ኢያሱ 4 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 4:1-24

1ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ከተሻገረ በኋላ፣ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ 2“ከሕዝቡ መካከል ከየነገዱ አንዳንድ ሰው፣ በድምሩ ዐሥራ ሁለት ሰው ምረጥ፤ 3እንዲሁም ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ልክ ካህናቱ ከቆሙበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋይ አንሥተው በመሸከም ከእናንተ ጋር እንዲሻገሩና ዛሬ በምታድሩበት ቦታ እንዲያኖሯቸው ንገራቸው።”

4ስለዚህ ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የሾማቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ፤ 5እንዲህም አላቸው፤ “ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዳችሁም በእስራኤል ነገድ ቍጥር አንዳንድ ድንጋይ በትከሻችሁ ተሸከሙ፤ 6ይህም በመካከላችሁ ምልክት እንዲሆናችሁ ነው። ወደ ፊት ልጆቻችሁ፣ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው ቢጠይቋችሁ፣ 7የዮርዳኖስ ወንዝ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መቆሙን፣ እንዲሁም ታቦቱ ዮርዳኖስን በሚሻገርበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መቆሙን፣ እነዚህ ድንጋዮች ለእስራኤል ሕዝብ የዘላለም መታሰቢያ መሆናቸውን ንገሯቸው።”

8እስራኤላውያንም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔር ለኢያሱ በነገረውም መሠረት፣ በእስራኤል ነገዶች ቍጥር ልክ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል አነሡ፤ ወደ ሰፈራቸውም ይዘው በመሻገር በዚያ አኖሯቸው። 9ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ቆመውበት በነበረው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ4፥9 ወይም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አቆመ በዚሁ ስፍራ ይገኛሉ።

10ሙሴ ለኢያሱ በሰጠው መመሪያ መሠረት፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲነግር ኢያሱን ያዘዘው እስኪፈጸም ድረስ፣ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ቈዩ፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ፤ 11ሕዝቡ ሁሉ ተሻግረው እንዳበቁ፣ የእግዚአብሔር ታቦትና ካህናቱ፣ ሕዝቡ እያዩአቸው ተሻገሩ። 12የሮቤል ነገድና የጋድ ነገድ፣ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት፣ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ከእስራኤላውያን ፊት ቀድመው ተሻገሩ። 13አርባ ሺሕ ያህሉ ጦርና ጋሻቸውን ይዘው፣ ለውጊያ ዝግጁ ሆነው፣ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ።

14በዚያች ዕለት እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሕዝቡ ሙሴን እንዳከበሩት ሁሉ፣ ኢያሱንም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አከበሩት።

15ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ 16“የምስክሩን ታቦት የተሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ ወንዝ እንዲወጡ እዘዛቸው።”

17ኢያሱም ካህናቱን “ከዮርዳኖስ ውጡ” ብሎ አዘዛቸው።

18ካህናቱ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ከውሃው በመውጣት እግራቸው ደረቁን መሬት ልክ ሲነካ የዮርዳኖስ ውሃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ እንደ ቀድሞው ሁሉ ሞልቶ በዳሩ ሁሉ ይፈስስ ጀመር።

19የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ሕዝቡ ዮርዳኖስን ተሻግሮ በኢያሪኮ ምሥራቃዊ ዳርቻ በጌልገላ ሰፈረ። 20ኢያሱም ከዮርዳኖስ ወንዝ ያወጧቸውን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች በጌልገላ ተከላቸው፤ 21እስራኤላውያንንም እንዲህ አላቸው፤ “ልጆቻችሁ ወደ ፊት፣ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው አባቶቻቸውን ቢጠይቁ፣ 22‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስ በደረቅ ምድር ተሻገረ’ ብላችሁ ንገሯቸው፤ 23እኛ እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን4፥23 ዕብራይስጡ ያም ሱፍ ይላል፤ ይኸውም የደንገል ባሕር ማለት ነው። እንዳደረቀው ሁሉ፣ እናንተም እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ወንዝ በፊታችሁ አደረቀው። 24ይህን ያደረገውም፣ የእግዚአብሔር ክንድ ብርቱ መሆኑን የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁና እናንተም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለዘላለም እንድትፈሩ ነው።”

Thai New Contemporary Bible

โยชูวา 4:1-24

1เมื่อเหล่าประชากรข้ามแม่น้ำจอร์แดนไปทุกคนแล้ว องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโยชูวาว่า 2“จงคัดเลือกชายสิบสองคนจากเหล่าประชากรเผ่าละหนึ่งคน 3และสั่งพวกเขาให้ยกก้อนหินมาสิบสองก้อน จากกลางแม่น้ำจอร์แดนตรงที่เหล่าปุโรหิตยืน และตั้งไว้ในสถานที่ซึ่งเจ้าจะไปตั้งค่ายพักค่ำวันนี้”

