ኤሎሂም) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) በተባለው ስሜ6፥3 ዘፀ 3፥15 ማብ ይመ ራሴን አልገለጥሁላቸውም።6፥3 ወይም እግዚአብሔር በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውምን? 4በእንግድነት የሚኖሩባትን የከነዓንን ምድር እንድሰጣቸው ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። 5ደግሞም በግብፃውያን ሥር በባርነት ሆነው ያሰሙትን የእስራኤላውያንን የሥቃይ ድምፅ ሰምቻለሁ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ።

6“ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ ከግብፃውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ እቤዣችኋለሁ። 7የራሴ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላክ (ኤሎሂም) እሆናችኋለሁ ከግብፃውያን ቀንበር ያላቀቅኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኔንም ታውቃላችሁ። 8ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

9ሙሴ ይህን ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ ተስፋ ከመቍረጣቸውና ከአስከፊ እስራታቸው የተነሣ ግን አላዳመጡትም።

10ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 11“ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን እስራኤላውያን ከአገሩ እንዲወጡ ይፈቅድላቸው ዘንድ ንገረው።”

12ሙሴ ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ)፣ “እስራኤላውያን ያልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል፤ እኔ ለራሴ ተብታባ ሰው ነኝ”6፥12 ዕብራይስጡ በዚህ ስፍራና 30 ላይ፣ ያልተገረዘ ከንፈር ይላል አለው።

የሙሴና የአሮን የትውልድ መዝገብ

13በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብፅ እንዲያወጡ አዘዛቸው።

14የየቤተ ሰቡ6፥14 በዚህ ስፍራና በ25 ላይ፣ ያለው ቤተ ሰብ የዕብራይስጥ ቃል ከጐሣም የበለጠ ነው። አለቆች እነዚህ ነበሩ፤

የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣

ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ።

እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው።

15የስምዖን ወንዶች ልጆች፣

ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና የከነዓናዊቷም ልጅ ሳኡል ነበሩ።

እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው።

16በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤

ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።

17የጌድሶን ወንዶች ልጆች በትውልዳቸው ሎቤኒና ሰሜኢ ነበሩ።

18የቀዓት ወንዶች ልጆች እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፤ ቀዓት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ።

19የሜራሪ ወንዶች ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ።

በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ነገዶች እነዚህ ናቸው።

20እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።

21የይስዓር ወንዶች ልጆች፣ ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ።

22የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፣ ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ።

23አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

24የቆሬ ወንዶች ልጆች፣ አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፤

እነዚህ የቆሬ ነገድ ጐሣ ናቸው።

25የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት።

እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ።

26እግዚአብሔር (ያህዌ) “እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብፅ አውጡ” ብሎ የነገራቸው እነዚህኑ አሮንንና ሙሴን ነበር። 27ስለ እስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት፣ የግብፅን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ነበሩ።

28እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን በግብፅ በተናገረው ጊዜ፣ 29እንዲህ አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ የነገርሁህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው።”

30ሙሴ ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “ፈርዖን ምን ብሎ ይሰማኛል? አንደበቴ ኰልታፋ ነው።”