ኢዮብ 41 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 41:1-34

1“ሌዋታንን41፥1 ምናልባት ዐዞ ሊሆን ይችላል። በመንጠቆ ልታወጣው፣

ወይም ምላሱን በገመድ ልታስረው ትችላለህን?

2መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣

ወይም ጕንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን?

3እርሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል?

በለስላሳ ቃላትስ ይናገርሃል?

4ለዘላለም ባሪያ ታደርገው ዘንድ፣

ከአንተ ጋር ይዋዋላልን?

5እንደ ወፍ አልምደኸው ከእርሱ ጋር ልትጫወት ትችላለህ?

ወይስ ለሴት አገልጋዮችህ መጫወቻነት ታስረዋለህን?

6ነጋዴዎችስ በእርሱ ላይ ይከራከራሉን?

ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል?

7ቈዳው ላይ ዐንካሴ ልትሰካ፣

ጭንቅላቱንም በዓሣ መውጊያ ጦር ልትበሳ ትችላለህን?

8እርሱን እስቲ ንካው፣

ግብግቡን ታስታውሳለህ፤ ከቶም አያላምድህም።

9እርሱን በቍጥጥር ሥር አውላለሁ ማለት ዘበት ነው፤

በዐይን ማየት እንኳ ብርክ ያስይዛል።

10ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፤

ማን ፊቱ ሊቆም ይችላል?

11ነክቶት በሰላም የሚሄድ ማን ነው?

ከሰማይ በታች ማንም የለም።41፥11 አንዳንድ ትርጕሞች፣ በዕዳ የሚጠይቀኝ ማን ነው? ከሰማይ በታች ያለው ሁሉ ንብረቴ ነው ይላሉ።

12“ስለ ብርታቱና ስለ አካላቱ ውበት፣

ስለ እጅና እግሩ ከመናገር አልቈጠብም።

13የደረበውን ልብስ ማን ሊያወልቅ ይችላል?

ማንስ ሊለጕመው ወደ መንጋጋው ይቀርባል?

14አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን፣

የአፉን ደጅ ማን ደፍሮ ይከፍታል?

15ጀርባው፣ አንድ ላይ የተጣበቁ፣

የጋሻ ረድፎች አሉት፤

16እጅግ የተቀራረቡ ስለሆኑ፣

ነፋስ በመካከላቸው አያልፍም፤

17እርስ በርስ የተገጣጠሙ ናቸው፤

አንዱ ከአንዱ ጋር ተጣብቋልና ማንም ሊለያያቸው አይችልም።

18እንጥሽታው የብርሃን ብልጭታ ያወጣል፤

ዐይኖቹም እንደ ማለዳ ጮራ ናቸው።

19ከአፉ ፍም ይወጣል፤

የእሳት ትንታግ ይረጫል።

20በሸንበቆ ማገዶ ላይ ከተጣደ ድስት እንደሚወጣ እንፋሎት፣

ከአፍንጫው ጢስ ይትጐለጐላል።

21እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤

የእሳትም ነበልባል ከአፉ ይወጣል።

22ብርታት በዐንገቱ ውስጥ አለ፤

አሸባሪነትም በፊቱ እመር እመር ይላል።

23የሥጋው ንብርብር እርስ በርስ የተጣበቀ፣

በላዩ የጸናና ከቦታው የማይናጋ ነው።

24ደረቱ እንደ ዐለት የጠጠረ፣

እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጠነከረ ነው።

25እርሱ በተነሣ ጊዜ፣ ኀያላን ይርዳሉ፤

በሚንቀሳቀስበትም ጊዜ ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።

26ጦር፣ ፍላጻ ወይም ዐንካሴ፣

ሰይፍም ቢያገኘው አንዳች አይጐዳውም።

27እርሱ ብረትን እንደ አገዳ፣

ናስንም እንደ ነቀዘ ዕንጨት ይቈጥራል።

28ቀስት አያባርረውም፤

የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው።

29ቈመጥ በእርሱ ፊት እንደ ገለባ ነው፤

ጦር ሲሰበቅ ይሥቃል።

30የሆዱ ሥር እንደ ሸካራ ገል ነው፤

እንደ መውቂያ መሣሪያም በጭቃ ላይ ምልክት ጥሎ ያልፋል።

31እንደሚፈላ ምንቸት ጥልቁን ያናውጠዋል፤

ባሕሩንም እንደ ሽቶ ብልቃጥ ያደርገዋል።

32ያለፈበትን መንገድ ብሩህ ያደርጋል፤

ቀላዩንም ሽበት ያወጣ ያስመስለዋል።

33ያለ ፍርሀት የተፈጠረ፣

እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።

34ከፍ ያሉትን ሁሉ በንቀት ይመለከታል፤

በትዕቢተኞችም ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።”

New International Version

Job 41:1-34

41 In Hebrew texts 41:1-8 is numbered 40:25-32, and 41:9-34 is numbered 41:1-26. 1“Can you pull in Leviathan with a fishhook

or tie down its tongue with a rope?

2Can you put a cord through its nose

or pierce its jaw with a hook?

3Will it keep begging you for mercy?

Will it speak to you with gentle words?

4Will it make an agreement with you

for you to take it as your slave for life?

5Can you make a pet of it like a bird

or put it on a leash for the young women in your house?

6Will traders barter for it?

Will they divide it up among the merchants?

7Can you fill its hide with harpoons

or its head with fishing spears?

8If you lay a hand on it,

you will remember the struggle and never do it again!

9Any hope of subduing it is false;

the mere sight of it is overpowering.

10No one is fierce enough to rouse it.

Who then is able to stand against me?

11Who has a claim against me that I must pay?

Everything under heaven belongs to me.

12“I will not fail to speak of Leviathan’s limbs,

its strength and its graceful form.

13Who can strip off its outer coat?

Who can penetrate its double coat of armor41:13 Septuagint; Hebrew double bridle?

14Who dares open the doors of its mouth,

ringed about with fearsome teeth?

15Its back has41:15 Or Its pride is its rows of shields

tightly sealed together;

16each is so close to the next

that no air can pass between.

17They are joined fast to one another;

they cling together and cannot be parted.

18Its snorting throws out flashes of light;

its eyes are like the rays of dawn.

19Flames stream from its mouth;

sparks of fire shoot out.

20Smoke pours from its nostrils

as from a boiling pot over burning reeds.

21Its breath sets coals ablaze,

and flames dart from its mouth.

22Strength resides in its neck;

dismay goes before it.

23The folds of its flesh are tightly joined;

they are firm and immovable.

24Its chest is hard as rock,

hard as a lower millstone.

25When it rises up, the mighty are terrified;

they retreat before its thrashing.

26The sword that reaches it has no effect,

nor does the spear or the dart or the javelin.

27Iron it treats like straw

and bronze like rotten wood.

28Arrows do not make it flee;

slingstones are like chaff to it.

29A club seems to it but a piece of straw;

it laughs at the rattling of the lance.

30Its undersides are jagged potsherds,

leaving a trail in the mud like a threshing sledge.

31It makes the depths churn like a boiling caldron

and stirs up the sea like a pot of ointment.

32It leaves a glistening wake behind it;

one would think the deep had white hair.

33Nothing on earth is its equal—

a creature without fear.

34It looks down on all that are haughty;

it is king over all that are proud.”