ኢዮብ 4 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 4:1-21

ኤልፋዝ

1ቴማናዊው ኤልፋዝም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2“አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን?

ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል?

3እነሆ፤ አንተ ብዙዎችን ታስተምር እንደ ነበር ዐስብ፤

የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፤

4ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤

የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር።

5አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤

ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም።

6እግዚአብሔርን መፍራት መታመኛህ፣

ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን?

7“አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው?

ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ?

8እኔ እንዳየሁ ክፋትን የሚያርሱ፣

መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።

9በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤

በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።

10አንበሳ ያገሣል፤ ቍጡውም አንበሳ ይጮኻል፤

የደቦል አንበሳው ጥርስ ግን ተሰብሯል።

11ብርቱው አንበሳ ዐደን በማጣት ይሞታል፤

የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።

12“ቃል በምስጢር መጣልኝ፤

ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች።

13በሚያስጨንቅ የሌሊት ሕልም ውስጥ፣

ከባድ እንቅልፍም በሰዎች ላይ በወደቀ ጊዜ፣

14ፍርሀትና መንቀጥቀጥ ያዘኝ፤

ዐጥንቶቼም ሁሉ ተናወጡ።

15መንፈስ ሽው ብሎ በፊቴ ዐለፈ፤

የገላዬም ጠጕር ቆመ።

16እርሱም ቆመ፣

ምን እንደ ሆነ ግን መለየት አልቻልሁም፤

አንድ ቅርጽ በዐይኔ ፊት ነበረ፤

በእርጭታ ውስጥ እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤

17‘ሥጋ ለባሽ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን?

ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹሕ ሊሆን ይችላልን?

18እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ ላይ እምነት ካልጣለ፣

መላእክቱንም በስሕተታቸው ከወቀሠ፣

19ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፣

መሠረታቸው ከዐፈር የሆነ፣

ከብልም ይልቅ በቀላሉ የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ?

20በንጋትና በምሽት መካከል ይደቅቃሉ፤

ሳይታሰብም ለዘላለም ይጠፋሉ።

21ያለ ጥበብ ይሞቱ ዘንድ፣

የድንኳናቸው ገመድ አልተነቀለምን?’

Japanese Contemporary Bible

ヨブ 記 4:1-21

4

エリファズのことば

1テマン人エリファズからヨブへの答え。

2「あえて、ひと言いわせてほしい。

もう黙ってはいられない。

3-4以前あなたは、悩んでいる人に向かって

神を信頼しなさいと口ぐせのように言っていた。

弱っている人、倒れそうになっている人、

立つ気力もなくして地面に座り込む人、

自暴自棄に陥った人を元気づけてきた。

5ところが、いざ自分がその身になってみると、

すっかり弱り果て、自暴自棄になっている。

6そんなときこそ、神を信頼するべきではないのか。

神は正しい人に目をかけてくださることが、

信じられないというのか。

7-8考えてもみなさい。

心底から正しくて罪のない人が

罰せられるなどという話を、

一度でも聞いたことがあるか。

罪と争いの種をまく者が悩みを刈り取ることは、

経験の教えるところだ。

9そのような者は、神の怒りの息吹によって死ぬ。

10若いライオンのように吠えたけっていても、

押しつぶされて滅びるのだ。

11いつかは、年をとって弱り果てたライオンのように

飢え、子どもたちも散り散りになる。

12耳もとのささやきのように、こっそりと、

ひとつの真理が私に伝えられた。

13あれは、人が寝静まった夜中だった。

私は幻を見たのだ。

14急に私は恐ろしくなり、

身の毛のよだつ思いに全身がわなないた。

15一つの霊が前を通り過ぎたとき、髪の毛は逆立った。

16といっても、霊の気配を感じただけで、

姿を見たわけではないが。

気味が悪いほど静まりかえった中で、

どこからともなく、こう言う声が聞こえてきた。

17『人にすぎない者が

神より正しいなどということがあろうか。

創造者よりきよいなどということがあろうか。』

18-19御使いさえ過ちを犯し、

神に信頼されていないとしたら、

ちりから造られた人間はなおさらのことだ。

人は虫のように、簡単につぶされて死ぬ。

20朝には生きていても、夕方には冷たい死体となり、

だれからも気に留められないまま永久に葬られる。

21か細いいのちの火は吹き消され、

なすすべもなく死ぬだけだ。