4โยชูวาจึงเรียกชายสิบสองคนนั้นซึ่งคัดเลือกจากชนอิสราเอลเผ่าละหนึ่งคนมา 5และสั่งว่า “จงออกไปกลางแม่น้ำจอร์แดนตรงที่หีบพันธสัญญาของพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านตั้งอยู่ แล้วแบกหินขึ้นบ่ามาคนละหนึ่งก้อน ตามจำนวนเผ่าของชนอิสราเอล 6เพื่อเป็นอนุสรณ์ท่ามกลางพวกท่าน ในอนาคตเมื่อลูกหลานของท่านถามว่า ‘หินเหล่านี้มีความหมายว่าอย่างไร?’ 7จงบอกพวกเขาว่าแม่น้ำจอร์แดนแยกออกต่อหน้าหีบพันธสัญญาขององค์พระผู้เป็นเจ้าเมื่อหีบข้ามแม่น้ำจอร์แดน น้ำในแม่น้ำจอร์แดนก็แยกขาดจากกัน หินเหล่านี้จะเป็นอนุสรณ์เตือนใจชนอิสราเอลตลอดไป”

8ชนอิสราเอลก็ทำตามที่โยชูวาสั่ง พวกเขาขนหินสิบสองก้อนจากกลางแม่น้ำจอร์แดนตามจำนวนเผ่าของอิสราเอล ตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าได้ทรงบัญชาโยชูวาไว้ และยกมาวางลงในสถานที่ตั้งค่ายพักแรมของพวกเขาในคืนวันนั้น 9โยชูวาให้นำหินสิบสองก้อนที่เคยอยู่กลางแม่น้ำจอร์แดน ในบริเวณที่ปุโรหิตผู้หามหีบพันธสัญญายืนอยู่นั้นมาตั้งไว้4:9 หรือโยชูวาให้ตั้งหินสิบสองก้อนที่กลางแม่น้ำจอร์แดนในบริเวณที่ปุโรหิตผู้หามหีบพันธสัญญายืนอยู่ และหินเหล่านั้นยังคงอยู่ที่นั่นจวบจนทุกวันนี้

10ปุโรหิตผู้หามหีบพันธสัญญายืนอยู่กลางแม่น้ำตราบจนเหล่าประชากรทำครบถ้วนทุกอย่างตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโยชูวา ดังที่โมเสสได้กำชับโยชูวา เหล่าประชากรรีบรุดข้ามแม่น้ำไป 11เมื่อทุกคนข้ามไปแล้ว ประชากรพากันมองดูปุโรหิตหามหีบพันธสัญญาขององค์พระผู้เป็นเจ้าขึ้นจากแม่น้ำ 12ชนเผ่ารูเบน กาด และมนัสเสห์ครึ่งเผ่าก็ข้ามแม่น้ำไป พวกเขาคาดอาวุธนำหน้าชนอิสราเอลตามที่โมเสสได้สั่งพวกเขาไว้ 13มีคนราวสี่หมื่นคนจับอาวุธออกรบต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าบุกไปยังที่ราบเยรีโค

14วันนั้นองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงยกชูโยชูวาขึ้นต่อหน้าปวงชนอิสราเอล และพวกเขายำเกรงโยชูวาตลอดชีวิตของโยชูวาเหมือนที่เคยยำเกรงโมเสส

15แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโยชูวาว่า 16“จงสั่งปุโรหิตผู้หามหีบแห่งพันธสัญญาให้ขึ้นจากแม่น้ำจอร์แดน”

17โยชูวาก็ออกคำสั่งแก่ปุโรหิตว่า “จงขึ้นมาจากแม่น้ำจอร์แดน”

18ปุโรหิตจึงหามหีบพันธสัญญาขององค์พระผู้เป็นเจ้าขึ้นจากแม่น้ำ ทันทีที่เท้าของพวกเขาแตะพื้นตลิ่ง สายน้ำก็ไหลกลับลงท่วมตลิ่งดังเดิม

19ในวันที่สิบของเดือนแรก เหล่าประชากรข้ามแม่น้ำจอร์แดนไปตั้งค่ายพักแรมที่กิลกาล ชิดเขตแดนด้านตะวันออกของเมืองเยรีโค 20โยชูวาก็ให้ตั้งหินสิบสองก้อนที่ยกมาจากแม่น้ำจอร์แดนนั้นไว้ที่กิลกาล 21เขากล่าวแก่ชนอิสราเอลว่า “ในอนาคตเมื่อลูกหลานของท่านถามว่า ‘ก้อนหินเหล่านี้มีความหมายว่าอย่างไร?’ 22จงบอกเขาว่า ‘อิสราเอลเดินข้ามแม่น้ำจอร์แดนบนพื้นแห้ง’ 23เพราะพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านทรงบันดาลให้แม่น้ำจอร์แดนแห้งต่อหน้าพวกท่าน เพื่อพวกท่านจะข้ามไปได้ เหมือนที่พระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านเคยทำให้ทะเลแดง4:23 คือ ทะเลต้นกกแห้งเป็นทางต่อหน้าเราจนพวกเราได้ข้ามไป 24ทั้งนี้เพื่อชาวโลกทั้งปวงจะรู้ว่าพระหัตถ์ขององค์พระผู้เป็นเจ้านั้นทรงอานุภาพ และเพื่อท่านทั้งหลายจะยำเกรงพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านตลอดไป”